settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ካልቪናዊነት አልያም አርሜኒያዊነት — የትኛው አመለካከት ነው ትክክል?

መልስ፤


ካልቪናዊነት እና አርሜኒያዊነት ሁለት የሥነ-መለኮት ሥርዓቶች ሲሆኑ ደኅንነትን በተመለከተ በእግዚአብሔር ሉዓላዊነት እና በሰው ኃላፊነት መካከል ያለውን ግንኙነት ለማብራራት ይሞክራሉ። ካልቪናዊናት የተሰየመው ለጆን ካልቪን ነው፣ የፈረንሳይ ሥነ-መለኮታዊ፣ ከ1509-1564 የኖረ። አርሜኒያዊነት የተሰየመው ለጃኮበስ አርሚኒየስ ነው፣ የዳች ሥነ-መለኮታዊ፣ ከ1560-1609 የኖረ።

ሁለቱም ሥርዓቶች በአምስት ነጥቦች ሊጠቃለሉ ይችላሉ። ካልቪናዊነት አጠቃላይ የሰውን ብልሽት ሲይዝ፣ አርሜናዊነት ደግሞ ከፊል ብልሽትን ይይዛል። አጠቃላይ ብልሽት የሚለው፣ እያንዳንዱ የሰውነት ገጽታ በኃጢአት የተለማመደ ነው፤ ስለዚህ፣ የሰው ልጆች ወደ እግዚአብሔር መምጣት አልቻሉም፣ በገዛ ራሳቸው ጥረት። ከፊል ብልሽት የሚለው እያንዳንዱ የሰው ገጽታ በኃጢአት ተለማምዷል፣ ነገር ግን በገዛ ራሳቸው ጥረት በእግዚአብሔር ላይ እምነት እንዳያሳድሩ እስከማድረግ ድረስ አይዘልቅም።

ካልቪናዊነት በተጨማሪም፣ መመረጥ ሁኔታዊ አይደለም ብሎ ያምናል፣ አርሜኒያዊነት ደግሞ በሁኔታዊ መመረጥ ሲያምን። ሁኔታዊ ያልሆነ መመረጥ፣ እግዚአብሔር ሰዎችን ለደኅንነት ይመርጣል፣ በአጠቃላይ በራሱ ፍቃድ ላይ ብቻ በመመርኮዝ፣ በግለሰቡ ላይ ባለ ምንም መልካም ነገር ሳይሆን የሚል አመለካከት ነው። ሁኔታዊ መመረጥ የሚለው እግዚአብሔር ሰዎችን ለደኅንነት ይመርጣል፣ ማን በክርስቶስ ለመዳን እንደሚያምን ባለው ቀዳሚ እውቀት ላይ በመመርኮዝ፣ እንዲህም ግለሰቡ እግዚአብሔርን በሚመርጥበት ሁኔታ።

ካልቪናዊነት ማስተሠረያውን (መዋጃውን) የሚመለከተው በውስን ሲሆን፣ አርሜኒያዊነት የሚመለከተው ባልተወሰነ ነው። ይህ ከአምስቱ ነጥቦች እጅግ አወዛጋቢው ነው። ውስን የሆነ መዋጃ ማለት፣ ኢየሱስ የሞተው ለተመረጡት ብቻ ነው የሚል እምነት ነው። ያልተወሰነው መዋጃ ኢየሱስ ለሁሉም ሞቷል፣ ግን ሞቱ ሊሠራ የሚችለው ግለሰቡ በእምነት እሱን ሲቀበል ነው የሚል እምነት ነው።

ካልቪናዊነት በተጨማሪም የእግዚአብሔርን ጸጋ መቋቋም እንደማይቻል ሲያምን፣ አርሜኒያዊነት የሚለው አንድ ግለሰብ የእግዚአብሔርን ጸጋ ሊቃወም ይችላል ነው። መቋቋም የማይቻለው ጸጋ የሚሞግተው፣ እግዚአብሔር አንድን ሰው ለደኅንነት ሲጠራ፣ ያ ሰው በጥሪው መሠረት ወደ ደኅንነት ይመጣል በሚል ነው። የሚቋቋሙት ጸጋ የሚለው፣ እግዚአብሔር ሁሉንም ለደኅንነት ጠርቷል፣ ግን ብዙ ሰው የእሱን ጥሪ ተቃውሟል፣ አልተቀበለውምም።

ካልቪናዊነት የሚይዘው የቅዱሳንን ትዕግሥት ሲሆን አርሜኒያዊነት ደግሞ የሚይዘው ሁኔታዊ የሆነውን ደኅንነት ነው። የቅዱሳን ትዕግሥት የሚያመለክተው ጽንሰ-ሐሳብ፣ በእግዚአብሔር የተመረጠ ሰው በእምነት ይጠበቃል እናም በቋሚነት ክርስቶስን አይክድም ወይም ከእርሱ ፊቱን አይመልስም። ሁኔታዊ ደኅንነት፣ በክርስቶስ ያመነ በእሱ/በእሷ ነጻ ፍቃድ ከክርስቶስ ፊቱን ሊመልስ ይችላል፣ እናም ደኅንነትን ያጣል የሚል አመለካከት ነው።

ስለዚህ፣ በካልቪናዊነት አልያም አርሜኒያዊነት ክርክር፣ ማን ነው ትክክል? መገንዘብ አስገራሚ የሚሆነው፣ በክርስቶስ አካል ብዝኃነት፣ ሁሉም ዓይነት የካልቪናዊነትና አርሜኒያዊነት ድብልቅ መኖሩ ነው። አምስት ነጥቦች ካልቬኒያውያን እና አምስት ነጥቦች አርሜኒያውያን አሉ፣ እንዲሁም በተመሳሳይ ጊዜ ሦስት ነጥቦች ካሊቪናውያን እና ሁለት ነጥቦች አርሜንያውያን። በርካታ አማኞች የሁለቱ አመለካከቶች እንደ ድብልቅ ያለ ነገር ላይ ደርሰዋል። በመዳረሻውም፣ በእኛ እይታ ሁለቱም ሥርዓቶች ያጡት ነገር፣ ማብራራት የማይቻለውን ለማብራራት በመሞከራቸው ነው። የሰው ልጆች ይህን የመሰለውን ጽንሰ-ሐሳብ ሙሉ ለሙሉ ለመረዳት ብቃት የላቸውም። አዎን፣ እግዚአብሔር ፍጹም ሉዓላዊና ሁሉንም የሚያውቅ ነው። አዎን፣ የሰው ልጆች ተገቢውን ውሳኔ እንዲያደርጉ የተጠሩ ናቸው፣ በክርስቶስ ላይ እምነትን በማኖር ለመዳን። እነዚህ ሁለት ገጽታዎች ለእኛ ተቃርኗዊ ሊመስሉን ይችላሉ፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ሐሳብ ፍጹም የሆነ ስሜት ይሰጣሉ።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ካልቪናዊነት አልያም አርሜኒያዊነት — የትኛው አመለካከት ነው ትክክል?
© Copyright Got Questions Ministries