settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ምትክ ሆኖ መዋጀት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


ምትክ ሆኖ መዋጀት የሚያመለክተው ኢየሱስ ክርስቶስ ለኃጢአተኞች ምትክ ሆኖ መሞቱን ነው። መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ሁሉ ኃጢአተኞች መሆናቸውን ያስተምራል (ሮሜ 3፡9-18፣ 23)። ለኃጢአተኝነታችን ቅጣቱ ሞት ነው። ሮሜ 6፡23 እንዲህ ያስነብባል፣ “የኃጢአት ደመወዝ ሞት ነውና፤ የእግዚአብሔር የጸጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።”

ቁጥሩ በርካታ ነገሮችን ያስተምራል። ክርስቶስ ከሌለን፣ እንሞትና ለዘላለም በገሃነም እንሆናለን፣ ይህም ስለ ኃጢአታችን ዋጋ ነው። ሞት እንደ መጽሐፍ ቅዱስ የሚያመለክተው “መለየትን” ነው። ሁሉም ይሞታል፣ ነገር ግን አንዳንዶች በመንግሥተ ሰማያት ከጌታ ጋር ለዘላለም ይኖራሉ፣ ሌሎች ደግሞ በገሃነም ለዘላለም ይኖራሉ። እዚህጋ የተጠቀሰው ሞት የሚያመለክተው በገሃነም የሚሆን ሕይወትን ነው። ሆኖም፣ ይህ ቁጥር የሚያስተምረን ሁለተኛው ነገር በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል የዘላለም ሕይወት እንደሚገኝ ነው። ይህ የእሱ ተቀያሪ መዋጀት ነው።

ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ሲሰቀል በእኛ ምትክ ሞቷል። እኛ ነበርን በመስቀል ላይ መሞት የነበረብን፣ ምክንያቱም የኃጢአተኝነት ሕይወት በመኖራችን። ነገር ግን ክርስቶስ ራሱ በእኛ ቦታ ቅጣቱን ተቀበለ— እሱ እኛን ተክቶ እኛ ይገባን የነበረውን ወሰደ። “እኛ በእርሱ ሆነን የእግዚአብሔር ጽድቅ እንሆን ዘንድ ኃጢአት ያላወቀውን እርሱን ስለ እኛ ኃጢአት አደረገው።” (2ኛ ቆሮንቶስ 5፡21)።

“ለኃጢአት ሞተን ለጽድቅ እንድንኖር፥ እርሱ ራሱ በሥጋው ኃጢአታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ” (1ኛ ጴጥሮስ 2፡24)። እዚህም እንደገና የምናየው ክርስቶስ፣ እኛ የፈጸምነውን ኃጢአት ወደ ራሱ ወስዶ ዋጋችንን እንደከፈለልን ነው። ጥቂት ቁጥሮችን ቀጥለን እናነባለን፣ “ክርስቶስ ደግሞ ወደ እግዚአብሔር እንዲያቀርበን እርሱ ጻድቅ ሆኖ ስለ ዓመፀኞች አንድ ጊዜ በኃጢአት ምክንያት ሞቶአልና፤ በሥጋ ሞተ በመንፈስ ግን ሕያው ሆነ” (1ኛ ጴጥሮስ 3፡18)። እነዚህ ቁጥሮች የሚያስተምሩን ክርስቶስ ለእኛ የደረገውን ቅያሪ ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን እነሱ ደግሞ የሚያስተምሩን፣ የእሱን ዋጆነት ነው፣ ማለትም እሱ ለኃጢአተኛው ሰው የሚገባውን ዋጋ ማሟላቱ ነው።

ሌለኛው ተጨማሪ አንቀጽ እሱም ስለ ተቀያሪ መዋጃ የሚናገረው ኢሳይያስ 53፡5 ነው። ይህ ቁጥር የሚናገረው ስለሚመጣው ክርስቶስ፣ እሱም ስለ ኃጢአታችን በመስቀል ላይ እንደሚሞት ነው። ይህ ትንቢት በጣም ዝርዝር ነው፣ እናም ስቅለቱ የተካሄደው ልክ ቀደም ብሎ እንደተተነበየው ነው። “እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።” ቅያሪውን አስተውሉ። እዚህም እንደገና ክርስቶስ ስለእኛ ዋጋ እንደከፈለ እናያለን!

እኛ በራሳችን የኃጢአታችንን ዋጋ ልንከፍል የምንችለው መቀጣትና ለዘላለም በገሃነም መሆን ነው። ነገር ግን የእግዚአብሔር ልጅ ኢየሱስ ክርስቶስ፣ ወደዚህ ዓለም መጣ የኃጢአታችንን ዋጋ ለመክፈል። እሱ ይሄንን በማድረጉ ምክንያት፣ እኛ አሁን የኃጢአታችንን ስርየት ብቻ አይደለም የምናገኘው፣ ነገር ግን ዘላለማዊነትን ከእሱ ጋር ልንሆን ነው። ይሄንን ለማድረግ ኢየሱስ ክርስቶስ በመስቀል ላይ ባደረገው ሥራ እምነታችንን ልናደርግ ይገባል። ራሳችንን ልናድን አንችልም፤ የእኛን ስፍራ የሚወስድ ተቀያሪ ያስፈልገናል። የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ተቀያሪ መዋጃ ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ምትክ ሆኖ መዋጀት ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries