settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የፍጻሜው ዘመን ምልክቶች ምንድን ናቸው?

መልስ፤


ማቴዎስ 24፡5-8 የፍጻሜ ዘመን መድረሱን የሚያመለክት ጠቃሚ ፍንጮች ይሰጠናል፣ “ብዙዎች፣ እኔ ክርስቶስ ነኝ እያሉ በስሜ ይመጣሉና፤ ብዙዎችንም ያስታሉ። ጦርንም የጦርንም ወሬ ትሰሙ ዘንድ አላችሁ፤ ይህ ሊሆን ግድ ነውና ተጠበቁ፥ አትደንግጡ፤ ዳሩ ግን መጨረሻው ገና ነው። ሕዝብ በሕዝብ ላይ መንግሥትም በመንግሥት ላይ ይነሣልና፥ ራብም ቸነፈርም የምድርም መናወጥ በልዩ ልዩ ስፍራ ይሆናል።” የሐሰተኛ ነቢያት እየጨመረ መምጣት፣ የጦርነት እየጨመረ መምጣት፣ እና የራብ እየጨመረ መምጣት፣ መቅሠፍት እና የተፈጥሮ አደጋዎች— እነዚህ የፍጻሜው ዘመን ምልክቶች ናቸው። በዚሀ ምንባብ ማስጠንቀቂያ ይሰጠናል፡ እንዳንስት፣ ምክንያቱም እነዚህ ምልክቶች የምጥ ጣር መጀመሪያ ናቸውና፤ ፍጻሜው ገና ይመጣል።

አንዳንድ ተርጓሚዎች እንደሚጠቁሙት እያንዳንዱ የመሬት መንቀጥቀጥ፣ እያንዳንዱ የፖለቲካ አለመረጋጋት፣ እና እስራኤል ላይ የሚደርሰው እያንዳንዱ ጥቃት በፍጻሜው ዘመን በፍጥነት እየደረሰ መሆኑን ርግጠኛ ምልክቶች ናቸው። የፍጻሜው ዘመን መድረሱን ሁነቶቹ ሲያመላክቱ፣ እነሱ የፍጻሜው ዘመን ደርሷል በሚል ጠቋሚ ላይሆኑ ይችላሉ። ሐዋርያው ጳውሎስ እንደሚያስጠነቅቀው በፍጻሜዎቹ ቀናት የሐሰት ትምህርት እየጨመረ ይመጣል። “መንፈስ ግን በግልጥ፣ በኋለኞች ዘመናት አንዳንዶች የሚያስቱ መናፍስትንና በውሸተኞች ግብዝነት የተሰጠውን የአጋንንትን ትምህርት እያደመጡ፥ ሃይማኖትን ይክዳሉ ይላል” (1 ጢሞቴዎስ 4፡1)። የፍጻሜ ቀናት “የጭንቅ ሰዓት” በመባል ይታወቃሉ፣ ከሰዎች ክፋት እየጨመረ መምጣትና ሰዎች “እውነትን በመቃወማቸው” ምክንያት (2 ጢሞቴዎስ 3፡1-9፤ ደግሞም 2 ተሰሎንቄ 2፡3 ተመልከት)።

ሌለኛው ታሳቢ ምልክት የሚያካትተው የአይሁድ ቤተ-መቅደስ በኢየሩሳሌም ዳግም መገንባት ሲሆን፣ እሱም በእስራኤል ላይ ጠላትነትን ይጨምራል፣ የአንድ የዓለም መንግሥት መቋቋም ተከትሎት። ሆኖም፣ እጅግ ዋነኛው የፍጻሜ ዘመን ምልክት የእስራኤል መንግሥት ነው። በ1948 እስራኤል እንደ ሉዓላዊ መንግሥት እውቅና አገኘች፣ በዋነኝነትም ከ70 ዓ.ም ወዲህ ለመጀመሪያ ጊዜ። እግዚአብሔር ለአብርሃም ቃል እንደገባለት፣ የእሱ ዝርዮች ከነአንን እንደ “ዘላለማዊ ርስት” እንደሚወርሱ (ዘፍጥረት 17፡8)፣ ሕዝቅኤልም ስለ እስራኤል ሥጋዊና መንፈሳዊ ተሐድሶ ተንብዮአል (ሕዝቅኤል ምዕራፍ 37)። እስራኤል በገዛ ምድሩ ላይ መንግሥት መመሥረቱ በፍጻሜ ዘመን ትንቢት አኳያ ዋነኛ ነገር ነው፣ ከእስራኤል የፍጻሜ ዘመን ሁኔታ ጋር ከመያያዙ የተነሣ (ዳንኤል 10፡14፤ 11፡41፤ ራዕይ 11፡8)።

እነዚህን ምልክቶች ግምት ውስጥ በማስገባት፣ ብልህ እና አስተዋዮች መሆን እንችላለን፣ የፍጻሜ ዘመን ተስፋዎችን በተመለከተ። ሆኖም እነዚህን ተናጠላዊ ሁነቶች መተርጎም አይኖርብንም፣ የፍጻሜው ዘመን መድረሱን በግልጽ እንደሚያመላክቱ አድርገን። እግዚአብሔር በቂ መረጃ ሰጥቶናል፣ ለመዘጋጀት እንድንችል፣ የተጠራነውም እንደዛ እንድንሆን ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የፍጻሜው ዘመን ምልክቶች ምንድን ናቸው?
© Copyright Got Questions Ministries