settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ዳግም የተወለደ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


ለዚህ ጥያቄ አስረግጦ መልስ የሚሰጠን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በዮሐንስ ወንጌል ምዕራፍ 3 ከቁጥር 1-21 ውስጥ ይገኛል። ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ፈሪሳዊና አይሁድ መሪዎች አንዱ ከሆነው ከኒቆዲሞስ ሲነጋገር እንመለከታለን። ኒቆዲሞስ ወደ ኢየሱስ የመጣው በምሽት ሲሆን ለኢየሱስ የሚያቀርባቸውን ጥያቄዎች ይዞ ነበር። ኢየሱስ ከኒቆዲሞስ ጋር ሲነጋገር እንዲህ አለ፡ “ እውነት እልሐለሁ አንድ ሰው ዳግም ካልተወለደ በስተቀር የእግዚሐብሔርን መንግስት አይወርስም”። ኒቆዲሞስ በበኩሉ እንዲህ ሲል ጠየቀ “ሰው ከሸመገለ በኋላ እንዴት ዳግም ይወለዳል?” እርግጠኛ ነኝ ወደ እናቱ ማህፀን እንደገና ተመልሶ ሊወለድ አይችልም። ኢየሱስም እንዲህ ሲል መለሰለት “እውነት እልሐለሁ አንድ ሰው በውሃና በመንፈስ ካልተጠመቀ በስተቀር ወደ እግዚሐብሔር መንግስት አይገባም”። ስጋ ስጋን ይወልዳል፣ መንፈስ ግን መንፈስን ይወልዳል፣ እንደገና ዳግም መወለድ አለብህ ብዬ ስለተናገርኩህ ልትደነቅ አይገባም። (ዮሐንስ 3፡3-7)

“ዳግም መወለድ” የሚለው ቃል በግልፅ ሲተነተን ከላይ የተወለደ ማለት ነው”። ኒቆዲሞስ የሚያንገበግብ ጉዳይ ነበረው። የመንፈስ ተሃድሶ፣ ወይም ከልብ መለወጥን ይፈልግ ነበር። አዲስ ልደት፣ዳግም ልደት፣ የእግዚሐብሔር እርምጃ ሲሆን ለሚያምን ሰው የዘላለም ህይወት የሚያጎናፅፈው ነው።(2ኛ ቆሮንቶሰ 5፡17 ፣ ቲቶ 3፡5 ፣ 1ኛ ጴጥ 1፡3 ፣ 1ኛ ዮሐ 2፡29 ፣ 3፡9 ፣ 4፡7 ፣ 5፡1-4 ፣ 18) እንደተጠቀሰው ዳግም ልደት የሚለው ቃል በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን “የእግዚሐብሔር ልጅ መሆን” የሚለውን ሃሳብ በውስጡ ይዟል።

“ለምንድነው አንድ ሰው ዳግም ልደት ያስፈለገው?” የሚለው ቃል መነሳቱ አይቀርም። ሐዋሪያው ጳውሎስ በኤፌሶን 2፡1 እንዲህ ይላል“በመተላለፋችሁና በሃጢያታችሁ ሙታን የነበራችሁትን እናንተን ህያው አደረጋችሁ።” ለሮማውያንም በሮሜ 3፡ 23 ሐዋርያው እንዲህ ጽፎላቸዋል“ሁሉም ሃጢያት ሰርተዋል የእግዚሐብሔርም ክብር ጎድሏቸዋል።” ስለዚህ ሰዎች ሃጢያታቸው እንዲሰረይላቸውና ከእግዚሐብሔር ጋር ግንኙነት እንዲኖራቸው ከፈለጉ ዳግም ሊወለዱ ይገባል።

ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል? ኤፌሶን 2፡8-9 እንዲህ ያብራራዋል፡ “በፀጋ በእምነት ድናችኋል፤ ይህ ከናንተ ሳይሆን የእግዚሐብሔር ስጦታ ነው፤ በስራ አይደለምና ማንም እንዳይመካ።” አንድ ሰው “ድነት ሲያገኝ” እሱ ወይም እሷ ዳግም ተወልዷል/ተወልዳለች። በአዲሱ ልደት የተነሳ የእግዚሐብሔር ልጅ ሆኖ በመንፈስ ታድሷል፤ በመንፈስ “ዳግም ልደት” ማለት የኛን የሃጢያት ዋጋ ለመክፈል በመስቀል ላይ በሞተው በኢየሱስ ክርስቶስ ማመን ማለት ነው። ስለዚህ “ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው አልፏል፤ እነሆ አዲሱ መጥቷል።” ( 2ኛ ቆሮ 5፡17)።

ከዚህ ቀደም ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ ግል አዳኝህ ካልተቀበልከው መንፈስ ቅዱስ ለልብህ ሲናገር እርምጃ መውሰድ አትፈልግም ይሆን? ዳግም እንድትወለድ ያስፈልጋል። ዛሬ የንስሃን ፀሎት በመፀለይ በክርስቶስ አዲስ ፍጥረት መሆን ይገባሐል። “ለተቀበሉት ሁሉ ግን፥ በስሙ ለሚያምኑት ለእነርሱ የእግዚሐብሔር ልጆች ይሆኑ ዘንድ ስልጣንን ሰጣቸው። እነርሱም ከእግዚሐብሔር ተወለዱ እንጂ ከደም ወይንም ከስጋ አልተወለዱም።” (ዮሐንስ 1፡ 12-13)።

ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝህ በመቀበል ዳግም ልትወለድ ከፈለግህ የሚከተለውን ፀሎት አብረኸን ፀልይ። አስታውስ ይህንን ፀሎት ወይም ሌላ አይነት ፀሎት ማቅረብ አያድንህም። ከኃጢያት የምትድነው በኢየሱስ ክርስትስ ብቻ ስታምን ነው። ይህ ፀሎት እግዚሐብሔር ድነትን ስለሰጠህ በርሱ መታመንህን ለማሳየትና ምስጋና ማቅረብ እንደሚገባህ የሚያመለክትህ ቀላል መንገድ ነው። “እግዚሐብሔር ሆይ አንተን ስለበደልኩ ቅጣት ይገባኛል። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኔ የሚገባውን ቅጣት ስለከፈለልኝ በርሱ በማመኔ ይቅርታ ተደርጎልኛል፤ በምህረትህ እታመናለሁ፤ ስለአስደናቂው ፀጋህ እንዲሁም ስለዘላለም ሕይህወት ስጦታህ አመሰግንሐለሁ! አሜን!

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ዳግም የተወለደ ክርስቲያን ማለት ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries