settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ የግል አዳኝህ መቀበል ምን ማለት ነው?

መልስ፤


ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ የግል አዳኝህ ተቀብለኸው ታውቃለህ? መልስ ከመሥጠትህ በፊት ጥያቄውን እንዳብራራ ይፈቀድልኝ። ጥያቄውን በበለጠ እንዲገባን፣ በመጀመሪያ “ኢየሱስ ክርስቶስ፣” “የግል” እና “አዳኝ” የሚሉትን ቃላት በደንብ መረዳት አለብን።

ኢየሱስ ማን ነው? ብዙዎች ኢየሱስ ጥሩ ሰው፣ ታላቅ መምህር ብሎም ነብይ እንደነበር ያምናሉ። እነዚህ ነገሮች ምንም እንኳን እውነት ቢሆኑም፣ የኢየሱስ ማንነት ለመግለጽ ግን በቂ አይደሉም። መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ስጋ የለበሰ አምላክ መሆኑን ይነግረናል፤ አምላክ ሰው ሆነ (ዮሐንስ ፩፥፩፣ ፲፬ ተመልከት)። አምላክ ወደ ምድር የመጣው ሊያስተምረን፣ ሊያርመን፣ ይቅር ሊለን - እንዲሁም ሊሞትልን! ኢየሱስ ክርስቶስ አምላክ ነው፣ ፈጣሪ፣ ፍፁም ኀይል ያለው ጌታ። ይህንን ኢየሱስ ተቀብለኸዋል?

አዳኝ ማለት ምን ድነው? ለምነስ ያሰፈልገናል? መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ሁላችንም ኀጢአት ሠርተናል፤ ሁላችንም እርኩስ ሥራ ፈጽመናል (ሮሜ ፫፥፲-፲፰)። ለዚህ ኀጢአታችንም የእግዚአብሔር ቁጣና ፍርድ ይገባናል። ዘለዓለማዊ በሆነ አምላክ ላይ ኀጢአት ስለሠራንም ዘለዓለማዊ የሆነ ቅጣት ይገባናል (ሮሜ ፮፥፳፫፤ ራእይ ፳፥፲፩-፲፭)። ለዚህም ነው አዳኝ ያስፈለገን!

ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ምድር መጥቶ በምትካችን ሞተልን። ሥጋ የለበሰ አምላክ እንደመሆኑ መጠን፣ የክርስቶስ ሞት ለኀጢአታችን የተደረገ መጨረሻ የሌለው ክፍያ ነው። ኢየሱስ የሞተው የኀጢአታችንን ቅጣት ለመቀበል ነው (ሮሜ ፭፥፰)። እኛን ከክፍያ ለማዳን፣ ኢየሱስ ዋጋውን ከፈለልን። የኢየሱስ ከሙታን መነሳት፣ ሞቱ ለኀጢአታችን ዋጋ በቂ መሆኑን አረጋግጦልናል። ለዚህም ነው ኢየሱስ አንድና ብቸኛ አዳኝ የሆነው (ዮሐንስ ፲፬፥፮፤ የሐዋርያት ሥራ ፬፥፲፪)! ኢየሱስ አዳኝህ እንደሆነ እያመንክ ነው?

ኢየሱስ “የግል” አዳኝህ ነው? ብዙ ሰዎች ክርስትና ማለት ወደ ቤተ ክርስትያን መመላለስ፣ ሥርዓተ ቅዳሴ መካፈልና አንዳድ ኀጢአቶችን አለመፈጸም ይመስላቸዋል። ይህ ግን ክርስትና አይደለም። እውነተኛ ክርስትና ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ግላዊ የሆነ ግንኙነት ሲኖረን ብቻ ነው። ኢየሱስ እንደ የግል አዳኝህ መቀበል ማለት እምነትህን በእርሱ ላይ ማኖር ነው። በሌላ ሰዎች እምነት ማንም ሊድን አይችልም። አንዳድ ጥሩ ሥራዎች በመሥራት ብቻ ኀጢአታችን ይቅር አይባልልንም። የድነት ብቸኛ መንገድ የኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝነት መቀበል ነው፤ ይህን ስናደርግም ሞቱ ለኀጢአታችን የተከፈለ ዋጋ መሆኑንና ከሙታን መነሳቱም ለዘለዓለማዊ ሕይወት እንደሚያስተማምነን እናምናለን ማለት ነው (ዮሐንስ ፫፥፲፮)። ኢየሱስ የግል አዳኝህ ነው?

ኢየሱስ ክርስቶስ እንደ የግል አዳኝህ ለመቀበል ዝግጁ ከሆንክ የሚከተሉትን ቃላት ለእግዚአብሔር ንገረው። አስታውስ፣ ይህንንም ሆነ ሌላ ጸሎት መድገም ብቻ በራሱ አያድንህም። በክርስቶስ ማመን ብቻ ነው ለያድንህ የሚችለው። ይህ ጸሎት የሚረዳህ በእግዚአብሔር ያለህን እምነት ለመግለጽና ለድነቱ ምስጋና ለማቅረብ ነው። “እግዚአብሔር ሆይ፤ ባነተ ላይ መበደሌና ለዚህም ኀጢአቴ ቅጣት እንደሚገባኝ አውቃለሁ። ቢሆንም ግን ኢየሱስ ክርስቶስ ቅጣቴን ተቀብሎልኛል፤ እርሱን በማመን ኀጢአቴ ይስተሰርይልኝ ዘንድ። ከኀጢአቴ ፈቀቅ በማለት እምነቴ በድነትህ አኖራለሁ። ኢየሱስን እንደግል አዳኜ ተቀብየዋለሁ! ወደር ለሌለው ጸጋህና ይቅር ባይነትህ አመሰግናሃለሁ፤ እንዲሁም የዘለዓለም ሕይወት ለሆነው ስጦታህ! አሜን!”

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ የግል አዳኝህ መቀበል ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries