settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መቼ /እንዴት መንፈስ ቅዱስን እንቀበላለን?

መልስ፤


ሐዋርያው ጳውሎስ በግልጽ እንደሚያስተምረው መንፈስ ቅዱስን የምንቀበለው ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛችን ስንቀበል ነው። አንደኛ ቆሮንቶስ 12፡13 እንዲህ ያውጃል፣ “አይሁድ ብንሆን የግሪክ ሰዎችም ብንሆን ባሪያዎችም ብንሆን ጨዋዎችም ብንሆን እኛ ሁላችን በአንድ መንፈስ አንድ አካል እንድንሆን ተጠምቀናልና። ሁላችንም አንዱን መንፈስ ጠጥተናል።” ሮሜ 8፡9 የሚነግረን፣ ሰው መንፈስ ቅዱስ ከሌለው በቀር እሱ ወይም እሷ የክርስቶስ አለመሆናቸውን ነው፡ “እናንተ ግን የእግዚአብሔር መንፈስ በእናንተ ዘንድ ቢኖር፥ በመንፈስ እንጂ በሥጋ አይደላችሁም። የክርስቶስ መንፈስ የሌለው ከሆነ ግን ይኸው የእርሱ ወገን አይደለም።” ኤፌሶን 1፡13-14 የሚያስተምረን መንፈስ ቅዱስ ለሚያምኑት ሁሉ የመዳን ማኅተም መሆኑን ነው፡ “እናንተም ደግሞ የእውነትን ቃል፥ ይኸውም የመዳናችሁን ወንጌል፥ ሰምታችሁ ደግሞም በክርስቶስ አምናችሁ፥ በተስፋው መንፈስ በመንፈስ ቅዱስ ታተማችሁ፤ እርሱም የርስታችን መያዣ ነው፥ ለእግዚአብሔር ያለውን ሁሉ እስኪዋጅ ድረስ፥ ይህም ለክብሩ ምስጋና ይሆናል።”

እነዚህ ሦስት አንቀጾች፣ መንፈስ ቅዱስን የምንቀበለው በመዳናችን ቅጽበት መሆኑን ግልጽ ያደርጋሉ። ጳውሎስ፣ ሁላችንም በአንድ መንፈስ ተጠምቀናል፣ እንዲሁም ሁላችንም አንዱን መንፈስ እንድንጠጣ ተሰጥቶናል፣ ማለት አይችልም ነበር፤ እንደዚያ ባይሆን ኖሮ ሁሉም የቆሮንቶስ አማኞች መንፈስ ቅዱስ ባደረባቸው ነበር። ሮሜ 8፡9 ጭራሹን ጠንከር ያለ ነው፣ አንድ ሰው መንፈሱ ከሌለው፣ እሱ የክርስቶስ አለመሆኑን በማስቀመጥ። ስለዚህ፣ የመንፈስ ቅዱስ ማደር፣ መዳንን እንደያዝን ዋነኛ መገለጫ ነው። ከዚህም በላይ፣ መንፈስ ቅዱስ “የመዳን ማኅተም” ሊሆን አይችልም፣ (ኤፌሶን 1፡13-14) እሱን በመዳን ቅጽበት እስካልተቀበልነው ድረስ። ብዙ ጽሑፎች በምላት ግልጽ አድርገውታል፤ እሱም፣ መዳናችን የሚረጋገጠው ክርስቶስን እንደ አዳኝ አድርገን በተቀበልንበት ቅጽበት ነው።

ይህ ውይይት አወዛጋቢ ነው፣ ምክንያቱም የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎቶች ዘወትር ግር የሚያሰኙ በመሆናቸው ነው። መንፈስ ቅዱስን መቀበል/ማደሪያ መሆን የሚከናወነው በደኅንነት ቅጽበት ነው። በክርስትና ሕይወት መንፈስ ቅዱስን መሞላት ቀጣይነት ያለው ሂደት ነው። እኛ የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት የሚከናወነው በደኅንነት ጊዜ ነው እንላለን፣ አንዳንድ ክርስቲያኖች ግን አይሉም። ይህም አንዳንዴ የሚፈጠርበት ምክንያት የመንፈስ ቅዱስ ጥምቀት፣ ከ“መንፈስ ቅዱስን መቀበል” ጋር ግርታ ስለሚፈጥር ነው፣ ከደኅንነት ጋር የተያያዘ ድርጊት በመምሰል።

ሲጠቃለልም፣ መንፈስ ቅዱስን እንዴት እንቀበላለን? መንፈስ ቅዱስን የምንቀበለው ባጭሩ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደ አዳኛችን አድርገን በመቀበል ነው (ዮሐንስ 3፡5-16)። መንፈስ ቅዱስን መቼ እንቀበላለን? መንፈስ ቅዱስ ቋሚ ሀብታችን የሚሆነው ባመንንበት ቅጽበት ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መቼ /እንዴት መንፈስ ቅዱስን እንቀበላለን?
© Copyright Got Questions Ministries