ጥያቄ፤
ክርስቲያን አካላዊ እንቅስቃሴን ማድረግ አለበት? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጤና ምን ይላል?
መልስ፤
በህይወት ውስጥ እንዳሉ ሌሎች ብዙ ነገሮች አካለዊ እንቅስቃሴን በሚመለከት ገድብን የሚጥሱ ነገሮች አሉ፡፡ አንዳንዶች ሙሉ ሙሉ መንፈሳዊ ነገር ላይ ሲያተኩሩ የሰውነት አካላቸውን ይዘነጋሉ፡፡ ሌሎች ከልክ በላይ ስለ ሰውነት አካላቸው ከፍተኛ ትኩረት በመስጠት መንፈሳዊ እድገትን ይዘነጋሉ፡፡ ሁለቱም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ሚዛን ይጠይቃሉ፡፡ 1ጢሞ 4፡8 የሚነግረን ‹‹ሰውነትን ለሥጋዊ ነገር ማስለመድ ለጥቂት ይጠቅማልና፤ እግዚአብሔርን መምሰል ግን የአሁንና የሚመጣው ሕይወት ተስፋ ስላለው፥ ለነገር ሁሉ ይጠቅማል።›› ልብ ማለት ያለብን ይህ ክፍል አካላዊ ብቃትን አያስፈልግም አላለም፤ ይጠቅማል ብሎአል ግን እግዚአብሔርን መምሰልን ግን አሰቀድሞ ትልቅ ትርፍ አለው ብሎአል፡፡
ሌላው፡- ሐዋሪያው ጳውሎስ መንፈሳዊውን ነገር ለማስረዳት አካላዊ እንቅስቃሴን በ1ቆሮ 9፡24-27 ጠቅሶአል፡፡ ክርስቲያናዊ ሕይወት ሽልማትን ለማግኘት የምንሮጠው ሩጫ ነው ብሎአል፡፡ ልናገኘው የምንሮጠው ወጋ ግን ዘላለማዊና የማይጠፋ ነው፡፡ በ2ጢሞ 2፡5 ‹‹ደግሞም በጨዋታ የሚታገል ማንም ቢሆን፥ እንደሚገባ አድርጎ ባይታገል፥ የድሉን አክሊል አያገኝም።›› ብሎአል፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ የመጽሐፍ ቅዱስ ትኩረት ባይሆንም ጳውሎስ የአትሎቲክስ መግለጫዎችን መንፈሳዊ እውነታዎችን ለማመላከት የተጠቀመው አካላዊ እንቅስቃሴንና ውድድርን በመልካም በሚጠቅም መልኩ ስለሚመለከከት ነው፡፡ እኛ መንፈሳዊ አንዲሁም አካላዊ ፍጡራን ነን፡፡ እንደ እግዚአብሔር ቃል መንፈሳዊ ህይወት የበለጠ ትኩረት ያለው በሆንም መንፈሳዊውን ወይንም አካላዊውን ስጋችንን ስንረሳ እንታያለን፡፡
ስለዚህ በግልጽ ክርስቲያን አካላዊ እንቅስቃሴ ቢያደርግ ምንም ስህተት የለውም፡፡ በእርግጥ ለአካላችን ተገቢውን እንክብካቤ እንድናደርግ መጽሐፍ ቅዱስ በግልጥ ያስቀምጥልናል፡፡ (1ጢሞ 6፡19-20). በተመሳሳይ ሁኔታ መጽሐፍ ቅዱስ ከንቱነትን ይቃወማል (1 ሳሙ 16:7; ምሳ 31:30; 1 ጴጥ 3:3-4). አካላዊ እንቅስቃሴን ማድረግ አካላችንን የተለየ በማድረግ ሰዎች እንዲያደንቁን መሆን የለበትም፡፡ አካላዊ እንቅስቃሴ የምናደርገው አካላዊ ጤናችንን በመጠበቅ የበለጠ አካላዊ ኃይል በማግኘት የመለጠ ለመንፈሳዊ አላማችን የበለጠ ራሳችንን ለመስጠት ነው፡፡
English
ክርስቲያን አካላዊ እንቅስቃሴን ማድረግ አለበት? መጽሐፍ ቅዱስ ስለ ጤና ምን ይላል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?