settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የኃጢያተኛው ፀሎት ማለት ምንድነው?

መልስ፤


የኃጢያተኛው ፀሎት የሚባለው አንድ ሰው በደለኛ መሆኑ ሲገባው ለእግዚሐብሔር የሚያቀርበው ፀሎት ሲሆን በዚህም አዳኝ እንደሚያስፈልገው የሚገልጽበት ሁኔታ ነው። የኃጢያተኛው ፀሎት ማቅረብ በራሱ የሚፈይደው ነገር የለም። የኃጢያተኛው ፀሎት ከምር ውጤታማ የሚሆነው ሰውዬው ስለበደለኝነቱ የሚያቀርበውን፣ የተረዳውን፣ የሚያምነውን በግልጽ አውቆ ድነት እንደሚያስፈልገው ሲረዳ ነው።

የመጀመሪያው የአንድ ኃጢያተኛ ፀሎት ገጽታ፣ ሁላችንም በደለኞች መሆናችንን መረዳት ነው። ሮሜ 3፡ 10 እንደሚያውጀው “እንዲህ ተብሎ እንደተጻፈ ጻድቅ የለም አንድስ ስንኳ።” መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ እንደሚናገር ሁላችንም በድለናል። ከእግዚሐብሔር ምህረትና ይቅርታ የሚያስፈልገን ኃጢያተኞች ነን። (ቲቶ 3፡ 5-7)። በኃጢያታችን ምክንያት ዘላለማዊ ቅጣት ይገባናል። (ማቴዎስ 25፡ 46)። የኃጢያተኛው ፀሎት ከፍርድ ይልቅ ለፀጋ የሚደረግ ተማፅኖ ነው። ከቁጣ ይልቅ ለምህረት የሚቀርብ ጥያቄ ነው።

ሁለተኛው የኃጢያተኛ ፀሎት ሌላ አካል እግዚሐብሔር የኛን የኃጢያት ሁኔታ ለማስወገድ ያቀረበውን መፍትሔ ማወቅ ነው። እግዚሐብሔር ስጋ ለብሶ ሰው በመሆን በኢየሱስ ክርስቶስ አካል ቀረበ። (ዮሐንስ 1፡ 1፣ 14) ኢየሱስ የእግዚሐብሔርን እውነት በማስተማር፣ በፍፁም ጽድቅ ኃጢያት የለሽ ይህወት ኖሯል። (ዮሐንስ 8፡ 46፣ 2ኛ ቆሮንቶስ 5፡ 21)። ኢየሱስ በኛ ፋንታ በመስቀል ላይ በመሞት ለኛ የተዘጋጀውን ቅጣት ተቀበለልን። (ሮሜ 5፡ 8)። ኢየሱስ ከሞት በመነሳት በኃጢያት፣ በሞትና በገሐነም እሳት ያለውን ድል አረጋገጠልን። (ቆሎሴ 2፡ 15፣ 1ኛ ቆሮ ፡ 15)። በዚህ ሁሉ ምክንያት ኃጢያቶቻችን ተወግደውልን በገነት የዘላለም ቤት ቃል ተገብቶልናል። ይህ የሚሆነው እምነታችንን በኢየሱስ ክርስቶስ ስናደርግ ነው። እኛ ድነት የምናገኘው በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን በፀጋው ብቻ ነው። የኤፌሶን መልዕክት 2፡ 8 እንደሚያብራራው “ፀጋው በእምነት አድኖአችኋልና ይህም የእግዚሐብሔር ስጦታ ነው እንጂ ከእናንተ አይደለም።”

የኃጢያተኛውን ፀሎት ስታቀርብ ኢየሱስ ክርስቶስን እንደግል አዳኝህ መቀበልህንና በእርሱ መደገፍህን ለእግዚሐብሔር የምታውጅበት ቀላሉ መንገድ ነው። ድነትን የሚያስገኙ “አዚማዊ” ቃላት የሉም። በኢየሱስ ክርስቶስ ሞትና ትንሳኤ ማመን ብቻ ነው ድነትን የሚያስገኝልን። ኃጢያተኛ መሆንህ ከተረዳህና በኢየሱስ ክርስቶስ የሚገኘውን ድነት ትፈልግ እንደሆን ይህንን የኃጢያተኛ ፀሎት ለእግዚሐብሔር እንድታቀርብ እንጋብዝሐለን። “እግዚሐብሔር ሆይ እኔ ኃጢያተኛ መሆኔን አውቃለሁ። እንደ ኃጢአቴ ውጤት ሊከፈለኝ እንደሚገባ እገነዘባለሁ። ይሁን እንጂ ኢየሱስ ክርስቶስ የግል አዳኜ መሆኑን እታመናለሁ። የግል አዳኜና ጌታዬ መሆኑን በኢየሱስና በኢየሱስ ብቻ እታመናለሁ። ይቅር ስላልከኝና ድነትን ስለሰጠኸኝ ጌታዬ ሆይ አመሰግንሐለሁ! አሜን!

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የኃጢያተኛው ፀሎት ማለት ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries