settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ስለ መንፈሳዊ ውጊያ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?

መልስ፤


ስለ መንፈሳዊ ውጊያ ሲነሣ ሁለት ቀዳሚ ስሕተቶች ይኖራሉ— ማጋነን እና ማንኳሰስ። አንዳንዶች ለእያንዳንዱ ኃጢአት፣ ለእያንዳንዱ ግጭት፣ እና ለእያንዳንዱ ችግር አጋንንትን ተጠያቂ ያደርጋሉ፣ ያም መጣል የሚያስፈልገው። ሌሎች መንፈሳዊውን ዓለም ሙሉ ለሙሉ ችላ ይላሉ፣ እንዲሁም መጽሐፍ ቅዱስ ውጊያችን ከመንፈሳዊ ኃይላት ጋር መሆኑን የነገረንን። ለስኬታማ መንፈሳዊ ውጊያ ቁልፉ ነገር መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛንን ማግኘት ነው። ኢየሱስ አንዳንድ ጊዜ ከሰዎች ያወጣ ነበር፣ አንዳንድ ጊዜም ሰዎችን ይፈውስ ነበር፣ አጋንንትን ሳይጠቅስ። ሐዋርያው ጳውሎስ ክርስቲያኖችን ያሳስባል፣ በራሳቸው ከኃጢአት ጋር እንዲታገሉ (ሮሜ 6) እና ከክፉው ጋር እንዲታገሉ (ኤፌሶን 6፡10-18)።

ኤፌሶን 6፡10-12 ይገልጻል፣ “በቀረውስ በጌታና በኃይሉ ችሎት የበረታችሁ ሁኑ። የዲያብሎስን ሽንገላ ትቃወሙ ዘንድ እንዲቻላችሁ የእግዚአብሔርን ዕቃ ጦር ሁሉ ልበሱ። መጋደላችን ከደምና ከሥጋ ጋር አይደለምና፥ ከአለቆችና ከሥልጣናት ጋር ከዚህም ከጨለማ ዓለም ገዦች ጋር በሰማያዊም ስፍራ ካለ ከክፋት መንፈሳውያን ሠራዊት ጋር ነው እንጂ።” ይህ ጽሑፍ ዋነኛ እውነቶችን ያስተምራል፡ ብርቱ መሆን የምንችለው በጌታ ኃይል ነው፣ የሚጠብቀን የእግዚአብሔር የጦር ዕቃ ነው፣ ውጊያችንም በዓለም ላይ ከክፉ ከመንፈሳዊ ኃይላት ጋር ነው።

ሁነኛ የሆነ ምሳሌ በጌታ ኃይል ብርታት ሚካኤል ነው፣ ሊቀ-መልአኩ፣ ይሁዳ 9 ላይ። ሚካኤል፣ ከእግዚአብሔር መላእክት ሁሉ እጅግ ብርቱ የሆነው፣ በገዛ ራሱ ኃይል ሰይጣንን አልገሠጸውም፣ ግን አለ፣ “ ጌታ ይገሥጽህ!” ራዕይ 12፡7-8 እንደ መዘገበው በመጨረሻው ሰዓት ሚካኤል ሰይጣንን ድል ያደርጋል። አሁንም፣ ከሰይጣን ጋር ወደ ውጊያ ሲመጣ፣ ሚካኤል በእግዚአብሔር ስምና ሥልጣን ነው የሚገሥጸው፣ በገዛ ራሱ ሳይሆን። ከኢየሱስ ክርስቶስ ጋር ባለን ግንኙነት ብቻ ነው ክርስቲያኖች በሰይጣንና በአጋንንቱ ላይ ሥልጣን የሚኖረን። በእሱ ስም ብቻ ነው ተግሣጻችን ኃይል የሚኖረው።

ኤፌሶን 6፡13-18 እግዚአብሔር ለእኛ የሰጠንን መንፈሳዊ የጦር ዕቃ ይገልጽልናል። ጸንተን መቆም አለብን፣ በእውነት መታጠቂያ፣ በጽድቅ ጥሩር፣ በሰላም ወንጌል፣ በእምነት ጋሻ፣ በመዳንም ራስ ቁር፣ በመንፈስ ሰይፍ፣ እና በመንፈስ በመጸለይ። እነዚህ መንፈሳዊ የጦር ዕቃዎች በመንፈሳዊው ውጊያ የሚወክሉት ምንድነው? በሰይጣን ውሸት ላይ እውነቱን መናገር ይኖርብናል። ጻድቅ ተብለን በተጠራንበት ሐቅ፣ ክርስቶስ ለእኛ በመሠዋቱ ማረፍ አለብን። ወንጌልን ማወጅ ይኖርብናል፣ ምንም ዓይነት ተቃውሞ ቢገጥመንም። በእምነታችን መናወጥ አይኖርብንም፣ ምንም ያህል በጽኑ ሁኔታ ብንጠቃም። የመጨረሻ መከላከያችን በደኅንነታችን ያለን ዋስትና ነው፣ ማንም መንፈሳዊ ኃይል ሊወስድብን የማይችለው ዋስትና። የማጥቂያ መሣርያችን የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ የእኛ ሐሳብና ስሜት ሳይሆን። የኢየሱስን ምሳሌ መከተል አለብን፣ አንዳንድ መንፈሳዊ ድሎች የሚገኙት በጸሎት ብቻ መሆኑን በመገንዘብ።

ኢየሱስ የመጨረሻ ምሳሌያችን ነው፣ ለመንፈሳዊ ጦርነት። ኢየሱስ ከሰይጣን የተሰነዘረበትን ቀጥተኛ ጥቃት፣ ማለትም በበረሀ በእርሱ ሲፈተን እንዴት እንደተቋቋመ አስተውል (ማቴዎስ 4፡1-11)። እያንዳንዱ ፈተና ምላሽ ያገኘው በተመሳሳይ መንገድ ነው— “ተጽፏል” በሚለው ቃል ነው። ኢየሱስ አውቋል፣ የሕያው እግዚአብሔር ቃል በሰይጣን ፈተና ላይ እጅግ ኃይለኛ የጦር ዕቃ መሆኑን። ኢየሱስ ራሱ ቃሉን ሰይጣንን ለመቃወም ከተጠቀመ፣ እኛስ ከዛ ያነሰ ነገር ለመጠቀም እንደፍራለን?

በመንፈሳዊ ውጊያ ላይ እንዴት መደረግ እንደሌለበት የተሻለው ምሳሌ የአስቄዋ ሰባት ልጆች ናቸው። “አጋንንትንም እያወጡ ይዞሩ ከነበሩት አይሁድ አንዳንዶች። ጳውሎስ በሚሰብከው በኢየሱስ እናምላችኋለን እያሉ ክፉዎች መናፍስት ባሉባቸው ላይ የጌታን የኢየሱስን ስም ይጠሩባቸው ዘንድ ሞከሩ። የካህናትም አለቃ ለሆነ አስቄዋ ለሚሉት ለአንድ አይሁዳዊ ይህን ያደረጉ ሰባት ልጆች ነበሩት። ክፉው መንፈስ ግን መልሶ፦ ኢየሱስንስ አውቀዋለሁ ጳውሎስንም አውቀዋለሁ፤ እናንተሳ እነማን ናችሁ? አላቸው። ክፉው መንፈስም ያለበት ሰው ዘለለባቸው ቆስለውም ከዚያ ቤት ዕራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ በረታባቸው አሸነፋቸውም” (ሐዋ. 19፡13-16)። ሰባቱ የአስቄዋ ልጆች የኢየሱስን ስም ተጠቅመው ነበር። ያ በቂ አይደለም። ሰባቱ የአስቄዋ ልጆች ከኢየሱስ ጋር ግንኙነት አልነበራቸውም፤ ስለዚህ፣ ቃላቸው ምንም ኃይልና ሥልጣን አልነበረውም። የአስቄዋ ሰባት ልጆች በአሠራሩ ነበር የታመኑት። እነርሱም በኢየሱስ አልታመኑም፣ እንደ ጌታና አዳኛቸው፣ እንዲሁም የእግዚአብሔርን ቃል በመንፈሳዊ ውጊያቸው አልተጠቀሙም። በውጤቱም፣ አሳፋሪ ድብደባ ደረሰባቸው። ከእነርሱ መጥፎ ምሳሌ ትምህርት እናገኛለን፣ እናም መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያዘው መንፈሳዊ ውጊያን ባግባቡ እንይዛለን።

በማጠቃለያ፣ በመንፈሳዊ ውጊያ ባለ ድል ለመሆን ቁልፎቹ ምንድናቸው? በቅድሚያ፣ በእግዚአብሔር ኃይል መታመን አለብን፣ በገዛ ራሳችን ሳይሆን። ሁለተኛ፣ በኢየሱስ ስም መገሠጽ አለብን፣ በራሳችን ሳይሆን። ሦስተኛ፣ ራሳችንን በእግዚአብሔር ሙሉ የጦር ዕቃ መጠበቅ አለብን። አራተኛ፣ ውጊያውን በመንፈስ ሰይፍ ማካሄድ አለብን— የእግዚአብሔር ቃል። በመጨረሻም፣ በሰይጣንና በአጋንንቱ ላይ መንፈሳዊ ውጊያ ስናካሂድ፣ እያንዳንዱ ኃጢአት ወይም ችግር አጋንንት አይደለም፣ ተግሣጽን የሚሻ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ስለ መንፈሳዊ ውጊያ መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries