ጥያቄ፤
ክርስቲያኖች ስለ ኃጢአታቸው ይቅርታን መለመናቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋልን?
መልስ፤
ተደጋጋሚው ጥያቄ፣ “ኃጢአትን ብሠራ እና ከዚያም በኋላ ስለዛ ኃጢአት ለእግዚአብሔር ለመናዘዝ ዕድል ሳላገኝ ብሞት ምን እሆናለሁ?” የሚል ነው። ሌላው የተለመደው ጥያቄ ደግሞ፣ “ኃጢአትን ብሠራና ከዚያም ስለ እርሱ ብረሳ ብሎም ለእግዚአብሔር ለመናዘዝም ፈጽሞ ብረሳው ምን እሆናለሁ?” የሚል ነው። እነዚህ ሁለቱም ጥያቄዎች በተሳሳተ ግምት ላይ ያረፉ ናቸው። ድኅነት/መዳን ማለት አማኞች ስለፈጸሙት እያንዳንዱ ኃጢአት ከመሞታቸው በፊት ለመናዘዝ እና ንስሐ ለመግባት የሚሞክሩበት ጉዳይ አይደለም። ድኅነት የተመሠረተው ክርስቲያን በእያንዳንዱ ኃጢአት ላይ በሚያደርገው ኑዛዜ ወይም ንስሐ ላይ አይደለም። ርግጥ ነው፣ ኃጠአታችንን ለእግዚአብሔር መናዘዝ ይኖርብናል፤ ኃጢአት መሥራታችንን በተገነዘብን ጊዜ። ሆኖም፣ ዘወትር እግዚአብሔርን ይቅርታ መጠየቅ አይኖርብንም። እኛ ለደኅንነት በኢየሱስ ክርስቶስ ላይ እምነታችንን ባኖርን ጊዜ፣ ኃጢአታችን ሁሉ ይቅር ይባልልናል። ይህም ያለፈውን፣ የአሁኑን፣ እና የወደፊቱን፣ ትልቅ ወይም ትንሹን ያካትታል። አማኞች ይቅርታን መጠየቅ ወይም ንስሐ መግባታቸውን መቀጠል አይኖርባቸውም፣ ኃጢአታቸው ይቅር ይባል ዘንድ። ኢየሱስ የሞተው ለኃጢአታችን ሁሉ ያለውን ቅጣት ለመክፈል ነው፣ እናም ይቅር በሚባሉበት ጊዜ፣ ሁሉም ይቅር ተብለዋል (ቆላስይስ 1፡14፤ ሐዋ. 10፡43)።
ማድረግ የሚኖርብን ኃጢአታችንን መናዘዝ ነው፡ “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው” (1 ዮሐንስ 1፡9)። ይህ ቁጥር እንድናደርግ የሚነግረን፣ ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር “እንድንናዘዝ” ነው። “መናዘዝ” የሚለው ቃል “ስምምነት ላይ መድረስ” ማለት ነው። ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር ስንናዘዝ፣ ኃጢአት በመሥራታችን ስሕተተኞች መሆናችንን ከእግዚአብሔር ጋር ተስማማን ማለት ነው። እግዚአብሔር ይቅር ይለናል፣ በንስሐ በኩል፣ ቀጣይነት ባለው መልኩ፣ “የታመነና ጻድቅ” ነው ከሚለው ሀቅ የተነሣ። እግዚአብሔር እንዴት “የታመነና ጻድቅ” ሊሆን ይችላል? እሱ ኃጢአትን ይቅር በማለት የታመነ ነው፣ ክርስቶስን እንደ አዳኝ ለተቀበሉት ሁሉ በገባው ቃል መሠረት። እሱ ጻድቅ ነው፣ ክርስቶስ ስለ ኃጢአታችን የከፈለውን ዋጋ ተግባራዊ በማድረግ፣ ኃጢአት ሁሉ ዋጋ እንደተከፈለበት እውቅና በመስጠት።
በተመሳሳይ ጊዜ፣ 1 ዮሐንስ 1፡9 እንደሚያመለክተው፣ በተወሰነ መልኩ፣ ይቅርታ እኛ ለእግዚአብሔር ኃጢአታችንን በምንናዘዘው ሁኔታ ላይ ይወሰናል። ይህ እንዴት ሊሆን ይችላል፣ ኃጢአታችን ሁሉ ይቅር ከተባለልን በኋላ፣ ክርስቶስን እንደ አዳኝ በተቀበልንበት ቅጽበት? ሐዋርያው ዮሐንስ እዚህ ጋ መግለጽ የሚፈልገው፣ “ተዛማጅነት” ያለውን ይቅርታ ይመስላል። ኃጢአታችን ሁሉ “አቋማዊ” በሆነ መልኩ ይቅር ተብሎልናል፣ ክርስቶስን እንደ አዳኝ በተቀበልንበት ቅጽበት። ይህ አቋማዊ ይቅርታ ለደኅንነታችን ዋስትና ነው፣ ብሎም ዘላለማዊ ቤት በሰማይ ለሚኖረን ተስፋ። ከሞት በኋላ እግዚአብሔር ፊት በምንቆምበት ጊዜ፣ እግዚአብሔር ወደ መንግሥተ ሰማያት እንዳንገባ፣ አያግደንም፣ በኃጢአታችን ምክንያት። ያም አቋማዊ ይቅርታ ነው። የተዛማጅነት ይቅርታ ጽንሰ-ሐሳብ የተመሠረተው፣ ኃጢአትን ስንሠራ እግዚአብሔርን እናስቀይማለን ብሎም መንፈሱን እናሳዝናለን (ኤፌሶን 4፡30)። በመዳረሻውም እግዚአብሔር የሠራነውን ኃጢአት ይቅር ሲለን፣ እነርሱ አሁንም ቢሆን በውጤታቸው ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ሊዘጉት ወይም ሊያጓትቱት ይችላሉ። ወጣት ልጅ ከአባቱ ተቃርኖ ቢፈርም፣ ከቤተሰብ አባልነቱ ውጣ አይባልም። መልካም አባት ልጆቹን ያለ ምንም ቅድመ-ሁኔታ ይቅር ይላል። በተመሳሳይ ጊዜም፣ በአባትና በልጅ መካከል ያለ ግንኙነት፣ ግንኙነቱ እስካልታደሰ ድረስ ሊገኝ አይችልም። ይህም ሊገኝ የሚችለው ልጅየው ለአባቱ ስሕተቱን ሲናዘዝና ይቅርታ ሲያቀርብ ብቻ ነው። በዚህን ምክንያት ነው፣ ለእግዚአብሔር ኃጢአታችንን የምንናዘዘው- ደኅንነታችንን ለማደስ ሳይሆን፣ ነገር ግን ራሳችንን ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ቀረበ ኅብረት ዳግም ለመመለስ፣ እሱም የሚወደንና ቀደም ብሎ ወደ ማረን።
English
ክርስቲያኖች ስለ ኃጢአታቸው ይቅርታን መለመናቸውን መቀጠል ይኖርባቸዋልን?