settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ጸሎቴ በእግዚአብሔር እንዲመለስ እንዴት እችላለሁ?

መልስ፤


ብዙ ሰዎች የሚያምኑት የተመለሰ ጸሎት፣ እግዚአብሔር የተቀበለው የጸሎት ጥያቄ፣ ለእሱ የቀረበውን ነው። የጸሎት ጥያቄ ተቀባይነት ከሌለው፣ “መልስ ያላገኘ” ጸሎት መሆኑ ይታወቃል። ሆኖም፣ ይህ ይህ የተሳሳተ የጸሎት መረዳት ነው። እግዚአብሔር ወደ እሱ የቀረበውን እያንዳንዱን ጥያቄ ይመልሳል። አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር “የለም” ወይም “ጠብቅ” በማለት ይመልሳል። እግዚአብሔር ጸሎታችንን የሚቀበለው እንደ ፍቃዱ ስንጠይቅ ብቻ ነው። “በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል። የምንለምነውንም ሁሉ እንዲሰማልን ብናውቅ ከእርሱ የለመነውን ልመና እንደ ተቀበልን እናውቃለን” (1 ዮሐንስ 5፡14-15)።

እንደ እግዚአብሐር ፍቃድ መለመን ምን ማለት ነው? እንደ እግዚአብሔር ፍቃድ መጸለይ ማለት እግዚአብሔርን ስለሚያከብሩ እና ከፍ ስለሚያደርጉ ነገሮች እና/ወይም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚያሳየው የእግዚአብሔር ፍቃድ ለሆኑ ነገሮች መጸለይ ማለት ነው። እግዚአብሔርን ስለማያስከብር ወይም እግዚአብሔር በሕይወታችን እንዲሆን ስለማይፈቅደው ስለ አንድ ነገር ከጸለይን፣ እግዚአብሔር የለምንነውን አይሰጠንም። የእግዚአብሔር ፍቃድ ምን እንደሆን እንዴት እናውቃለን? እግዚአብሔር ተስፋ ሰጥቶናል፣ ከለመንነው ጥበብን እንደሚሰጠን። ያዕቆብ 1፡5 ያውጃል፣ “ከእናንተ ግን ማንም ጥበብ ቢጎድለው፥ ሳይነቅፍ በልግስና ለሁሉ የሚሰጠውን እግዚአብሔርን ይለምን፥ ለእርሱም ይሰጠዋል።” ለመጀመር የተሻለው ስፍራ 1 ተሰሎንቄ 5፡12-24 ነው፣ እሱም ብዙ ነገሮችን የሚዘረዝር፣ ለእኛ የእግዚአብሔር ፍቃድ የሆኑትን። የእግዚአብሔርን ቃል በተሻለ ከተረዳን፣ ስለ ምን እንደምንጸልይ በተሻለ እናውቃለን (ዮሐንስ 15፡7)። ስለ ምን እንደምንጸልይ በተሻለ በተረዳን ቁጥር፣ እግዚአብሔር ለጥያቄያችን አዘውትሮ “አዎን” የሚል ምላሽ ይሰጠናል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ጸሎቴ በእግዚአብሔር እንዲመለስ እንዴት እችላለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries