settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር አሁንም ለእኛ ይናገራልን?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር ሊሰማ በሚችል መልኩ ለሕዝቡ እንደሚናገር ብዙ ጊዜ መዝግቧል (ዘጸአት 3፡14፤ ኢያሱ 1፡1፤ መሳፍንት 6፡18፤ 1ኛ ሳሙኤል 3፡11፤ 2ኛ ሳሙኤል 2፡1፤ ኢዮብ 40፡1፤ ኢሳይያስ 7፡3፤ ኤርምያስ 1፡7፤ ሐዋርያት ሥራ 8፡26፤ 9፡15— ይህ በርግጥ ጥቂት ናሙና ነው)። እግዚአብሔር ዛሬም ሊሰማ ለሚችል ሰው የማይናገርበት ምክንያት መኖሩን ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክንያት አይኖርም። በመቶዎች የሚቆጠር ጊዜ መጽሐፍ ቅዱስ እግዚአብሔር እንደሚናገር መዝግቧል፣ እኛ ማስታወስ ያለብን ይህም 4000 ዓመታት የሰው ልጅ ታሪክ ሂደት ሁሉ መሆኑን ነው። እግዚአብሔር እንዲሰማ የሚናገረው በልዩነት ነው፣ በሕግ አይደለም። በመጽሐፍ ቅዱስ የተመዘገቡት የእግዚአብሔር ንግግር ሁኔታዎች እንኳ፣ በሚሰማ ድምጽ፣ የውስጥ ድምጽ፣ ወይም የአዕምሮ እይታ ቢሆንም ዘወትር ግልጽ ላይሆን ይችላል።

እግዚአብሔር ዛሬም ለሕዝቡ ይናገራል። በመጀመሪያ፣ እግዚአብሔር በቃሉ በኩል ለእኛ ይናገራል (2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16-17)። ኢሳይያስ 55፡11 እንዲህ ይነግረናል፤ “ከአፌ የሚወጣ ቃሌ እንዲሁ ይሆናል የምሻውን ያደርጋል የላክሁትንም ይፈጽማል እንጂ ወደ እኔ በከንቱ አይመለስም።” መጽሐፍ ቅዱስ የእግዚአብሔርን ቃል መዝግቧል፣ ማወቅ የሚገባንን ሁሉ፣ እንድንድንና የክርስትና ሕይወት እንኖር ዘንድ። ሁለተኛ ጴጥሮስ 1፡3 እንዲህ ይላል፣ “የመለኮቱ ኃይል፥ በገዛ ክብሩና በበጎነቱ የጠራንን በማወቅ፥ ለሕይወትና እግዚአብሔርን ለመምሰል የሚሆነውን ነገር ሁሉ ስለ ሰጠን።”

ሁለተኛ፣ እግዚአብሔር በአዕምሮ እይታ፣ በሁነቶች፣ እና በአስተሳሰቦች በኩል ይናገራል። እግዚአብሔር በሕሊናችን ክፉና ደጉን እንድንለይ ይረዳናል (1ኛ ጢሞቴዎስ 1፡5፤ 1ኛ ጴጥሮስ 3፡16)። እግዚአብሔር የእኛ አዕምሮ የሱን ሐሳብ ይረዳ ዘንድ በማጽናት ሂደት ላይ ነው (ሮሜ 12፡2)። እግዚአብሔር፣ ሁኔታዎች በሕይወታችን ተፈጥረው ያልፉ ዘንድ ይፈቅዳል፣ ሊያመላክተን፣ ሊለውጠን፣ እንዲሁም በመንፈሳዊነት እናድግ ዘንድ ሊረዳን (ያዕቆብ 1፡2-5፤ ዕብራውያን 12፡5-11)። አንደኛ ጴጥሮስ 1፡6-7 ያስታውሰናል፤ “በዚህም እጅግ ደስ ይላችኋል፥ ነገር ግን በእሳት ምንም ቢፈተን ከሚጠፋው ወርቅ ይልቅ አብልጦ የሚከብር የተፈተነ እምነታችሁ፥ ኢየሱስ ክርስቶስ ሲገለጥ፥ ለምስጋናና ለክብር ለውዳሴም ይገኝ ዘንድ አሁን ለጥቂት ጊዜ ቢያስፈልግ በልዩ ልዩ ፈተና አዝናችኋል።”

በመጨረሻም፣ እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ በሚሰማ መልኩ ሊናገር ይችላል። ይህም በእጅጉን አጠራጣሪነት ቢኖረውም፣ ይህ ይከሰታል፣ አንዳንድ ሰዎች ዘወትር እንደሚሆን እንደሚያስረግጡት። እንዲሁም፣ በመጽሐፍ ቅዱስም እግዚአብሔር በሚሰማ መናገሩ መደበኛ ሳይሆን በተለየ ነው። ማንም እግዚአብሔር እንደሚናገረው ቢገልጽ/ብትገልጽ ዘወትር፣ የተባለው እና መጽሐፍ ቅዱስ የሚለው ይነጻጸራል። እግዚአብሔር ዛሬ የሚናገር ከሆነ፣ የእሱ ቃል፣ በመጽሐፍ ቅዱስ ላይ ካለው ጋር ሙሉ ለሙሉ መስማማት አለበት (2ኛ ጢሞቴዎስ 3፡16-17)። እግዚአብሔር ራሱን አይቃረንም።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር አሁንም ለእኛ ይናገራልን?
© Copyright Got Questions Ministries