ጥያቄ፤
ክርስቲያን ወደ ኃኪም መሄድ አለበት?
መልስ፤
አንዳንድ ክርስቲያኖች አሉ የህክምና ክትትልን መፈለግ በእግዚአብሔር ላይ እምነት ማጣት መስሎ የሚታያቸው አሉ፡፡ በእምነት ቃል እንቅስቃሴ ሃኪምን ማማከር እንደ እምነት መጉደል ተደርጎ ስለሚቆጠር እግዚአብሔር እንዳይፈውሰን ይከለክላል ይላሉ፡፡ እንደ ክርስቲያን ሳይንስ ቡድን ላሉ የሃኪሞችን እርዳታ መፈለግ አንዳድ ጊዜ እግዚአብሔር እንድንፈወስበት የሰጠንን ኃይል ለመጠቀም እንደ ጋሬጣ ይታያል፡፡ እንደዚህ አይነቱ አመለካከት ትልቅ ጥፋት ነው፡፡ መኪናህ ጉዳት ቢደርስበት ወደ መካኒክ ትወስደዋለህ ወይስ እግዚአብሔር ተአምር እንዲያደርግ እና እንዲፈውስልህ ትጠብቃለህ; በቤትህ ውስጥ ያለው ቧንባ በፈነዳ ባንቧ ሰራተኛ ወጥተህ ትፈልጋለህ ወይስ እግዚአብሔር እንዲጠግንል ትጠብቃለህ; እግዚአብሔር መኪናችን ማደስና ቧንቧውን መጠገን እንደሚችለው ሁሉ አካላችንንም መፈወስ ይችላል፡፡ እግዚአብሔር ታአምራት ማድረግና የመፈወሱ እውነታ ሁልጊዜ እኛን ለመርዳት በእወቀት ወስጥ ያለፉ ሰዎችን እርዳታ ከመፈለግ ይልቅ ሁልጊዜ ተአምራት መጠበቅ አለብን ማለት አይደለም፡፡
ሌላው ኃኪሞች ብዙ ጊዜ በመጽሐፍ ቅዱስ ብዙ ጊዜ በማጣቀሻነተ ተጠቅሰዋል፡፡ ያለ አውዱ ሊወሰድ የሚችል ብቸኛ ወደ ሃኪሞች መሄድ የለብንም ብሎ ለማስተማር ሊወሰድ የሚችል ጥቅስ 2ዜና 16፡12 ‹‹ በነገሠም በሠላሳ ዘጠኝኛው ዓመት አሳ እግሩን ታመመ ደዌውም ጸናበት ነገር ግን በታመመ ጊዜ ባለ መድኃኒቶችን እንጂ እግዚአብሔርን አልፈለገም።›› የሚል ነው፡፡ ጉዳዩ የአሳ ሃኪሞችን አለመፈለጉ አይደለም ግን ‹‹እርዳታን ከእግዚአብሔር አልፈለገም›› ወደ ኃኪም እንኳ ስንሄድ እምነታችን ሙሉ በሙሉ መሆን ያለበት በእግዚአብሔር እንጂ በሃኪሙ አይደለም፡፡
ስለ ‹‹የመድሃኒት ህክምና›› የሚናገሩ ብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች አሉ፡፡ በአጠቅለያ ባንዴጅ መጠቀም(ኢሳ 1:6), ዘይት (ያዕ 5:14), ዘይት እና ወይን (ሉቃ 10:34), ቅጠሎች (እዝ 47:12), ወይን (1 ጢሞ 5:23), እና ቀባት, የሚቀባ የገልአድ መድሃኒት (ኤር 8:22). እንዲሁም የሃዋሪያት ሥራ እና የሉቃስ ወንጌል ጸሃፊ የሆነው ሉቃስ በጳውሎስ ‹‹የተወደደው ባለመድሃኒ›› ተብሎአለ፡፡ (ቆላ 4:14).
ማር 5፡25-30 የማያቆርጥ ደም ይፈሳት የነበረች ሴት ታሪክ ይናገራል፤ ገንዘቧን ሁሉ አፍስሳ ባለመድሃኒቶች ግን ሊፈውሷት አልቻሉም፡፡ ወደ ኢየሱስ መጣች የልብሱን ጫፍ ብነካው እፈወሳለሁ ብላ አመነች በእምነትም ነካችው ተፈወሰች፡፡ ኢየሱስ ለምን ከኃጢያተኞች ጋር ጊዜ እንደሚያሳልፍ ለፈሪሳዊያን ሲመልስ እንዲህ አለ ማቲ 9፡12፡- ‹‹ሕመምተኞች እንጂ ባለ ጤናዎች ባለ መድኃኒት አያስፈልጋቸውም፤›› ከዚህ ክፍል በመነሳት የሚከተሉትን መርህዎች መንደፍ ይቻላል፡፡
1) ኃኪሞች እግዚአብሔርን አይደሉም እንደዛም መታየት የለባቸውም፡፡ አንዳንድ ጊዜ ሊረዱን ይችላሉ ግን ሌላ ጊዜ የገንዘብ ማባከኛ ብቻ ይሆናሉ፡፡
2) ሃኪሞችን በምድር ላይ እንደተለመደው የእነርሱን እርዳታ መፈለግ በቃሉ የተወገዘ አይደለም፡፡ በእርግጥ የመድሃኒት ህክምናዎች በመልካም ታይተዋል፡፡
3) የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት በየተኛውም የህክምና ችግር መፈለግ አለበት (ያዕ 4:2; 5:13). ሁልጊዜ እኛ እንደፈለግነው ሊመልስልን ቃል አልገባልንም (ኢሳ 55:8-9), ግን የእርሱ ፈቃድ በፍቅር በእኛ ፍላጎት ውስጥ አልፎ እንደሚፈጸም ማረጋገጫ ዋስትና አለን (መዝ 145:8-9).
ስለዚህ ክርስቲያን ወደ ሃኪም መሄድ አለበት? እግዚአብሔር እኛ የፈጠረን ከፍተኛ የማወቅ ችሎታ ሰጥቶን ነው፤ መድሃኒት ለመስራት አካላችንን ለማከም እንድንችል ችሎታን ሰጥቶናል፡፡ ይህን እውቀት መጠቀም የህክምና ፈውስ ማግኘት መፈለግም ምንም ስህተት የለበትም፡፡ ሃኪሞች ለእኛ ከእግዚአብሔር እንደ ተሰጡን ስጦታዎች እግዚአብሔር ለመፈወስ ከህመም ለማገገም መንገድ እንዳደረጋቸው መታየት ይችላሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ የእኛ ሙሉ እምነተ መሆን ያለበት በእግዚአብሔር ላይ ነው እንጂ በመድሃኒቶች እና በሃኪሞች ላይ መሆን የለበትም፡፡ ከባድ በሆኑ ወሳኔዎች በንለምነው ጥበብን ሊሰጠን ቃል የገባ ጌታ ስላለን እርሱንልንፈልግ ይገባል፡፡ (ያዕ 1፡5)
English
ክርስቲያን ወደ ኃኪም መሄድ አለበት? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?