settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ በርግጥ ነበረን? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መኖር አንዳች ዓይነት ታሪካዊ ማስረጃ አለውን?

መልስ፤


በተለይ፣ ይህ ጥያቄ ሲጠየቅ፣ ጠያቂው ግለሰብ ጥያቄውን የሚያቀርበው “ከመጽሐፍ ቅዱስ ውጪ” በሆነ መልኩ ነው። ይሄንን ሐሳብ ግን እንዳለ አንወስደውም፣ ማለትም መጽሐፍ ቅዱስ ለኢየሱስ ሕላዌ ማስረጃ እንደሌለው ተደርጎ የቀረበውን። አዲስ ኪዳን ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ በመቶ የሚቆጠሩ ማጣቀሻዎች አሉት። ከእነሱም ወንጌላት የተጻፉባቸውን ቀናት የሚጠቅሱት በሁለተኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም ነው፣ ኢየሱስ ከሞተ ከ100 ዓመት በኋላ። ምንም እንኳ ጉዳዩ ይህ ቢሆንም (እኛ በእጅጉን የምንከራከርበት)፣ የጥንት ማስረጃዎችን በተመለከተ፣ ከ200 ዓመት በታች የሚሆኑት ጽሑፎች፣ ሁነቱ ከተከናወነ በኋላ እንደ ተጨባጭ ማስረጃ ይወሰዳሉ። ከዚህም በላይ፣ አብዛኞቹ ብዙሃን ሊቃውንት (ክርስቲያንና ክርስቲያን ያልሆኑት) እንደሚያረጋግጡት የጳውሎስ መልዕክቶች (ቢያንስ አንዳንዶቹ) በርግጥ በጳውሎስ የተጻፉት በአንደኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም አጋማሽ ነው፣ ከኢየሱስ ሞት ከ40 ዓመት ወዲህ። የጥንታዊ ጽሑፎችን ማስረጃ በተመለከተ፣ ይህም የተለየና ጠንካራ ማስረጃ የሚሆን ነው፣ ኢየሱስ የሚባል ሰው በእስራኤል በአንደኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም መኖሩን የሚያስረግጥ።

ሌላው ግንዛቤ ውስጥ መግባት ያለበት ጠቃሚ ጉዳይ በ70 ዓ.ም ሮሞች ኢየሩሳሌምንና አብዛኛውን እስራኤል መውረራቸውና ነዋሪዎቹን መግደላቸው ነው። ሞላው ከተሞች ተቃጥለው ወድመዋል ማለት ይቻላል። እናም መደነቅ አይኖርብንም፣ አብዛኞቹ ኢየሱስ እንደነበረ የሚያሳዩት ማስረጃዎች ቢደመሰሱ። አብዛኞቹ የኢየሱስ የዓይን ምስክሮች ሊገደሉ ይችላሉ። እነዚህ ሀቆች በሕይወት የተረፉትን የኢየሱስን የዓይን ምስክሮች እማኝነት ውስን ያደርጉታል።

የኢየሱስ አገልግሎት በአብዛኛው የተከናወነው በአንጻራዊ መልኩ የሮሜ ግዛት በሆነ በአንድ ጥግ ባለ እጅግም ጠቀሜታ ባልነበረው ስፍራ ነበር ብሎ መውሰድ ይቸላል። አስገራሚ መጠን ያለው መረጃ ስለ ኢየሱስ የሚገኘው ሃይማኖታዊ ካልሆኑ ታሪካዊ ምንጮች ነው። በጣም ጠቃሚ የሆኑት ስለ ኢየሱስ የሚገልጹት ጥቂት ታሪካዊ ማስረጃዎች የሚከተሉት ይገኙባቸዋል፡

የአንደኛው ክፍለ ዘመን የሮሜ ታሲተስ፣ እሱም የጥንታዊው ዓለም በጣም ትክክለኛ ታሪክ ጸሐፊ ተደርጎ የሚወሰደው፣ ስለ ባዕድ አምላኪያን “ክርስቲያኖች” ጠቅሷል (ከክሪስተስ፣ እሱም በላቲን ክርስቶስ)፣ በጴንጤናዊው ጲላጦስ፣ በጠባርዮስ አገዛዝ መከራ የተቀበሉት። ሱቶንዩስ፣ የንጉሠ ነገሥቱ የሀድሪያን ዋና ጸሐፊ ክርስቱስ (ክርስቶስ) የሚባል ሰው በአንደኛው ክፍለ ዘመን እንደኖረ ጽፏል (አናልስ 15.44)።

ፍላቪዩስ ጆሴፈስ በጣም የታወቀ የአይሁድ ታሪክ ጸሐፊ ነው። በእሱ አንቲኩቲስ ስለ ያዕቆብ ይጠቅሳል፣ “የኢየሱስ ወንድም፣ እሱም ክርስቶስ የሚባለው።” አወዛጋቢ ቁጥር እዚህጋ አለ፣ (18፡3) እንዲህ የሚል፣ “እናም በዚህ ጊዜ ኢየሱስ የሚባል አስተዋይ ሰው ነበር፣ እሱን ሰው ብሎ መጥራት ተገቢ ከሆነ። እሱ አስገራሚ ለውጦችን አሳይቷል… እሱ ክርስቶስ ነበር… እሱም በሦስተኛው ቀን በሕይወት ሆኖ ተከሰተላቸው፣ መለኮታዊ ነቢያት እነዚህን እንደ ተነበዩት፤ እንዲሁም ሌሎች አስር ሺህ አስገራሚ ነገሮችን እሱን በተመለከተ እንደተናገሩት።” አንድ ጽሑፍ እንዲህ ይነበባል፣ “ በዚህ ጊዜም ኢየሱስ የሚባል አስተዋይ ሰው ነበር። ጠባዩም መልካም ነው እናም [እሱ] መልካም እንደነበር ይታወቃል። እንዲሁ ብዙ ሰዎች ከአይሁድ መካከልም ሆነ ከሌሎች ሕዝቦች የእሱ ደቀ መዛሙርት ሆነዋል። ጲላጦስ እንዲሰቀልና እንዲሞት ፈረደበት። ነገር ግን የእሱ ደቀ መዛሙርት የሆኑት ደቀ መዛሙርትነታቸውን አላቆሙም። እነሱም ከስቅለቱ ከሦስት ቀናት በኋላ እንደታያቸውና ሕያው እንደሆነ መስክረዋል፤ በመሠረቱም ምናልባት መሲሕ ሳይሆን እንዳልቀረና ስለእሱም ነቢያት ድንቆችን እንተነበዩ።”

ጁሊየስ አፍሪካነስ ታሪክ ጸሐፊውን ታሉስን ጠቅሶ የክርስቶስን ስቅለት ተከትሎ ስለተከሰተው ጨለማ አብራርቷል (የሚገኙ ጽሑፎች፣ 18)።

ፕሊኒ ወጣቱ፣ በደብዳቤዎች 10፡96፣ ስለ ጥንት ክርስቲያኖች የአምልኮ ሥርዓት አስፍሯል፣ ከዚህም በተጨማሪ ክርስቲያኖች ኢየሱስን እንደ እግዚአብሔር ያመልኩ እንደነርና በጣም ሥነ ምግባራዊ እንደነበሩ ሲሆን፣ በተጨማሪም ስለ ፍቅር ግብዣና ስለ ጌታ ራት ጠቅሷል።

የባቢሎናዊ ታልሙድ (ሳሄንድሪን 43ሀ) የኢየሱስን በፋሲካ ዋዜማ መሰቀል ያጸናል፣ እንዲሁም በክርስቶስ ላይ የቀረቡት ክሶች አስማትን መፈጸምና የአይሁድን ሃይማኖት መተውን ማበረታታት ነበር።

የሳሞሳታው ሉሲያን የሁለተኛው ክፍለ ዘመን የግሪክ ጸሐፊ ሲሆን ኢየሱስ በክርስቲያኖች ይመለክ እንደነበር፣ አዲስ ትምህርቶችን ማስተዋወቁን፣ እንዲሁም ለእነሱ እንደተሰቀለ አስፍሯል። እሱ እንዳለው የኢየሱስ ትምህርቶች የአማኞች ወንድማማችነትን ጨምሮ፣ የመለወጥ ጠቀሜታ፣ እናም ሌሎች ጣዖታትን የመካድ ጠቀሜታን ጠቅሷል። ክርስቲያኖች የኖሩት በኢየሱስ ሕግ መሠረት ነበር፣ ራሳቸው ሕያው እንደሆኑ ያምናሉ፣ ሞትን ባለመፍራት ባሕርይ ነበሩ በፍቃዳቸው የተሰጡ፣ እንዲሁም ቁሳዊ በሆኑ ነገሮች ያልተያዙ ነበሩ።

ማራ ባር ሴራፒኦን እንደሚያረጋግጠው ኢየሱስ ብልህ እና መልካም ሰው ነበር፣ በብዙዎች ዘንድም የእስራኤል ንጉሥ እንደነበር ይታሰባል፣ በአይሁድ እንዲሞት የተደረገ፣ በተከታዮቹ ትምህርትም ሕያው የሆነ ነው።

ከዚያም የግኖስቲክ ጽሑፎች ይኖሩናል (የእውነት ወንጌል፣ የዮሐንስ ራዕይ፣ የቶማስ ወንጌል፣ የትንሣኤ መግለጫ፣ ወዘተ) እነዚህ ሁሉ ኢየሱስን ይገልጻሉ።

እንደ እውነቱ፣ ወንጌልን ከቀደምት ክርስቲያን ካልሆኑ ምንጮች ድጋሚ ማዘጋጀት እንችላለን፡ ኢየሱስ፣ ክርስቶስ ተብሎ ይጠራ ነበር (ጆሴፈስ)፣ “ምትሃት” ይሠራ ነበር፣ እስራኤልንም ወደ አዲስ ትምህርት መርቶታል፣ እናም ለእነሱ በፋሲካ ተሰቅሏል (የባቢሎናዊ ታልሙድ) በይሁዳ (ታሲተስ)፣ ነገር ግን አምላክ እንደሆነ የሚያስረዳ፣ እናም ዳግም የሚመጣ (ኤሌዛር)፣ እሱም ተከታዮቹ የሚያምኑት፣ የሚያመልኩት እንደ እግዚአብሔር (ፕሊኒ ወጣቱ)።

ለኢየሱስ ክርስቶስ ሕላዌ የሚያስተማምን ማስረጃ አለ፣ በሁለቱም ሃይማኖታዊ ባልሆኑትም ሆነ በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪክ። ምናልባትም ለኢየሱስ ሕያው መሆን ታላቁ ማስረጃ ሊሆን የሚችለው፣ በጥሬው በሺህ የሚቆጠሩ በአንደኛው ክፍለ ዘመን ዓ.ም የነበሩ ክርስቲያኖች፣ አስራ ሁለቱን ሐዋርያት ጨምሮ ለኢየሱስ ክርስቶስ በመሥዋዕትነት ሕይወታቸውን ለመስጠት ፍቃደኛ መሆናቸው ነው። ሰዎች የሚሞቱት እውነት እንደሆነ ላመኑበት ነው፣ ነገር ግን ማንም ቢሆን ውሸት መሆኑን ላወቀው ጉዳይ አይሞትም።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ በርግጥ ነበረን? ስለ ኢየሱስ ክርስቶስ መኖር አንዳች ዓይነት ታሪካዊ ማስረጃ አለውን?
© Copyright Got Questions Ministries