ጥያቄ፤
ክርስቲያን እናቶች ስለመሆን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?
መልስ፤
እናትነት እግዚአብሔር ለብዙ ሴቶች ሊሰጠው የሚፈልገው ትልቅ ሃላፊነት ነው፡፡ ክርስቲያን እናት ለጆቿን እንድትውድ ተነግሮናል (ቲቶ 2:4-5), በእርሷ በኩል ትችት ዘለፋ በእግዚአብሔርና ደህንነትን በሰጣት በተሸከመችው በእግዚአብሔር ስም ላይ ማምጣት የለባትም፡፡
ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ናቸው፡፡ (መዝ 127:3-5). በቲቶ 2፡4 የግሪኩ ቃል ‹‹ፊሎቴክኖስ›› እናት ለልጇ የሚኖራትን ፍቅር ለመግለጽ ጥቅም ላይ ውሏል፡፡ ይህ ቃል የተለየ ‹‹የእናት ፍቅር›› የሚገልጽ ነው፡፡ ከዚህ ቃል ውስጥ የምናገኘው ሃሳብ ለልጆቻችን ልናደርግ የሚገባውን ጥንቃቄ እነርሱን ማሳደግ በፍቅር ማቀፍ የሚያስፈልጋቸውን በማቅረብ ከእግዚአብሔር እጅ እንደተቀበልናቸው ልዩ ስጦታ እያንዳንዳቸውን እንደ ጓደኛ ሆነን ማቅረብ የሚል ነው፡፡
በእግዚአብሔር ቃል ለክርስቲያን እናቶች የታዘዙ ትዕዛዞች አሉ፡፡
መገኘት- በጠዋት በቀትር እና በማታ (ዘዳ 6:6-7)
ተሳትፎ- መቀራረብ፣ መወያየት፣ ማሰብ፣ እና ህይወት አብሮ መካፈል (ኤፌ 6:4)
ማስተማር- ቃሉን እና የአለም መጽሐፍ ቅዱሳዊ እይታ (መዝ 78:5-6; ዘዳ 4:10; ኤፌ 6:4)
ማሰልጠን - ልጆች ያላቸውን ጥንካሬ ችሎታ እንዲያውቁና እንዲያሳድጉ መርዳት (ምሳ 22:6) እንዲሁም መንፈሳዊ ስጦታቸውን (ሮሜ 12:3-8 እና 1ኛቆሮ 12)
መቅጣት- እግዚአብሔርን መፍራት ማስተማር፤ ያለማቋረጥ መስመሩን ማሳየት፤ በፍቅርና፤ በጽንአት፤ (ኤፌ 6:4; ዕብ 12:5-11; ምሳ 13:24; 19:18; 22:15; 23:13-14; 29:15-17)
ማሳደግ- የማያቋርጥ የቃል ማበረታቻን የሚያገኙበትን ሁኔታ ማዘጋጀት፤ ሞክረው እንዲሳሳቱ ነጻነት መስጠት፤ ማፍቀር በየትኛውም ሁኔታ ውስጥ መውደድ (ቲቶ 2:4; 2 ጢሞ 1:7; ኤፌ 4:29-32; 5:1-2; ገላ 5:22; 1ኛ ጴጥ 3:8-9)
በታማኝነት ምሳሌ መሆን- የምትናገረውን መኖር ፤ በመልካም መኖር ለልጆች (ዘዳ 4:9, 15, 23; ምሳ 10:9; 11:3; መዝ 37:18, 37). በመልካም ምሳሌነት የመኖርን ምንነት ለጆች በመዳሰስና ሊማሩበት በሚችሉበት መንገድ ማሳየት፡፡
መጽሐፍ ቅዱስ ሆሉም ሴት እናት መሆን አለበት አይልም፡፡ ሆኖም በእናትነት የተባረኩ ግን ሃላፊነታቸውን በጥንቃቄ ሊወጡ ያስፈልጋቸዋል፡፡ እናቶች በልጆቻቸው ህይወት ውስጥ ትልቅ ቦታ እና ሚና አላቸው፡፡ እናትነት የማያስደስት ሃላፊነት አይደለም፡፡
እናት በእርግዝና ወቅት ልጆች እንደሚሸከሙና በጨቅላ ህጻንነታቸው እንደሚመግቡ እና እንደሚንከባከቡ እናቶች በጉርምስናም ሆነ በታዳጊነት በወጣትነት አድገው የራሳቸው ልጆች እንኳ በኖረቸው የማያቋርጥ ሚና በልጆቻቸው ህይወት ይጫወታሉ፡፡ የእናትነት ሚና የግድ ማደግና መለወጥ ሲኖርበት ፍቅር፤ ጥበቃ፤ ማሳደግ እና የምታደርገው ማበረታታት ምንጊዜም መቆም የለበትም፡፡
English
ክርስቲያን እናቶች ስለመሆን መጽሐፍ ቅዱስ ምን ይላል?