settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የጸጋ ስጦታዬ ምን እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?

መልስ፤


ምንም ዓይነት ምትኀታዊ ቀመር ወይም የተወሰነ ሙከራ፣ የጸጋ ስጦታዎቻችን በትክክል ምን እንደሆኑ ሊገልጽልን የሚችል የለም። መንፈስ ቅዱስ እንደፈቀደው ስጦታዎችን ያከፋፍላል (1ኛ ቆሮንቶስ 12፡7-11)። ለክርስቲያኖች የተለመደው ችግር፣ እግዚአብሔርን ልናገለግልበት በምንፈልገው አካባቢ ለኛ በሚመስለን ጸጋ ስጦታ መያዝና መፈተን ነው። መንፈሳዊ ስጦታ የሚሠራው እንደዚህ አይደለም። እግዚአብሔር የጠራን በሁሉም ነገሮች በፍቃደኝነት እንድናገለግለው ነው። በሚያስፈልገን ምንም ዓይነት ስጦታ ወይም ስጦታዎች ሊያበቃን ይችላል፤ የጠራንን ሥራ ለመፈጸም።

መንፈሳዊ ተሰጥዎአችንን ለማግኘት በተለያዩ መንገዶች መለየት ይቻላል። የመንፈሳዊ ስጦታ ሙከራዎች ወይም ዳሰሳዎች፣ በጣም ሳንጠመድ ከተደረጉ ስጦታችን የት እንደሆነ እንድንገነዘብ በሚገባ ሊያሳዩን ይችላሉ። ከሌሎች የሚገኝ ማረጋገጫም መንፈሳዊ ተሰጥዎአችን ምን እንደሆነ ሊያሳየን ይችላል። ጌታን ስናገለግል የሚያዩን ሌሎች ሰዎች ዘወትር መንፈሳዊ ስጦታችንን ሊለዩ ይችላሉ፣ እኛ በሚገባ ያልጨበጥነውን ወይም ያላስተዋልነውን። ጸሎትም ደግሞ ጠቃሚ ነው። እንዴት መንፈሳዊ ስጦታ እንደሚሰጠን በትክክል የሚያውቀው አንዱ አካል፣ ስጦታ ሰጪው ራሱ ነው—መንፈስ ቅዱስ። እግዚአብሔርን ልንጠይቀው እንችላለን፣ እንዴት እንደተሰጠን፣ መንፈሳዊ ስጦታዎቻችንን ለእሱ ክብር በተሻለ ለመጠቀም።

አዎን፣ እግዚአብሔር አንዳንዶችን መምህራን እንዲሆኑ ጠርቷቸዋል፤ እናም የማስተማርን ጸጋ ሰጥቷቸዋል። እግዚአብሔር አንዳንዶችን አገልጋዮች እንዲሆኑ ጠርቷቸዋል፣ እርዳታ በማድረግ ጸጋ ባርኳቸዋል። ሆኖም፣ የጸጋ ስጦታችንን ለይቶ ማወቅ፣ ከጸጋ ስጦታችን ውጪ እግዚአብሔርን ማገልገል ያግደናል ማለት አይደለም። እግዚአብሔር ምን ዓይነት የጸጋ ስጦታ (ዎች) እንደ ሰጠን ማወቁ ጠቀሜታ አለውን? እንደ እውነቱ እርግጥ ነው። እግዚአብሔርን በሌሎች አግባቦች ልናገለግልበት የምንችለውን ዕድል የሚያሳጠን ከሆነ በመንፈሳዊ ስጦታ ላይ ከመጠን በላይ ማተኮሩ ስህተህ ነውን? አዎን። እግዚአብሔር እንዲጠቀምብን የተሰጠን ከሆነ፣ እሱ በሚያስፈልገን መንፈሳዊ ስጦታ ሊያዘጋጀን ይችላል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የጸጋ ስጦታዬ ምን እንደሆነ እንዴት ማወቅ እችላለሁ?
© Copyright Got Questions Ministries