settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ወደ መንግስተ ሰማይ የሚያስገባው ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ነውን?

መልስ፤


“እኔ በመሰረቱ መልካም ሰው ነኝ። ስለዚህ ወደ መንግስተ ሰማይ እገባለሁ” “በእርግጥ አንዳንዴ መጥፎ ነገሮችን እፈፅማለሁ። ነገር ግን በይበልጥ ደግሞ መልካም ተግባሮችን አደርጋለሁ፣ ስለዚህ ወደ መንግስተ ሰማይ እገባለሁ።” “በመጽሐፍ ቅዱስ ባለማመኔ ብቻ እግዚሐብሔር ወደ ገሃነም እሳት ይልከኛል ብዬ አላስብም።” ዘመኑ ተለውጧል! “በህጻናት ላይ የጭካኔ ተግባር የሚፈፅሙና ነፍሰ ገዳዮች ብቻ ናቸው ወደ ገሃነም እሳት የሚጣሉት።”

እነዚህ ሁሉ የተለመዱ አስተሳሰቦች ናቸው። ሐቁ ግን ሁሉም ውሸቶች ናቸው። የዚህ ዓለም ገዢ የሆነው ሰይጣን እነዚህን አስተሳሰቦች በአዕምሯችን እንዲተከሉ አድርጓል። እሱና ማንም የሱን መንገድ የሚከተል ሁሉ የእግዚሐብሔር ጠላት ነው። (1ኛ ጴጥሮስ 5፡ 8)። ሰይጣን አታላይ ነው። ብዙ ጊዜ እራሱን መልካም አስመስሎ ይቀርባል። (2ኛ ቆሮንቶስ 11፡ 4)፣ የእግዚሐብሔር ተከታይ ያልሆኑትን ሰዎች አዕምሮ ይቆጣጠራል።

“ለእነርሱም የእግዚሐብሔር ምሳሌ የሆነ የክርስቶስ የክብሩ ወንጌል ብርሃን እንዳያበራላቸው፣ የዚህ ዓለም አምላክ የማያምኑትን ሃሳብ አሳወረ። (2ኛ ቆሮንቶስ 4፡4) ። እግዚሐብሔር ለጥቃቅን ኃጢያቶች ግድ የለውም፤ ወይም ገሃነም እሳት የተዘጋጀው “ለመጥፎ ሰዎች” ነው ብሎ ማመን ሐሰት ነው። “ትንሿ ነጭ ውሸት” ሳትቀር ሁሉም ኃጢያት ከእግዚሐብሔር ይለየናል። ሁሉም ኃጢያት ሰርተዋል፤ ማንም ሰው በራሱ መልካም ሆኖ ወደ መንግስተ ሰማይ ለመግባት ብቃት የለውም (ሮሜ 3፡ 23)። ወደ መንግስተ ሰማይ መግባታችን የተመሰረተው መልካም ስራችን ከመጥፎ ተግባራችን አመዝኖ ስለተገኘ አይደለም። ነገሩ እንደዚህ ከሆነ ሁላችንም እንከስራለን። “በፀጋ ከሆነ ግን ከስራ መሆኑ ቀርቷአል፣ ፀጋ ያለዚያ ፀጋ መሆኑ ቀርቶአል።” (ሮሜ 11፡6) ምንም ዓይነት መልካም ነገር ብናደርግ ወደ መንግስተ ሰማይ መግባት አንችልም (ቲቶ 3፡5) “በጠበበው ደጅ ግቡ፣ ወደ ጥፋት የሚወስደው ደጅ ሰፊ፣ መንገዱም ትልቅ ነውና፣ ወደእርሱም የሚገቡ ብዙዎች ናቸው።” (ማቴዎስ 7፡13)። እግዚሐብሔርን ማምለክ ተወዳጅ ባልሆነ ባህል ሁሉም የኃጢያትን ሕይወት በመለማመድ የሚኖሩ ቢሆኑ እግዚሐብሔር ድርጊታቸውን ይቅር አይለውም።

“በበደላችሁና በኃጢያታችሁ ሙታን ነበራችሁ፤ በእርሱም፥ በዚህ ዓለም እንዳለው ኑሮ፣ በማይታዘዙትም ልጆች ላይ አሁን ለሚሰራው መንፈስ አለቃ እንደሆነው በአየር ላይ ስልጣን እንዳለው አለቃ ፈቃድ፣ በፊት ተመላለሳችሁባቸው። (ኤፌሶን 2፡ 1-2)።

እግዚሐብሔር ዓለም እንደፈጠረ እንከንየለሽና መልካም ነበረች። ከዚያም አዳምንና ሄዋንን ፈጠረና እግዚሐብሔርን መከተልና መታዘዝን የሚያስችል ምርጫ እንዲኖራቸው ነፃ ህሊና ሰጣቸው። ነገር ግን ለእግዚሐብሔር እንዳይታዘዙ በሰይጣን ተፈተኑና በሃጢያት ወደቁ። ከእግዚሐብሔር ጋር የቀረበ ግንኙነት እንዳይኖራቸው ይህ ስራቸው ለያቸው (እኛንም ጨምሮ ከነሱ በኋላ በመጣው ትውልድ እንደሆነው ሁሉ) እሱ ፍፁምና ቅዱስ ነው። በኃጢያትም ላይ መፍረድ ይገባዋል። እንደ ኃጢያተኞች በራሳችን ከእግዚሐብሔር ጋር መታረቅ አንችልም። በመንግስተ ሰማይ ከእግዚሐብሔር ጋር አብረን እንድንሆን መንገድ አዘጋጀልን። “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚሐብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” ( ዮሐንሰ 3፡ 16)። “የኃጢያት ደመወዝ ሞት ነውና፣ የእግዚሐብሔር የፀጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” (ሮሜ 6፡ 23)። እኛ እንዳንሞት ስለታሰበ ነው ክርስቶስ ተወልዶ ለኃጢያታችን የሞተው። በሞተ በሦስተኛው ቀን ከመቃብር ተነሳ። (ሮሜ 4፡ 25) በዚህም በሞት ላይ ያለውን አሸናፊነት አረጋግጧል። በእግዚሐብሔርና በሰው መካከል የነበረውን ክፍተት በመዝጋት እስካመንን ድረስ ከእርሱ ጋር ግላዊ ግንኙነት እንዲኖረን አደረገ።

“እውነተኛ አምላክ ብቻ የሆንህ አንተን የላክኸውንም ኢየሱስ ክርስቶስን ያውቁ ዘንድ ይህቺ የዘላለም ሕህወት ናት።” (ዮሐንስ 17፡ 3)። በርካታ ሰዎች በእግዚሐብሔር ያምናሉ፣ ሰይጣንም እንዲሁ፤ ነገር ግን ድነትን ለመቀበል ወደ እግዚሐብሔር ዞር ማለት አለብን። ከእርሱ ጋር ግላዊ ግንኙነት በመፍጠር ከኃጢያት እርቀን ልንከተለው ይገባል። ባለን ነገርና በምንከተለው እንቅስቃሴ ሁሉ በኢየሱስ መታመን አለብን። “እርሱም ለሚያምኑ ሁሉ የሆነ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን የሚገኘው የእግዚሐብሔር ፅድቅ ነው ልዩነት የለምና።” (ሮሜ 3፡ 22)። በክርስቶስ በኩል ካልሆነ ሌላ የድነት መንገድ እንደሌለ መጽሐፍ ቅዱሳችን ያስተምራል። ኢየሱስ በዮሐንስ 14፡6 እንዲህ ይላል “እኔ መንገድና እውነት ሕይወትም ነኝ፤ ከእኔ በቀር ወደአብ የሚመጣ የለም።”

የድነት ብቸኛ መንገድ ኢየሱስ ነው፣ ምክኒያቱም ለኃጢያታችን ቅጣት የሚከፍልልን እሱ ብቻ ስለሆነ ነው። (ሮሜ 6፡ 23)። ማንም ሌላ ኃይማኖት ስለኃጢያት ጥልቀትና ከባድነት እንዲሁም ውጤት የሚያስተምር የለም። ኢየሱስ ክርስቶስ ብቻ ነው ለኃጢያት የሚከፈለውን ሊገመት የማይችል ክፍያ ያቀረበው። ሌላ ኃይማኖት ይህን ማድረግ አይችልም። የሌላ “ኃይማኖት መስራች” አምላክ ሆኖ እንደሰው የታየ የለም። ( ዮሐንስ 1፡ 1,14)። ግምት የለሽ እዳ የሚከፈልበት ብቸኛ መንገድ በመሆኑ። እሱ እዳችንን መክፈል እንዲችል ኢየሱስ አምላክ መሆን ነበረበት። ለመሞት እንዲችል ሰው መሆን ነበረበት። ድነት በብቸኝነት የሚገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ነው! “መዳንም በሌላ በማንም የለም፣ እንድንድንበት ዘንድ የሚገባን ለሰዎች የተሰጠ ስም ከሰማይ በታች ሌላ የለምና።”

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ወደ መንግስተ ሰማይ የሚያስገባው ብቸኛው መንገድ ኢየሱስ ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries