settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የቤት እንስሳት ወደ መንግሥተ-ሰማያት ይሄዳሉን? የቤት እንስሳት ነፍስ አላቸውን?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ የቤት እንስሳት ነፍስ እንዳላቸው ወይም የቤት እንስሳት በመንግሥተ-ሰማያት እንደሚሆኑ ምንም ዓይነት ግልጽ የሆነ ትምህርት አይሰጥም፡፡ ሆኖም ግን በጉዳዩ ላይ የተወሰነ ገለጻ ለማዳበር አጠቃላይ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መርሆዎችን መጠቀም እንችላለን፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ሁለቱም ሰው (ኦሪት ዘፍጥረት 2፤7) እና እንስሳት (ኦሪት ዘፍጥረት 1፤30፤6፤17፤7፤15፤22) የህይወት እስትንፋስ እንዳላቸው ያን ይጠቅሳል፡፡ በሰው ልጆች እና በእንስሳቶች መሐከል ያለው ዋና ልዩነት የሰው ልጅነት በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳያ ተፈጥሯል (ኦሪት ዘፍጥረት 1፤26-27) እንስሳቶች ግን አይደሉም፡፡ በእግዚአብሔር መልክ እና አምሳያ መፈጠር ማለት የሰው ልጆች እንደ እግዚአብሔር ናቸው፤ለመንፈሳዊነት የበቁ፤በአዕምሮ፤በስሜት እና ፈቃድ እና ከሞት በኃላ የሚቀጥል የማንነታቸው ክፍል አላቸው፡፡ የቤት እንስሳት “ነፍስ”ወይም አስፈላጊ ያልሆነ ክፍል ካላቸው ስለዚህ የግድ የተለየ እና የወረደ ጥራት ሊሆን ይገባል፡፡ ይህ ልዩነት ምናልባት የቤት እንስሳት ከሞት በኃላ በመኖራቸው አይቀጥሉም ማለት ነው፡፡

ልናስበው የሚገባን ሌላው ጉዳይ በዘፍጥረት ውስጥ እንስሳት የእግዚአብሔር የመፍጠሩ ሂደት ክፍል ናቸው፡፡ እግዚአብሔር እንስሳትን ፈጠራቸው እና መልካም ናቸውም አለ (ኦሪት ዘፍጥረት 1፤25)፡፡ ስለዚህ እንስሳት በአዲሱ ምድር ለምን ሊኖሩ እንደማይችሉ ምንም ምክንያት የለም (የዮሐንስ ራዕይ 21፤1)፡፡ በጣም በእርግጠኝነት በሺሁ ዓመት መንግሥት ወቅት እንስሳት ይኖራሉ (ትንቢተ ኢሳያስ 11፤6፤65፤25)፡፡ የተወሰኑቱ እነዚህ እንስሳቶች ምናልባት በዚህ በምድር እያለን የነበሩን የቤት እንስሳቶች እንደሆኑ በእርግጠኝነት መናገር አይቻልም፡፡ እግዚአብሔር ጻድቅ እንደሆነ እናውቃለን እናም ወደ መንግሥተ-ሰማይ በምንገባበት ጊዜ በዚህ ጉዳይ ላይ ምንም ዓይነት ነገር እንኳን ቢሆን ከእርሱ ውሳኔ ጋር በፍጹም መስማማት ውስጥ ራሳችንን እናገኛለን፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የቤት እንስሳት ወደ መንግሥተ-ሰማያት ይሄዳሉን? የቤት እንስሳት ነፍስ አላቸውን?
© Copyright Got Questions Ministries