settings icon
share icon
ጥያቄ፤

አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ምንድናቸው?

መልስ፤


ብዙ ሰዎች የተሳሳተ መረዳት አላቸው፣ መንግሥተ ሰማይ በርግጥ ምን እንደሚመስል። ራዕይ ምዕራፍ 21-22 ስለ አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ዝርዝር ስዕል ይሰጠናል። ከፍጻሜ ዘመን ሁነቶች በኋላ፣ የአሁኖቹ ሰማይና ምድር ያልፋሉ፣ ብሎም በአዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ይተካሉ። የአማኞች ዘላለማዊ መኖርያ ስፍራ አዲስ ምድር ይሆናል። አዲሱ ምድርም “መንግሥተ ሰማይ” ይሆናል፣ እሱም ዘላለማዊነትን የምናሳልፍበት። አዲሱ ምድር ላይ ነው፣ አዲሲቷ ኢየሩሳሌም፣ ሰማያዊቷ ከተማ፣ የምትደረገው። በአዲሲቷ ምድር ላይ ነው፣ የዕንቍ በሮች እና የወርቅ አደባባዮች የሚሆኑት።

ሰማይ— አዲስ ምድር— አካላዊ ስፍራ ነው፣ ከከበሩ ሥጋዊ አካላት ጋር አብረን የምንኖርበት (1 ቆሮንቶስ 15፡35-58)። መንግሥተ-ሰማይ “በደመናት ውስጥ ነው” የሚለው ጽንሰ-ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። እኛም “መናፍስት ሆነን በሰማይ ላይ እንንሳፈፋለን” የሚለውም ጽንሰ-ሐሳብ መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። አማኞች የሚለማመዱት መንግሥተ ሰማይ አዲስና ፍጹም የሆነ ፕላኔት ነው፣ እዚያም እኛ የምንኖርበት። አዲሱ ምድር ከኃጢአት፣ ከክፉ፣ ከሕመም፣ ከመከራና ሞት ነጻ ይሆናል። እሱም ከአሁኑ ምድራችን ጋር ተመሳሳይ ሊሆን ይችላል፣ ወይም ምናልባት የአሁኑ ዓለማችን አዲስ ፍጥረት፣ ነገር ግን የኃጢአት ርግማን የሌለበት።

ስለ አዲሱ ሰማይስ? ማስታወስ የሚገባው ጠቃሚ ነገር፣ በጥንቶቹ አስተሳሰብ፣ “ሰማያት” የሚያመለክቱት ሰማይንና ከጠፈር በላይን ነው፣ አልፎ ተርፎም የእግዚአብሔር ማደሪያ ስፍራ። ስለዚህ፣ ራዕይ 21፡1 አዲስ ሰማይን ሲጠቅስ ሊያመለክት የሚሻው ሞላው ዩኒቨርስ መፈጠሩን ነው— አዲስ ምድር፣ አዲስ ሰማያት፣ አዲስ ውጫዊ ጠፈር። እሱም የሚመስለው የእግዚአብሔር ሰማይም ዳግም እንደሚፈጠር ነው፣ በዩኒቨርስ ላይ ላለው ነገር ሁሉ “አዲስ ጅማሮ” ለማድረግ፣ ሥጋዊም ሆነ መንፈሳዊ። እኛ ከአዲሶቹ ሰማያት ጋር ዘላለማዊ ቀረቤታ ይኖረናልን? ሊሆን ይችላል፣ ነገር ግን ለማግኘት መጠበቅ ይኖርብናል። ሁላችንም ለእግዚአብሔር ቃል መፍቀድ ይኖርብናል፣ ስለ መንግሥተ ሰማይ ያለንን መረዳት ለመቅረጽ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

አዲስ ሰማይና አዲስ ምድር ምንድናቸው?
© Copyright Got Questions Ministries