settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የቃየን ሚስት ማን ነበረች? የቃየን ሚስቱ እህቱ ነበረች?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ የቃየን ሚስት ማን እንደነበረች ለይቶ አይናገርም፡፡ ብቸኛ መልስ ሊሆን የሚችለው የቃየን ሚስቱ እህቱ ወይም የእህት/ወንድም ልጅ ወይም የእህት/ወንድም ቅድመ-አያት፤ወ.ዘ.ተ ነበረች፡፡ ቃየን አቤልን በገደለ ጊዜ ዕድሜው ስንት እንደነበር አይናገርም (ኦሪት ዘፍጥረት 4፤8)፡፡ ሁለቱም ገበሬዎች ስለነበሩ ምናልባት ሁለቱም የራሳቸው ቤተሰብ ያላቸው የደረሱ ጎልማሶች ነበሩ፡፡ አቤል በተገደለበት ጊዜ በእርግጠኝነት አዳም እና ሔዋን ልክ ከቃየል እና ከአቤል ይልቅ የበለጡ ልጆችን ወልደው ነበር፡፡ በእርግጠኝነት በኃላ በጣም ብዙ ልጆች ነበሯቸው (ኦሪት ዘፍጥረት 5፤4)፡፡ ቃየል አቤልን ከገደለ በኃላ ለህይወቱ የመፍራቱ እውነታ (ኦሪት ዘፍጥረት 4፤14) አስቀድሞ ሌሎች ብዙ ልጆች እና ምናልባትም የአዳም እና የሔዋን አያት ልጆች በዚያን ጊዜ መኖራቸው እንደነበር ያን ያመለክታል፡፡ የቃየን ሚስት (ኦሪት ዘፍጥረት 4፤17) የአዳም እና የሔዋን ሴት ልጅ ወይም የልጅ ልጅ ነበረች፡፡

አዳም እና ሔዋን የመጀመሪያዎቹ (እና ብቸኞች) የሰው ፍጡሮች ስለነበሩ ልጆቻቸው እርስ በእርሳቸው ከመጋባት ይልቅ ሌላ ምርጫ ባልነበራቸው ነበር፡፡ እግዚአብሔር ከጊዜያት በኃላ በቤተ-ዘመድ መሐከል የሚደረግ ጋብቻ አስፈላጊ እንዳይሆን (ኦሪት ዘሌዋውያን 18፤6-8) ለማድረግ በቂ ሰዎች እስከነበሩበት ጊዜ ድረስ የቤተ-ዘመድ ጋብቻን አልከለከለም ነበር፡፡ ዛሬ በዘመድ መሐከል የሚደረግ የጾታ ግንኙነት ብዙውን ጊዜ የዘረ-መል ግድፈቶችን የማምጣቱ ምክንያት ተመሳሳይ ዘረ-መል ያላቸው ሁለት ሰዎች (ያም ወንድም እና እህት) አንድ ላይ ልጆች በሚኖሩአቸው ጊዜ የተጨቆነው የዘር-መላቸው ባህርይ የጎላ የመሆን ከፍተኛ አደጋ አለ፡፡ ከተለያዩ ቤተሰቦች የሆኑ ሰዎች ልጆች በሚኖራቸው ጊዜ እነዚያ ሁለቱም ቤተሰቦች ተመሳሳይ ባህርያትን መሸከም በከፍተኛ ሁኔታ የሚሆን አይመስልም፡፡ ከዘር ግንድ ጋር የተያያዙ ችግሮች ከመብዛታቸው፤ከመባዛታቸው፤እና ከትውልድ ወደ ትውልድ ከመተላለፋቸው ጋር የሰው የዘረ-መል መለያው በዘመናት ሁሉ ውስጥ በጨመረ ሁኔታ ተበክሏል፡፡ አዳም እና ሔዋን ምንም ዓይነት የዘረ-መል ግድፈት አልነበራቸውም እና የመጀመሪያዎቹ ጥቂት የዘር ሐረግ ትውልዳቸው አሁን እኛ ካለን ይልቅ በጣም የተሻለ የጤንነት ጥራት እንዲኖራቸው አስችሏቸዋል፡፡ የአዳም እና የሔዋን ልጆች ምንም ቢሆን ጥቂት የዘረ-መል ግድፈት ነበረባቸው፡፡ ስለሆነም እርስ በእርሳቸው መጋባት ለእነርሱ አስጊ አልነበረም፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የቃየን ሚስት ማን ነበረች? የቃየን ሚስቱ እህቱ ነበረች?
© Copyright Got Questions Ministries