settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር የተተነፈሰ ቃል ነው ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


ሰዎች ስለ መጽሐፍ ቅዱስ እስትንፋሳዊነት ሲናገሩ፣ እነሱ የሚጠቅሱት እውነት፣ እግዚአብሔር በመለኮታዊነት ሰዋዊ የቅዱስ ቃሉን ጸሐፊዎች አነሣሣ፣ በዚህ ዓይነት መንገድ እነሱ የጻፉት የእግዚአብሔር የራሱ ቃል ነው። በቅዱሳን መጻሕፍት ዐውደ-ጽሑፍ፣ እስትንፋሳዊ የሚለው ቃል፣ ፍችው በቀላሉ፣ “እግዚአብሔር የተነፈሰው” ነው። እስትንፋሳዊ ቃል ማለት፣ መጽሐፍ ቅዱስ በርግጥ የእግዚአብሔር ቃል ነው፣ እናም መጽሐፍ ቅዱስን ከሌሎች ሁሉ መጻሕፍት ልዩ ያደርገዋል።

መጽሐፍ ቅዱስ እስከ ምን ደረጃ በእግዚአብሔር የተተነፈሰ እንደሆነ የተለያዩ አመለካከቶች ቢኖሩም፣ መጽሐፍ ቅዱስ ራሱ እንደሚያስረግጠው እያንዳንዱ ቃል በየትኛውም የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ከእግዚአብሔር አንደመጣ ምንም ጥርጥር ሊኖር አይችልም (1 ቆሮንቶስ 2:12-13፤ 2 ጢሞቴዎስ 3:16-17)። ይህ የቅዱሳን መጻሕፍት አተያይ ዘወትር የሚጠቀሰው እንደ “ቃላዊ አጠቃላይ” እስትንፋሳ ቃል ነው። ያ ማለት እስትንፋሰ እግዚአብሔር እስከ ቃላት ደረጃ የሚስፋፋ መሆኑን ነው (ቃላዊ) — ጽንሰ-ሐሳቦችን ወይም ሐሳቦችን ሳይሆን— እናም እስትንፋሳዊ ቃል እስከ ሁሉም የቅዱስ ቃሉ ክፍሎች ይስፋፋል፣ እንዲሁም ወደ ሁሉም የቅዱስ ቃሉ ርዕሰ-ጉዳዮች (አጠቃላይ)። አንዳንድ ሰዎች የሚያምኑት የተወሰኑ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ብቻ እስትንፋሳዊ ቃል አንደሆኑ ነው፣ ወይም አስተሳሰቦችና ጽንሰ-ሐሳቦች ብቻ እነሱም ከሃይማኖት ጋር የተያያዙት እስትንፋሳዊ ቃል እንደሆኑ ነው፣ ነገር ግን እንደዚህ ዓይነቶቹ የእስትንፋሳዊ ቃል አተያዮች ባጭሩ ውድቅ ይሆናሉ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ራሱ ከሚያስረግጠው አኳያ። ሙሉ የቃል አጠቃላይ እስትንፋሳዊነት ለእግዚአብሔር ቃል እጅግ አስፈላጊ ባሕርይ ነው።

እስትንፋሳዊ ቃል ዳርቻ በ2 ጢሞቴዎስ 3፡16 ላይ በግልጽ ይታያል፣ “የእግዚአብሔር ሰው ፍጹምና ለበጎ ሥራ ሁሉ የተዘጋጀ ይሆን ዘንድ፥ የእግዚአብሔር መንፈስ ያለበት መጽሐፍ ሁሉ ለትምህርትና ለተግሣጽ ልብንም ለማቅናት በጽድቅም ላለው ምክር ደግሞ ይጠቅማል።” ይህ ቁጥር የሚነግረን እግዚአብሔር ቅዱስ ቃሉን ሁሉ እስትንፋሳዊ ቃል እንዳደረገና ለእኛም ጠቀሜታ እንዲሆን ነው። የመጽሐፍ ቅዱስ የተወሰኑ ክፍሎች ብቻ አይደሉም ለሃይማኖታዊ ዶክትሪን ጥቅም ላይ የሚውሉት፣ እስትንፋሳዊ ቃል የሆኑት፣ ነገር ግን እያንዳንዱ ከዘፍጥረት እስከ ራዕይ ያለ ቃል ሁሉ እንጂ። በእግዚአብሔር እስትንፋሳዊ ቃል ስለሆነ ቅዱስ ቃሉ ሥልጣናዊ ነው ዶክትሪንን ለመመሥረት ጥቅም ላይ በሚውልበት ጊዜ፣ እንዲሁም ሰውን ለማስተማር በቂ ነው፣ ከእግዚአብሔር ጋር እንዴት ትክክለኛ የሆነ ግንኙነት እንደሚኖረው። መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስረግጠው በእግዚአብሔር እስትንፋሳዊ ቃል መሆኑን ብቻ አይደለም፣ ነገር ግን እኛን ለመለወጥና “ፍጹማን” ለማድረግ የሚችል ከተፈጥሮ በላይ የሆነ ችሎታ ደግሞ አለው። ከዚህ ሌላ ምን ያስፈልገናል?

ሌለኛው ከቅዱሳት መፃህፍት እስትነፈሳዊነት ጋር የሚያያዘው ቁጥር 2 ጴጥሮስ 1፡21 ነው። ይህ ቁጥር እንድንገነዘብ የሚረዳን፣ ምንም እንኳ እግዚአብሔር ሰዎችን ከነተለየ ስብዕናቸውና የአጻጻፍ ስልታቸው ቢጠቀምም፣ እግዚአብሔር በመለኮታዊነት እያንዳንዱን የጻፉትን ቃል እስትፈሳዊ አድርጎታል። ኢየሱስ ራሱ የቅዱስ ቃሉን ቃላዊ ግልጽ እስትንፋስነት እንዲህ ሲል አረጋግጧል፣ “እኔ ሕግንና ነቢያትን ለመሻር የመጣሁ አይምሰላችሁ፤ ልፈጽም እንጂ ለመሻር አልመጣሁም። እውነት እላችኋለሁ፥ ሰማይና ምድር እስኪያልፍ ድረስ፥ ከሕግ አንዲት የውጣ ወይም አንዲት ነጥብ ከቶ አታልፍም…” (ማቴዎስ 5:17-18)። በእነዚህ ቁጥሮች፣ ኢየሱስ የቅዱስ ቃሉን ትክክለኛነት ያጠናክራል፣ እስከ ትንሿ ዝርዝር እና እስከ ሥርዓተ-ነጥብ ድረስ ወርዶ፣ የእግዚአብሔር ቃል በመሆኑ ምክንያት።

ቅዱሳን መጻሕፍት የእግዚአብሔር ተመስጧዊ ቃል በመሆናቸው ምክንያት፣ እነሱ ደግሞ ፍጹምና ሥልጣናዊ ናቸው ብለን መደምደም እንችላለን። ትክክለኛ የእግዚአብሔር ፍቃድ አተያይ ቃሉን በትክክል ወደ መመልከት ይመራናል። እግዚአብሔር ፍጹም- ኃያል፣ ፍጹም-አዋቂ፣ ፍጹም-ፍጹም ስለሆነ የእሱ ቃልም በራሱ ልዩ መልክ ተመሳሳይ ባሕርይ አለው። የቅዱስ ቃሉን እስትንፋስነት ያጸኑት እነዚያው ተመሳሳይ ቁጥሮች፣ ፍጹምነቱንም ሆነ ሥልጣናዊነቱን ያጸናሉ። ያለ ጥርጥር፣ መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚያስረግጠው ነው—የማይካድ፣ ሥልጣናዊ፣ የእግዚአብሔር ቃል ለሰዎች።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ በእግዚአብሔር የተተነፈሰ ቃል ነው ማለት ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries