settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ከእግዚሐብሔር ጋር እንዴት እስማማለሁ?

መልስ፤


ከእግዚሐብሔር ጋር “ለመስማማት” በመጀመሪያ “ስህተት” ምን መሆኑን መረዳት ይኖርብናል። መልሱ ኃጢያት ነው። “በጎ ነገርን የሚሰራ የለም፣ አንድም ስንኳ የለም” (መዝሙር 14፡ 3) ። በእግዚሐብሔር ህጎች ላይ አምፀናል። እኛ ሁላችን እንደበጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን” (ኢሳያስ 53፡ 6)

መጥፎው ዜና ደግሞ የኃጢያት ቅጣት ሞት መሆኑ ነው። “ኃጢያት የምትሰራ ነፍስ እርስዋ ትሞታለች” (ሕዝቅኤል 18፡ 4) ። መልካሙ ዜና ደግሞ አፍቃሪ የሆነው እግዚሐብሔር ድነትን ለኛ ለማስገኘት ፈፅሞ አልተወንም። ኢየሱስ እንደተናገረው ዓላማው “የጠፉትን ፈልጎ ማግኘትና ማዳን” ነበር። (ሉቃስ 19፡ 10) በመስቀል ተሰቅሎ እንደሞተ ዓላማው መከናወኑን ለማብሰር “እነሆ ተፈፀመ” የሚለውን ቃል ተናገረ። (ዮሐንስ 19፡ 30) ።

ከእግዚሐብሔር ጋር የሚስማማ ግንኙነት ለመጀመር ኃጢያትህን ማወቅ ይጠይቃል። ከዚህ ቀጥሎ ለእግዚሐብሔር ኃጢያትህን በትህትና መናዘዝ ያስፈልጋል። (ኢሳያስ 57፡ 15) ። ከዚያም ኃጢያትን ላለመፈፀም ቁርጠኝነት ያስፈልጋል። “ሰው በልቡ አምኖ ይጸድቃልና በአፉም መስክሮ ይድናልና።” (ሮሜ 10፡ 10)

ይህ ንስሐ በእምነት መደገፍ አለበት። በተለይም ይህ እምነት የመስዋዕትነት ሞትና አስደናቂው ትንሳኤው ያንተ አዳኝ እንዲሆን ብቃት የሚሰጠው መሆኑን ማረጋገጥ አለበት። “… ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር፣ እግዚሐብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህ” (ሮሜ 10፡ 9) ። እንደ ዮሐንስ 20፡ 27፣ የሐዋሪያት ስራ 16፡ 31 ፣ ገላትያ 2፡ 16 ፣ 3፡ 11፣ 26 እና ኤፌሶን 2፡ 8 የመሳሰሉት ምዕራፎች ስለእምነት አስፈላጊነት ይናገራሉ።

ከእግዚሐብሔር ጋር መስማማት ማለት እግዚሐብሔር ባንተ ፋንታ ላከናወነው ተግባር የምትሰጠው አፀፋዊ ምላሽ ነው። እርሱ አዳኙን ላከው፣ የአንተን ኃጢያት ለማስወገድ አስፈላጊውን መስዋዕት አቀረበ። (ዮሐንስ 1፡ 29) ይህንን የተስፋ ቃልም ሰጠህ፣ “የጌታን ስም የሚጠራም ሁሉ ይድናል” (የሐዋሪያት ስራ 2፡ 21)።

ለንስሐና ይቅርታ ግሩም ገላጭ የሚሆነው ስለጠፋው ልጅ የተነገረው ምሳሌ ነው (ሉቃስ 15፡ 11-32)። ታናሹ ልጅ የአባቱን ስጦታ በአሳፋሪ ኃጢያት አባከነው (ቁጥር 13) ። ጥፋቱን በተረዳ ጊዜ ወደ ቤቱ ለመመለስ ወሰነ (ቁጥር 18)። እንደ ልጅ እንደማይቀበለው በልቡ አስቦ ነበር( ቁጥር 19) ነገር ግን ተሳስቷል። አባቱ የጠፋውን አመፀኛ ልጁን እንደ ድሮው እንደሚወደው አረጋገጠለት (ቁጥር 20)። ሁሉም ነገር ተረስቶ ፈንጠዝያው ቀጠለ (ቁጥር 24) ። እግዚሐብሔር የገባውን ቃል ለመፈፀም ይተጋል። ይህም ይቅርታ የማድረግን ተስፋ ያጠቃልላል። “እግዚሐብሔር ልባቸው ለተሰበረ ቅርብ ነው፣ መንፈሳቸው የተሰበረውንም ያድናቸዋል” (መዝሙር 34፡ 18)።

ከእግዚሐብሔር ጋር ለመስማማት ብትፈልግ ልትፀልየው የምትችል አንድ ፀሎት እናሳይህ። አስታውስ ይህንን ፀሎት ወይም ሌላ ፀሎት ማነብነብ አያድንህም። ከኃጢያት ሊያድንህ የሚችለው በክርስቶስ ብቻ መታመን ነው። እግዚሐብሔር ድነትን ስላስገኘልህ በእርሱ መታመንህን ለመግለጽና ምስጋናህን ለማቅረብ የምትጠቀምበት ፀሎት ነው። “እግዚሐብሔር ባንተ ላይ ኃጢያት እንደፈፀምኩ አውቃለሁ፤ ለዚህም ቅጣት ይገባኛል። ነገር ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ለኔ የሚገባውን ቅጣት ስለተቀበለልኝ በእርሱ በማመን ይቅርታ ተደርጎልኛል። ለድነቴ እምነቴን ባንተ ላይ እጥላለሁ። ስለአስደናቂው ፀጋህና ይቅርታህ እንዲሁም ስለ የዘላለም ሕይወት ስጦታህ አመሰግንሐለሁ! አሜን!

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ከእግዚሐብሔር ጋር እንዴት እስማማለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries