settings icon
share icon
ጥያቄ፤

መጽሐፍ ቅዱስ አሥራት ስለመስጠት ምን ይላል?

መልስ፤


ብዙ ክርስቲያኖች አሥራትን በመስጠት ጉዳይ ይታገላሉ፡፡ በአንዳንድ አቢያተ-ክርስቲያናት አሥራትን የመስጠት ጉዳይ ከልክ በላይ ጎልቷል፡፡ በተመሳሳይም ብዙ ክርስቲያኖች ስጦታዎችን ለጌታ ማድረግን በተመለከተ ለመጽሐፍ ቅዱሳዊ ማሳሰቢያዎች መገዛትን እምቢ ብለዋል፡፡ አሥራት መስጠት ለሀሴት እና ለመባረክ እንዲሆን በማሰብ ነው፡፡ የሚያሳዝነው ያ አንዳንድ ጊዜ ዛሬ በቤተክርስቲያን ውስጥ ያለ ጉዳይ አይደለም፡፡

አሥራት መስጠት የብሉይ ኪዳን ሀሳብ ነው፡፡ አሥራት ሁሉም እስራኤላውያን ካገኙት ወይም ካፈሩት ለመገናኛው ድንኳን/መቅደስ ከመቶ አሥር እጅ እንዲሰጡ ህጉ የሚጠብቅባቸው ነበር (ኦሪት ዘሌዋውያን 27፤30፤ኦሪት ዘኁልቁ 18፤26፤ ኦሪት ዘዳግም 14፤24፤2ኛ ቆሮንቶስ 31፤5)፡፡ በእርግጥ የብሉይ ኪዳን ህግ ብዙውን ጊዜ በዛሬው ጊዜ የሚሰጠውን ከመቶ አሥር እጅ የሆነውን ሳይሆን ጠቅላላው ቢያንስ ከመቶ ወደ 23.3 እጅ ሊጠጋ የሚችልን በዛ ያለ አሥራት እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ አንዳንዶች የብሉይ ኪዳን አሥራትን መስዋዕት በማድረጉ ሥርዓት ውስጥ የካህናትን እና የሌዋውያንን ፍላጎቶች ለማሟላት የሚሆን የግብር አሰባሰብ ዘዴ እንደሆነ አድርገው ይረዳሉ፡፡ የአዲስ ኪዳን ግን ክርስቲያን ለአሥራት የህግ ሥርዓት መገዛት እንዳለበት በየትም ሥፍራ አያዝም ወይም እንዲሁም አይመክርም፡፡ ጳውሎስ አማኞች ቤተክርስቲያንን ይረዱ ዘንድ የገቢያቸውን ድርሻ ማስቀመጥ እንዳለባቸው ይጠቅሳል (1ኛ ቆሮንቶስ 16፤1-2)፡፡

የአዲስ ኪዳን አንድ ሰው ማስቀመጥ ያለበትን የገቢውን መቶኛ የትም አይደነግግም፤ነገር ግን “ገቢን ማስቀመጥ” ብቻ ይላል (1ኛ ቆሮንቶስ 16፤2)፡፡ በክርስቲያን ቤተክርስቲያን ውስጥ ያሉ አንዳንዶች ከብሉይ ኪዳን አሥራት ከመቶ አሥር እጅ የሚለውን ወስደው ለክርስቲያኖች ለስጦታቸው እንደ “ተወሰነ አነስተኛው” ቁጥር አድርገው ዛሬ ተግባራዊ አድርገዋል፡፡ የአዲስ ኪዳን ስለ መስጠት ጠቃሚነት እና ትርፎች ይናገራል፡፡ እንደምንችለው ልንሰጥ ይገባናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ያ ማለት ከመቶ አሥር እጅ የበለጠ መስጠት፤ አንዳንድ ጊዜ ምናልባት ያነሰ መስጠት ማለት ይሆናል፡፡ ሁሉም በክርስቲያኑ ችሎታ እና የቤተክርስቲያን ፍላጎት ላይ ይመሠረታል፡፡ እያንዳንዱ ክርስቲያን አሥራት በመስጠቱ በሚያደርገው ተሳትፎ ወይም ምን ያህል በመስጠቱ ጉዳይ ተግቶ መጸለይ እና የእግዚአብሔርን ጥበብ ሊፈልግ ይገባል (የያዕቆብ መልዕክት 1፤5)፡፡ ከሁሉም በላይ አሥራቶች እና ስጦታዎች በሙሉ በንጹህ ልብ እና አመለካከት ለእግዚአብሔር በሚደረግ አምልኮ እና ለክርስቶስ አካል አገልግሎት በሚሆን መልኩ መሠጠት አለባቸው፡፡ “እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ይወዳልና እያንዳንዱ በልቡ እንዳሰበ ይስጥ፥ በኀዘን ወይም በግድ አይደለም።” (2ኛ ቆሮንቶስ 9፤7)

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

መጽሐፍ ቅዱስ አሥራት ስለመስጠት ምን ይላል?
© Copyright Got Questions Ministries