settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የኃጢአት ፍቺ ምንድነው?

መልስ፤


ኃጠአት በመጽሐፍ ቅዱስ የተገለጸው የእግዚአብሔርን ሕግ እንደመተላለፍ ነው (1 ዮሐንስ 3፡4) እንዲሁም በእግዚአብሔር ላይ ማመጽ (ዘዳግም 9:7፤ ኢያሱ 1:18)፡፡ ኃጢአት የጀመረው በሉሲፈር ነው፣ ምናልባትም ከመላእክት እጅግ የተዋበውና ኃይለኛው። በሥልጣኑ ስላልረካ ከእግዚአብሔር በላይ ለመሆን ተመኘ፣ ያም ውድቀቱ ሆነ፣ የኃጢአት መጀመሪያ (ኢሳይያስ 14:12-15)፡፡ ሰይጣን ተብሎ ዳግም ተሰየመ፣ እሱም ኃጢአትን ወደ ሰው ልጆች አመጣ፣ በዔድን ገነት፣ እዚያም አዳምና ሔዋንን በተመሳሳይ ተንኮል ፈተናቸው፡ “እንደ እግዚአብሔር ትሆናላችሁ፡፡” ዘፍጥረት 3 የአዳምንና ሔዋንን በእግዚአብሔር እና በትዕዛዙ ላይ ማመጽን ይገልጻል። ከዛን ጊዜ ጀምሮ ኃጢአት በሰው ልጆች ትውልድ ሁሉ ላይ ተላለፈ፣ እኛም የአዳም ዝርያዎች ከእርሱ ኃጢአትን ወረስን። ሮሜ 5፡12 የሚነግረን በአዳም ምክንያት ኃጢአት ወደ ምድር መግባቱን ነው፣ ሞትም ወደ ሰዎች ሁሉ ተላለፈ፣ “የኃጢአት ዋጋው ሞት” በመሆኑ ምክንያት (ሮሜ 6፡23)።

በአዳም በኩል ወደ ኃጢአት የማዘንበል ውርስ ወደ ሰው ዘር ገባ፣ የሰው ልጆችም በተፈጥሯቸው ኃጢአተኞች ሆኑ። አዳም ኃጢአት ሲሠራ፣ የእርሱ ውስጣዊ ተፈጥሮ በዓመጻ ኃጢአቱ ምክንያት ተለወጠ፣ በእርሱም ላይ መንፈሳዊ ሞትና የሞራል ውድቀትን አመጣ፣ ይኽም ከእርሱ በኋላ በመጡት ላይ ሁላ የሚተላለፍ። እኛ ኃጢአተኛ የሆንነው ኃጢአት ስለሠራን አይደለም፤ ይልቁንም ኃጢአትን የምንሠራው ኃጢአተኞች ስለሆንን እንጂ ነው። ይህም የሚተላለፍ የሞራል ውድቀት፣ የውርስ ኃጢአት ይባላል። ሥጋዊ ባሕርያትን ከወላጆቻችን እንደወረስን ሁሉ፣ ኃጢአታዊ ተፈጥሮንም ከአዳም ወርሰናል። ንጉሥ ዳዊት በዚህ በወደቀ ሰው ተፈጥሮ ላይ ያዝናል፣ መዝሙር 51፡5 ላይ፡ “እነሆ፥ በዓመፃ ተፀነስሁ፥ እናቴም በኃጢአት ወለደችኝ።”

ሌለኛው የኃጢአት ዓይነት የፍቃድ (የግል) ኃጢአት በመባል ይታወቃል። በሁለቱም፣ በገንዘብና በሕጋዊ መቼቶች ጥቅም ላይ ሲውል፣ የግሪኩ ቃል ሲተረጎም “የግል” ማለት “የአንዱ የሆነውን ነገር መውሰድና በሌለኛው ሒሳብ ማስቀመጥ ነው።” የሙሴ ሕግ ከመሰጠቱ በፊት ኃጢአት በሰው ላይ አልተቆጠረም ነበር፣ ምንም እንኳ ሰዎች በውርስ ኃጢአት ምክንያት ኃጢአተኞች የነበሩ ቢሆኑም። ሕግ ከተሰጠ በኋላ፣ ሕግን በመጣስ ምክንያት ኃጢአት መታሰብ (መቆጠር) ጀመረ፣ በእነርሱ ላይ (ሮሜ 5፡13)። ከሕግ መተላለፍ በፊት እንኳ ቢሆን፣ በሰው ላይ ተቆጠረ፣ የመጨረሻው የኃጢአት ቅጣት (ሞት) መግዛቱን ቀጠለ (ሮሜ 5፡14)። ሰዎች ሁሉ፣ ከአዳም እስከ ሙሴ፣ በሞት ሥር ነበሩ፣ የሙሴን ሕግ በኃጢአታዊ ድርጊታቸው በመቃወም ሳይሆን፣ (እነርሱም ያልነበራቸውን)፣ ነገር ግን በወረሱት በገዛ ራሳቸው የኃጢአት ተፈጥሮ ምክንያት። ከሙሴ በኋላ፣ ሰዎች ለሞት ተገዢ ሆኑ፣ በሁለቱም፣ ከአዳም በወረሱት ኃጢአት እና ፈቅደው የእግዚአብሔርን ሕግጋት በመጣሳቸው ምክንያት።

እግዚአብሔር የመተላለፍን መርሕ የሰውን ልጅ ለመጥቀም ተጠቀመበት፣ የአማኞችን ኃጢአት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ሲያኖር፣ እሱም የዛን ኃጢአት ዋጋ የከፈለ— ሞት— በመስቀል ላይ። ኃጢአታችንን በኢየሱስ ላይ በማኖር፣ እሱን እንደ ኃጢአተኛ ቆጠረው፣ እሱም ያልሆነውን፣ እናም ለመላው ዓለም ኃጢአት ሞተ (1 ዮሐንስ 2፡2)። መረዳት የሚያስፈልገው ጠቃሚ ነገር ኃጢአት በእርሱ ላይ መደረጉ ነው፣ እርሱ ግን ከአዳም አልወረሰውም። የኃጢአትን ቅጣት ተሸከመ እንጂ፣ ፈጽሞ ኃጢአተኛ አልሆነም። የእርሱ ንጹሕና ፍጹም ባሕርይ በኃጢአት አልተነካካም። እሱም በሰው ዘር ሁሉ በተፈጸመ ኃጢአት እንደ ኵነኔኛ ተቆጠረ፣ ምንም እንኳ ምንም ባይፈጽምም። በምትኩ፣ እግዚአብሔር የክርስቶስን ጽድቅ በአማኞች ላይ አኖረ፣ የእኛን ሒሳብም በእርሱ ጽድቅ ሞላው፣ ልክ የእኛን ኃጢአት በእርሱ ሒሳብ ላይ እንዳኖረ (2 ቆሮንቶስ 5፡21)።

ሦስተኛው ዓይነት ኃጢአት የግል ኃጢአት ነው፣ እሱም በየዕለቱ በእያንዳንዱ የሰው ልጅ የሚፈጸም። ከአዳም ኃጢአታዊ ተፈጥሮ በመውረሳችን ምክንያት፣ የግል፣ የራሳችንን ኃጢአት እንፈጽማለን፣ እያንዳንዱ ንጹሕ ከሚመስለው እውነት ያልሆነ፣ እስከ ግድያ። እምነታቸውን በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ ያላኖሩ የእነዚህን የግል ኃጢአቶች ቅጣት መክፈል ይኖርባቸዋል፣ ብሎም ከውርስና ከፍቃድ ኃጢአት ጋር። ሆኖም፣ አማኞች ከዘላለም የኃጢአት ቅጣት ነጻ ወጥተዋል— ገሃነምና መንፈሳዊ ሞት— አሁን ደግሞ እኛ ኃጢአትን ለመቋቋም ኃይል አለን። እንግዲህ እኛ መምረጥ እንችላለን፣ የግል ኃጢአትን ላለመሥራት፣ ምክንያቱም በእኛ ላይ በሚያድረው በመንፈስ ቅዱስ ኃጢአትን ለመቋቋም ኃይልን ስለምናገኝ፣ እኛን በመቀደስና ኃጢአተኝነታችንን በማሳሰብ፣ በምንተላለፍበት ጊዜ (ሮሜ 8፡9-11)። አንድ ጊዜ የግል ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር ከተናዘዝን በኋላና ይቅርታን ከጠየቅን ወዲህ፣ ከእርሱ ጋር ፍጹም ወደ ሆነ ኅብረትና ግንኙነት እንመለሳለን። “ኃጢአታችንን ብንናዘዝ፣ እሱ ኃጢአታችን ይቅር ሊለንና ከዓመጻም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው” (1 ዮሐንስ 1፡9)።

እኛ ሁላችንም ሦስት ጊዜ ተኮንነናል፣ በውርስ ኃጢአት፣ በፍቃድ ኃጢአት፣ እና በግል ኃጢአት ምክንያት። ለዚህ ኃጢአት ብቸኛው ትክክለኛ ቅጣት ሞት ነው (ሮሜ 6፡23)፣ ሥጋዊ ሞት ብቻ ሳይሆን መንፈሳዊ ሞት (ራዕይ 20፡11-15)። ምስጋና ይብዛለት፣ የውርስ ኃጢአት፣ የፍቃድ ኃጢአት፣ እና የግል ኃጢአት በኢየሱስ መስቀል ላይ ተሰቅሏል፣ እናም አሁን በኢየሱስ ክርስቶስ በአዳኝነቱ ላይ ባለ እምነት “በደሙ በኩል መዋጀት አለን፣ የኃጢአት ይቅርታ፣ እንደ ጸጋው ባለ ጠግነት” (ኤፌሶን 1፡7)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የኃጢአት ፍቺ ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries