settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የድንግል መውለድ ለምን በእጅጉን አስፈላጊ ሆነ?

መልስ፤


የድንግል መውለድ መሠረተ እምነት በጣም አስፈላጊ ነው (ኢሳይያስ 7፡14፤ ማቲዎስ 1፡23፤ ሉቃስ 1፡27፣ 34)። በቅድሚያ ቃሉ ሁነቱን እንዴት እንደሚገልጸው እንመልከት። የማርያም ምላሽ የሆነውን ጥያቄ ስንመለከት፣ “ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል?” (ሉቃስ 1፡34)፣ ገብርኤል ሲመልስ፣ “መንፈስ ቅዱስ ባንቺ ላይ ይመጣል፣ የልዑሉም ኃይል ይጸልልሻል” ብሏል፣ (ሉቃስ 1፡35) መልአኩም፣ ዮሴፍ ማርያምን ለማግባት ፍራቻ እንዳያድርበት እንዲህ በሚሉ ቃላት አበረታቶታል፡ “ከእስዋ የተጸነሰው ከመንፈስ ቅዱስ ነው” (ማቲዎስ 1፡20)። ማቲዎስ ስለ ድንግል ሲያስረዳ፣ “በመንፈስ ቅዱስ ፀንሳ ተገኘች” ብሏል፣ (ማቴዎስ 1፡18)። ገላትያ 4፡4 በተጨማሪ ስለ ድንግል መውለድ ያስተምራል፡ “እግዚአብሔር ከሴት የተወለደውን ልጁን ላከ።”

ከእነዚህ አንቀጾች፣ በእርጠኝነት ግልጽ የሚሆነው የኢየሱስ ልደት በማርያም አካል ላይ የተፈጸመ የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ነው። ሥጋዊ ያልሆነው (መንፈስ ቅዱስ) እና ሥጋ የሆነው (የማርያም ማኅፀን ሁለቱም በጉዳዩ ገብተውበታል። እርግጥ ማርያም ራስዋ ልታረግዝ አትችልም፣ በዚያ አግባብም እሷ እንደ “ዕቃ” ነች። የሥጋዌን ተአምር ሊያደርግ የሚችለው እግዚአብሔር ብቻ ነው።

ሆኖም፣ በማርያምና በኢየሱስ መካከል ያለውን አካላዊ ግንኙነት መካድ ኢየሱስ እውን ሰው አይደለም የሚል አንድምታ ያመጣል። መጽሐፍ የሚያስተምረው ኢየሱስ ፍጹም ሰው እንደሆነ ነው፣ እንደኛ ዓይነት አካላዊ ሥጋ ያለው። ይህንንም የተቀበለው ከማርያም ነው። በተመሳሳይ መልኩ፣ ኢየሱስ ፍጹም ሰው ነው፣ ዘላለማዊ፣ ኃጢአት የለሽ በሆነ ባሕርይ (ዮሐንስ 1፡14፤ 1ኛ ጢሞቲዎስ 3፡16፤ ዕብራውያን 2፡14-17።)

ኢየሱስ በኃጢአት አልተወለደም፤ ያም ማለት፣ ምንም የኃጢአት ተፈጥሮ የለውም (ዕብራውያን 7፡26)። ይህም የሚመስለው የኃጠአት ተፈጥሮ ከትውልድ ወደ ትውልድ በአባት አማካኝነት የሚተላለፈውን ለማለት ነው (ሮሜ 5፡12፣ 17፣19)። የድንግል መውለድ የኃጢአት ተፈጥሯዊ መተላለፍን አስቀርቶ ዘላለማዊው እግዚአብሔር ፍጹም ሰው እንዲሆን አስቻለ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የድንግል መውለድ ለምን በእጅጉን አስፈላጊ ሆነ?
© Copyright Got Questions Ministries