settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔርን ማን ፈጠረው? እግዚአብሔር ከየት መጣ?

መልስ፤


የተለመደው የኢአማኒዎች (ኤቲስት) እና የተጠራጣሪዎች (ስኬፕቲክስ) መከራከሪያ ሲሆን፣ ሁሉም ነገር ምክንያት ካስፈለገው፣ እንዲሁ እግዚአብሔርም ምክንያት ያስፈልገዋል የሚል ነው። መደምደሚያውም እግዚአብሔር ምክንያት ካስፈለገው፣ እግዚአብሔር እግዚአብሔር አይደለም ማለት ነው (እናም እግዚአብሔር እግዚአብሔር ካልሆነ፣ እግዚአብሔር የለም ማለት ነው)። ይህ በመጠኑም ቢሆን “እግዚአብሔርን ማን ሠራው?” ከሚለው መሠረታዊ ጥያቄ ወሰብሰብ (ረቀቅ) ያለ ነው። ሁሉም እንደሚያውቀው ማንኛውም ነገር ከምንም እንደማይመጣ ነው። ስለሆነም፣ እግዚአብሔር “አንድ ነገር” ከሆነ፣ እናም በርግጥ፣ ምክንያት (መነሻ) ይኖረዋል ማለት ነውን?

ጥያቄው ተንኮል አለበት፣ ምክንያቱም የሚያደባው በተሳሳተ ግምት ሆኖ፣ ይህም እግዚአብሔር ከሆነ ስፍራ እንደመጣና ከዚያም ያ ስፍራ የት እንደሆነ በመጠየቅ ነው። መልሱም፣ ጥያቄው ራሱ ትርጉም አልባ መሆኑ ነው። ይህም፣ “ሰማያዊ ምን ምን ይሸታል?” ብሎ እንደ መጠየቅ ያህል ነው። ሰማያዊ፣ ሽታ ያላቸው ነገሮች ምድብ አይደለም፣ ስለሆነም ጥያቄው ራሱ የተሳሳተ ነው። በተመሳሳይ መንገድ፣ እግዚአብሔር ከተፈጠሩ ወይም መነሻ ካላቸው ነገሮች ምድብ አይደለም። እግዚአብሔር መነሻ የሌለው እና ያልተፈጠረ ነው— በቀላሉ እሱ ይኖራል።

ይሄንን እንዴት እናውቃለን? እኛ ከምንም ነገር ምንም ነገር እንደሚመጣ እናውቃለን። ስለዚህ፣ በየትኛውም ጊዜ ፈጽሞ ሕላዌ የነበረው ምንም ነገር ካልነበረ፣ እንዲሁ ምንም ነገር ወደ ሕላዌ አይመጣም ማለት ነው። ነገር ግን ነገሮች ሕልውና አላቸው። ስለሆነም፣ ፈጽሞ ምንም ነገር ያልነበረበት ጊዜ ሊኖር እንደማይችል፣ አንድ ነገር ዘወትር በሕላዌው ይኖራል ማለት ነው። ይሄንን ዘላለማዊ ሕላዌ ያለውን እግዚአብሔር ብለን እንጠራዋለን። እግዚአብሔር መነሻ የሌለው ሕላዌ ሲሆን እሱም ሁሉንም ነገሮች ወደ ሕላዌ ያመጣ ነው። እግዚአብሔር ያልተፈጠረ ፈጣሪ ሲሆን፣ መላውን ፍጥረት (ዩኒቨርስ) እና በውስጡ ያለውን የፈጠረ ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔርን ማን ፈጠረው? እግዚአብሔር ከየት መጣ?
© Copyright Got Questions Ministries