settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የሺህ ዓመት መንግሥት ምን ማለት ነው፣ እሱንስ በጥሬው መረዳት ይገባል?

መልስ፤


የሺሀ ዓመቱ መንግሥት ርዕስ የተሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ለሚገዛበት 1000 ዓመት ነው። አንዳንዶች 1000 ዓመትን በተምሳሌታዊ ዘይቤ ሊተረጉሙ ይሻሉ። አንዳንዶች 1000 ዓመቱን የሚረዱት ባመዛኙ ዘይቤአዊ አባባል ነው፣ “ረጅም የሆነ ጊዜ፣” በጥሬው ያልሆነ፣ በሥጋ ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ እንደሚገዛ ያለ። ሆኖም፣ ራዕይ 20፡2-7 ላይ፣ ስድስት ጊዜ የሺ ዓመቱ መንግሥት ተለይቶ 1000 ዓመት እንደሚሆን ተገልጿል። እግዚአብሔር “ረጅም የሆነ ጊዜ” የሚለውን ለማሳየት ቢፈልግ፣ በቀላሉ ሊያደርገው ይችል ነበር፣ ለይቶ እና ደጋግሞ ትክክለኛውን የጊዜ ቅንብብ ከመንገር ይልቅ።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚነግረን ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር ሲመለስ በኢየሩሳሌም እንደሚነግሥ ነው፣ በዳዊትም ዙፋን ላይ ይቀመጣል (ሉቃስ 1፡32-33)። ሁኔታዊ ያልሆኑት ኪዳናትም በጥሬው የሆነ፣ የክርስቶስ ሥጋዊ መመለስን ያሳያል፣ መንግሥቱን ለማቋቋም። አብርሃማዊው ኪዳን ለእስራኤል ምድርን ተስፋ ሰጥቷል፣ መጪውን ትውልድና ገዥነት፣ እና መንፈሳዊ ባርኮት (ዘፍጥረት 12፡1-3)። የፍልስጥኤም ኪዳን ለእስራኤል ተስፋ ሰጥቷል፣ ወደ ምድሩ መመለስና ምድሩን መሙላት (ዘዳግም 30፡1-10)። ዳዊታዊው ኪዳን ለእስራኤል ይቅርታን ተስፋ ሰጥቷል— ማለትም አሕዛብ የሚባረኩበት አግባብ (ኤርምያስ 31፡31-34)።

በዳግም ምጽአቱ፣ እነዚህ ኪዳናት ተፈጻሚ ይሆናሉ፣ እስራኤል ከሕዝቦች ሁሉ ሲሰባሰብ (ማቴዎስ 24፡31)፣ የተለወጡት (ዘካርያስ 12፡10-14)፣ እና ወደ አገራቸው ይመለሳሉ፣ በመሲሑ በኢየሱስ ክርስቶስ መሪነት። መጽሐፍ ቅዱስ የሚሊኒየሙ ጊዜ ሁኔታን ይገልጻል፣ ፍጹም የሆነ አካባቢ በሥጋዊና በመንፈሳዊ ረገድ እንደሚሆን። የሰላም ጊዜ ይሆናል (ሚኪያስ 4:2-4፤ ኢሳይያስ 32:17-18)፣ ደስታ (ኢሳይያስ 61:7፣ 10)፣ ምቹ (ኢሳይያስ 40:1-2)፣ ምንም ድህነትና ሕመም አይኖርም (አሞጽ 9:13-15፤ ኢዩኤል 2:28-29)። መጽሐፍ ቅዱስ ጨምሮ አማኞች ብቻ ወደ ሚሊኒየሙ መንግሥት እንደሚገቡ ይነግረናል። በዚህም ምክንያት፣ ፍጹም የጽድቅ ሰዓት ይሆናል (ማቴዎስ 25:37፤ መዝሙር 24:3-4)፣ ታዛዥነት (ኤርምያስ 31፡33)፣ ቅድስና (ኢሳይያስ 35፡8)፣ እውነት (ኢሳይያስ 65፡16)፣ እና የመንፈስ ቅዱስ ሙላት (ኢዩኤል 2፡28-29)። ክርስቶስ እንደ ንጉሥ ይገዛል (ኢሳይያስ 9:3-7፤ 11:1-10)፣ ከዳዊት ጋር እንደ ገዥ (ኤርምያስ 33:15-21፤ አሞጽ 9:11)። የከበሩና ገዥዎችም ደግሞ ይገዛሉ (ኢሳይያስ 32:1፤ ማቴዎስ 19:28)፣ ኢየሩሳሌምም የፖለቲካ ማዕከል ትሆናለች (ዘካርያስ 8:3)።

ራዕይ 20፡2-7 የሚሊኒየሙን መንግሥት ትክክለኛ ሰዓት ያሳያል። ከእነዚህ ቃሎች ውጭም፣ በርካታ ሌሎች የመሲሑን በምድር ላይ መንገሥ የሚያመለክቱ በጥሬው የተቀመጡ አሉ። አብዛኞቹ የእግዚአብሔር ኪዳናትና ተስፋ ፍጻሜዎች በጥሬው፣ በአካላዊ፣ በመጪው መንግሥት ላይ ያርፋል። የሚሊኒየሙን መንግሥት እና የሱም 1000 ዓመት ጊዜ መሆን የሚለውን ጥሬ ትርጉም ላለመቀበል የሚያስችል ምንም ዓይነት ተጨባጭ መሠረት የለም።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የሺህ ዓመት መንግሥት ምን ማለት ነው፣ እሱንስ በጥሬው መረዳት ይገባል?
© Copyright Got Questions Ministries