settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ ለአሁኑ ጊዜ ይጠቅማልን?

መልስ፤


ዕብራውያን 4፡12 ይላል፣ “የእግዚአብሔር ቃል ሕያውና የሚሠራ ነውና። ሁለትም አፍ ካለው ሰይፍ ሁሉ ይልቅ የተሳለ ነው፣ ነፍስንና መንፈስንም ጅማትንና ቅልጥምንም እስኪለይ ድረስ ይወጋል፤ የልብንም ስሜትና አሳብ ይመረምራል።” መጽሐፍ ቅዱስ በተጠናቀቀ ጊዜ በግምት ከ1900 ዓመት በፊት፣ ርግጠኝነቱና ጠቀሜታው ሳይለወጥ እስከ ዛሬ ጊዜ ድረስ ቀርቷል። መጽሐፍ ቅዱስ ዓይነተኛ ተጨባጭ ምንጭ ነው፣ እግዚአብሔር ለሰጠን መገለጥ ሁሉ፣ ስለ ራሱም ሆነ ለሰው ስላለው ዕቅድ።

መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ተፈጥሯዊ ዓለም እጅግ በርካታ መረጃ ይዟል፣ እሱም በሳይንሳዊ ምልከታዎች እና በምርምር የተረጋገጠ። አንዳንዶቹ እነዚህ አንቀጾች የሚያካትቱትም ሌዋውያን 17:11፤ መክብብ 1:6-7፤ ኢዮብ 36:27-29፤ መዝሙር 102:25-27 እና ቆላስያስ 1:16-17። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ያለው የመቤዠት ዕቅድ እንደማይታጠፍ፣ በርካታ የተለያዩ ገጸ-ባሕርያት ጥሩ ሆነው ተገልጸዋል። በእነዚህ ገለጻዎች፣ መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ በርካታ መረጃዎችን ይሰጣል፣ ስለ ሰው ባሕርይና ዝንባሌዎች። የእኛ የራሳችን የዕለት ተ’ለት ልምምድ የሚያሳየን ይህ መረጃ እጅግ ትክክለኛና የሰዎች ሁኔታ ገለጻ እንደሆነ ነው፣ ከማንኛውም የሥነ-ልቦና መጽሐፍ ይልቅ። በመጽሐፍ ቅዱስ የተመዘገቡት በርካታ ታሪካዊ ሐቆች በተጓዳኝ የቅዱሳን መጻሕፍት ምንጮች ተረጋግጠዋል። ታሪካዊ ጥናት ዘወትር እንደሚያሳየው እጅግ በርካታ ስምምነት በመጽሐፍ ቅዱስ ይዘቶችና በተጓዳኝ የቅዱሳት መጻሕፍት መሐል ስምምነት መኖሩን ነው፣ በተመሳሳይ ሁነቶች ላይ።

ሆኖም፣ መጽሐፍ ቅዱስ የታሪክ መጽሐፍ አይደለም፣ የሥነ-ልቦና መጽሐፍ፣ ወይም የሳይንስ ጋዜጣ። መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠን ገለጻ ነው፣ እሱ ማን እንደሆነ፣ እና የሱን ፍላጎትና ዕቅድ፣ ለሰው ልጆች ያለውን። የዚህ መገለጥ እጅግ ዋነኛ አካል፣ በኃጢአት ምክንያት ከእግዚአብሔር የተለየንበት ታሪክ ነው፤ እንዲሁም እግዚአብሔር ኅብረቱን ለመመለስ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ በተደረገ መሥዋዕት የሰጠን ነው። ለመቤዠት ያለን መሻት አልተለወጠም። እግዚአብሔርም ከእሱ ጋር ሊያስታርቀን ያለው መሻት እንዲሁ።

መጽሐፍ ቅዱስ እጅግ በርካታ ትክክለኛና ጠቃሚ መረጃ ይዟል። የመጽሐፍ ቅዱስ ዋነኛ ጠቃሚ መልእክት—መቤዠት— በመላው ዓለም እና ሳያቋርጥ በሰው ልጆች ላይ እየተተገበረ ነው። የእግዚአብሔር ቃል ፈጽሞ አያረጅም፣ አይቀየርም፣ ወይም እየተሻሻለ አይሄድም። ባህሎች ይቀየራሉ፣ ሕግጋት ይቀየራሉ፣ ትውልዶች ይመጣሉ ይሄዳሉ፣ ነገር ግን የእግዚአብሔር ቃል ዛሬም ጠቃሚ ነው፣ በመጀመሪያ ሲጻፍ እንደነበረው። ቃሉ ሁሉ ተለይቶ ዛሬ ላይተገበርብን ይችላል፣ ነገር ግን ቃሉ ሁሉ የያዘውን ሐቅ ዛሬ በሕይወታችን መተግበር እንችላለን፣ ይገባናልም።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ ለአሁኑ ጊዜ ይጠቅማልን?
© Copyright Got Questions Ministries