settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የእግዚአብሔርን ድምጽ እንዴት መረዳት እንችላለን?

መልስ፤


ይህ ጥያቄ በበርካታ ሰዎች በዘመናት ሁሉ መሐል ተጠይቋል። ሳሙኤል የእግዚአብሔርን ድምጽ ሰምቷል፣ ነገር ግን በዔሊ እስከተነገረው ድረስ መገንዘብ አልቻለም (1 ሳሙኤል 3፡1-10)። ጌዲዮን አካላዊ መገለጥ ከእግዚአብሔር ዘንድ ነበረው፣ እሱም የሰማውን ተጠራጥሯል፣ ምልክቶችን አንድ ጊዜ ሳይሆን ሦስት ጊዜ እስኪጠይቅ ድረስ (መሳፍንት 6፡17-22፣36-40)። የእግዚአብሔርን ድምጽ ስንሰማ፣ እሱ እየተናገረ መሆኑን እንዴት እናውቃለን? ከሁሉ በፊት፣ አንድ ነገር አለን፣ ጌዲዮንና ሳሙኤል የሌላቸው። የተሟላ መጽሐፍ ቅዱስ አለን፣ ተመስጧዊው የእግዚአብሔር ቃል፣ ለማንበብ፣ ለማጥናት፣ እና ለመመርመር። “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” (2 ጢሞቴዎስ 3፡16-17)። ስለ አንድ ርዕሰ-ጉዳይ ወይም የሕይወታችን ውሳኔ ጥያቄ ሲኖረን፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ እሱ ምን እንዳለ መመልከት ይኖርብናል። እግዚአብሔር ፈጽሞ በተጻራሪው አይመራንም፣ በቃሉ ካስተማረን ውጭ (ቲቶ 1፡2)።

የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት የእግዚአብሔር ልንሆን ይገባል። ኢየሱስ አለ፣ “በጎቼ ድምጼን ይሰማሉ፤ እኔም አውቃቸዋለሁ፣ እነርሱም ይከተሉኛል” (ዮሐንስ 10፡27)። የእግዚአብሔርን ድምጽ የሚሰሙት የእርሱ የሆኑት ናቸው — በጸጋው የዳኑ፣ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን። እነዚህ ናቸው በጎቹ፣ የእርሱን ድምጽ የሚሰሙና የሚገነዘቡ፣ እንደ እረኛቸው ስለሚያውቁት። የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመገንዘብ፣ የእርሱ መሆን ይገባናል።

ድምጹን የምንሰማው ለመጽሐፍ ቅዱስ ጥናት ጊዜ ስንሰጥ ነው፣ እንዲሁም ከቃሉ ጋር የጸጥታ የጠበቀ ግንኙነት። ከእግዚአብሔር እና ከቃሉ ጋር በቀረበ ወዳጅነት ረጅም ሰዓት ካለን፣ ድምጹንና የእርሱን ምሪት በሕይወታችን ለመገንዘብ ቀላል ይሆንልናል። የባንክ ሠራተኞች ሐሰተኛ ብሮችን እንዲለዩ ይሠለጥናሉ፣ እውነተኛ ብሮችን በጣም ቀርቦ በማጥናት፣ ሐሰተኛውን ለመለየት አመቺ እንዲሆን። ለእግዚአብሔር ቃል ቅርበት ሊኖረን ይገባል፣ አንዱ ስሕተትን በሚናገርበት ሰዓት፣ ከእግዚአብሔር አለመሆኑን እናውቃለን።

እግዚአብሔር ለሰዎች በሚሰማ መልኩ ዛሬ ሲናገር፣ በቀዳሚነት የሚናገረው በተጻፈው ቃሉ በኩል ነው። አንዳንድ ጊዜ የእግዚአብሔር ምሪት በመንፈስ ቅዱሱ በኩል ሊመጣ ይችላል፣ በሕሊናችን በኩል፣ በተያያዥ መንገዶች በኩል፣ እና በሌሎች ሰዎች ግንኙነት በኩል። ከቅዱስ ቃሉ እውቀት የሰማነውን በማነጻጸር፣ የእግዚአብሔርን ድምጽ መለየት እንማራለን።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የእግዚአብሔርን ድምጽ እንዴት መረዳት እንችላለን?
© Copyright Got Questions Ministries