settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እራሴን የማላጠፋው ለምንድን ነው?

መልስ፤


ራስን በማጥፋት የገዛ ህይወታቸውን የማብቃት ሀሳቦች ላሏቸው ልቦቻችን ያዝናሉ፡፡ አሁን ያ አንተ ከሆንህ እንደ ተስፋ ቢስነት እና ተስፋ መቁረጥ ያሉ ብዙ ስሜቶች ይናገር ይሆናል፡፡ በጣም ጥልቅ ጉድጓድ ውስጥ እንዳለህ ይሰማህ ይሆናል እና ለነገሮች መሻሻል ምንም ተስፋ እንዳሌለ ትጠራጠራለህ፡፡ ማንም ሰው ከየት እንየመጣህ እንዳለ ግድ ያለው ወይም የሚገነዘብ አይመስልም፡፡ በቃ ህይወት መኖር አይገባትም… ወይም ነው?

ልክ አሁን እግዚአብሔርን በእውነት በህይወትህ እግዚአብሔር እንዲሆን የመፍቀዱን ነገር እንድታስብበት ጥቂት ጊዜያቶችን ብትወስድ በእውነት እርሱ ምን ያህል ትልቅ እንደሆነ ያረጋግጣል፤ “ለእግዚአብሔር የሚሳነው ነገር የለምና።” (የሉቃስ ወንጌል 1፤37) ምናልባት ካለፉት ጉዳቶች ጠባሳዎች የብዙ የመነቀፍ እና መጣል ስሜት ምክንያት ሆኗል፡፡ ያ ምናልባት ወደ ባዶነት፤ ንዴት፤መራርነት በቂም በቀል የተሞሉ አስተሳሰቦች ይመራህ ይሆናል ወይም በተወሰኑ በአንተ በጣም ጠቃሚ ግንኙነቶችህ ውስጥ ችግሮችን ያመጡ ጤናማ ያልሆኑ ፍርሃቶች ሊሆኑ ይችላሉ፡፡

ለምን አንተ ራስህን አታጠፋም? ወዳጄ ምንም ያህል መጥፎ ነገሮች በህይወትህ ቢኖሩም በተስፋ መቁረጥ ዋሻ ውስጥ ሊመራህ እና ወደ እሱ ወደሚደነቅ ብርሃን ሊያወጣህ አንተን በመጠበቅ ላይ ያለ የፍቅር አምላክ አለ፡፡ እሱ የሚታመን ተስፋህ ነው፡፡ ስሙም ኢየሱስ ነው፡፡

ይህ ኢየሱስ ፤ኃጥአት የሌለበት የእግዚአብሔር ልጅ፤በአንተ የመገፋት እና የመዋረድ ጊዜ ጋር ይዛመዳል፡፡ ነቢዩ ኢሳያስ በትንቢተ ኢሳያስ 53፤2-6 በእያንዳንዱ ሰው “እንደ ተናቀ እና እንደ ተገፋ” ሰው እየገለጠ ስለ እሱ ጽፏል፡፡ ህይወቱ በሀዘን እና በስቃይ የተሞላ ነበር፡፡ ነገር ግን ተሸክሞት የነበረው ሀዘን የራሱ አልነበረም፤የእኛ ነበሩ፡፡ በኃጥአታችን ምክንያት ሁሉንም ተወግቷል፤ቆስሏል፤ እና ተጨፍልቋልም፡፡ በእሱ ሥቃይ ምክንያት ህይወታችን ነጻ ሊወጣ ይችላል እና ሙሉም ይሆናል፡፡

ወዳጄ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁሉም ኃጥአቶችህ ይቅር ይባሉ ዘንድ ይህን ሁሉ ችሏል፡፡ ምንም ያህል ክብደት ያለው በደል ብትሸከም እሱን በትህትና እንደ አዳኝህ ብትቀበለው ይቅር እንደሚልህ ያን እወቅ፡፡ “በመከራ ቀን ጥራኝ፥ አድንህማለሁ…።” (መዝሙረ ዳዊት 50፤15) ለኢየሱስ ይቅር ለማለት እስካሁን የሠራኸው የትኛውም በጣም መጥፎ ነገር ምንም ነገር የለም፡፡ የተወሰኑቱ ምርጦቹ ባሪያዎች እንደ ነፍሰ ገዳይነት (ሙሴ)፤ ነፍስ ገዳይነት እና ማመንዘር (ንጉሥ ዳዊት) እና አካላዊ እና ስሜታዊ ስድብ (ሐዋሪያው ጳውሎስ) የመሳሰሉትን ጸያፍ ኃጥአቶችን ፈጽመዋል፡፡ ነገር ግን በጌታ ይቅርታዎችን እና የበዛ አዲስ ህይወትን አገኙ፡፡ “ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፥ ሁሉም አዲስ ሆኖአል።” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፤17)

ራስህን የማታጠፋው ለምንድነው? ወዳጄ፤ እግዚአብሔር “የተሰበረውን” ነገር ፤እሱም አሁን ያለህን ህይወት፤ራስህን በመግደል ፍጻሜ ልታበጅለት የምትፈልገው ህይወትህን ለመጠገን ተዘጋጅቶ አለ፡፡ በትንቢተ ኢሳያስ 61፤1-3 ውስጥ ነብዩ ጽፏል፤ “የጌታ የእግዚአብሔር መንፈስ በእኔ ላይ ነው፥ ለድሆች የምሥራችን እሰብክ ዘንድ እግዚአብሔር ቀብቶኛልና ልባቸው የተሰበረውን እጠግን ዘንድ፥ ለተማረኩትም ነጻነትን ለታሰሩትም መፈታትን እናገር ዘንድ ልኮኛል። የተወደደችውን የእግዚአብሔርን ዓመት አምላካችንም የሚበቀልበትን ቀን እናገር ዘንድ፥ የሚያለቅሱትንም ሁሉ አጽናና ዘንድ፤ እግዚአብሔር ለክብሩ የተከላቸው የጽድቅ ዛፎች እንዲባሉ ለጽዮን አልቃሾች አደርግላቸው ዘንድ፥ በአመድ ፋንታ አክሊልን፥ በልቅሶም ፋንታ የደስታን ዘይት፥ በኀዘንም መንፈስ ፋንታ የምስጋናን መጐናጸፊያ እሰጣቸው ዘንድ ልኮኛል።”

ወደ ኢየሱስ ና እናም በህይወትህ አዲስ ሥራ እንዲጀምር እንዳመንከው ሀሴትህን እና ጠቃሚነትህን እንዲመልስልህ ፍቀድለት፡፡ ያጣኸውን ሀሴት ሊመልስልህ ተስፋን ይሰጣል እና ሊደግፍህም አዲስ መንፈስ ይሰጥሃል፡፡ የአንተ የተሰበረ ልብ ለእሱ ውድ ነው፤”የእግዚአብሔር መሥዋዕት የተሰበረ መንፈስ ነው፥ ኦ እግዚአብሔር የተሰበረውንና የተዋረደውን ልብ አትንቅም።”

ጌታን እንደ አዳኝህ እና እረኛህ ትቀበለዋለህ? እሱ አንድ ቀን በአንድ ጊዜ በቃሉ ፤በመጽሐፍ ቅዱስ፤አማካይነት አስተሳሰብህን እና እርምጃህን ይመራል፤ “አስተምርሃለሁ በምትሄድበትም መንገድ እመራሃለሁ ዓይኖቼን በአንተ ላይ አጠናለሁ።” (መዝሙረ ዳዊት 32፤8) “የዘመንህም ጸጥታ፥ የመድኃኒት ብዛት፥ ጥበብና እውቀት ይሆናል እግዚአብሔርን መፍራት መዝገቡ ነው።” በክርስቶስ እስካሁን ትግሎች አሉብህ ነገር ግን አሁን ተስፋ ይኖርሃል፡፡ እሱ “ከወንድም አብልጦ የሚጠጋጋ ነው።” (መጽሐፈ ምሳሌ 18፤24) በውሳኔዎችህ ሰዓት የጌታ የኢየሱስ ጸጋ ከአንተ ጋር ይሁን፡፡

ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኝህ ማመን ብትፈልግ በልብህ ውስጥ ለእግዚአብሔር እነዚህን ቃላቶች ተናገር፤ “እግዚአብሔር በህይወቴ ውስጥ እፈልግሃለሁ፡፡ እባክህ ላደረግሁት ለእነዚያ ሁሉ ይቅር በለኝ፡፡ እምነቴን በክርስቶስ ኢየሱስ አደርጋለሁ እናም አዳኜም እንደሆነ አምናለሁ፡፡ እባክህ እጠበኝ፤አድነኝ፤ እና በሕይወቴ ሀሴቴን መልስልኝ፡፡ ለእኔ ስላለህ ፍቅርህ እናም በኢየሱስ በእኔ ፈንታ መሞት አመሰግናለሁ፡፡”

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እራሴን የማላጠፋው ለምንድን ነው?
© Copyright Got Questions Ministries