settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የክርስቲያን የዓለም አተያይ ምንድነው?

መልስ፤


“የዓለም አተያይ” የሚያመለክተው የተጠቃለለ የዓለም አመለካከትን ከአንድ ተወሰነ አቋም አኳያ ነው። “ክርስቲያን የዓለም አተያይ፣” ማለትም የተጠቃለለ የዓለም አተያይ ከክርስቲያናዊ አቋም ማለት ነው። የአንድ ሰው የዓለም አተያይ የራሱ “ትልቅ ስዕል” ነው፣ ስለ ዓለም ያለው ኅብራዊ እምነቶች ሁሉ። እሱም እውነታን የሚረዳበት መንገዱ ነው። የአንዱ የዓለም አተያይ የየዕለቱን ውሳኔዎቹን የሚሰጥበት መሠረት ነው፣ ስለዚህም እጅግ ጠቃሚ ነው።

ጠረጴዛ ላይ የተቀመጠ አፕል (ፖም) በብዙ ሰዎች ይታያል። የዕጽዋት ተመራማሪ አፕሉን ተመልክቶ ይመድበዋል። አርቲስት ተመልክቶ ሕይወትን ያይበትና ይስለዋል። ባለ ግሮሰሪ ዋጋ ያይበትና ቆጠራ ያደርጋል። ሕፃን ምሳውን ያይና ይበላዋል። ማንኛውንም ሁኔታ እንዴት እንደምንመለከት፣ ዓለምን በግዙፍነቱ በምንመለከትበት መልኩ ተጽዕኖ ያርፍበታል። ማንኛውም ዓይነት የዓለም አተያይ፣ ክርስቲያንም ሆነ ክርስቲያንም አልሆነ፣ ቢያንስ በእነዚህ ጥያቄዎች ዙሪያ ይቃኛል፡

1) ከየት ነው የመጣነው? (እና ለምን እዚሀ ሆንን?”
2) ዓለም ምን ነክቶታል?
3) እንዴት እናጸናዋለን?

ዛሬ የተለመደው የዓለም አተያይ ተፈጥሯዊነት (ናቹራሊዝም) ነው፣ እሱም ሦስቱን ጥያቄዎች እንዲህ የሚመልስ፡ 1) እኛ የተፈጥሮ ዘፈቀዳዊ ድርጊቶች ውጤት ነን፣ ያለ ምንም ርግጠኛ ዓላማ። 2) ተፈጥሮን ማክበር እንደሚገባን አላከበርንም። 3) ዓለምን ማዳን እንችላለን፣ በሥነ-ምኅዳርና በጥበቃ። የተፈጥሯዊነት የዓለም አተያይ በርካታ ተዛማጅ ፍልስፍናዎችን ያስገኛል፣ ለአብነትም የሞራል አንጻራዊነት፣ የኤግዚስተንሻሊዝም፣ ፕራግማቲዝም፣ እና ዩቶፒአኒዝም።

የክርስቲያን የዓለም አተያይ፣ በሌላ በኩል፣ ሦስቱን ጥያቄዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ አኳያ ይመልሳል፡ 1) እኛ የእግዚአብሔር ፍጥረት ነን፣ ዓለምን እንድንገዛ የታቀድንና ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት እንዲኖረን (ዘፍጥረት 1:27-28; 2:15)። 2) በእግዚአብሔር ላይ ኃጢአትን ሠራን፣ እናም ሙሉውን ዓለም በርግማን ላይ ጣልነው (ዘፍጥረት 3)። 3) እግዚአብሔር ራሱ ዓለምን ዋጀ፣ በልጁ በኢየሱስ ክርሰቶስ መሥዋዕትነት (ዘፍጥረት 3:15; ሉቃስ 19:10)፣ እናም አንድ ቀን ፍጥረትን ወደ ቀድሞ ፍጹም አቋሙ ይመልሰዋል (ኢሳይያስ 65:17-25)። ክርስቲያናዊ የዓለም አተያይ እንድናምን ይመራናል፣ በሞራል ፍጽምና፣ ተአምራት፣ ሰብዓዊ ክብር፣ እና መቤዠት ሊኖር እንደሚችል።

የዓለም አተያይ አጠቃላይ እንደሆነ ማስታወስ ጠቃሚ ነው። እሱም የሕይወትን እያንዳንዱን ገጽታ ይነካል፣ ከገንዘብ እስከ ሞራላዊነት፣ ከፖለቲካ እስከ አርት። እውነተኛ ክርስትና በቤተ-ክርስቲያን ከምንጠቀምባቸው የሐሳብ ስብስቦች ይበልጣል። ክርስትና መጽሐፍ ቅዱስ ላይ እንዳለ አስተሳሰብ በራሱ የዓለም አተያይ ነው። መጽሐፍ ቅዱስ “በሃይማኖታዊ” እና “ሃይማኖታዊ ባልሆነ” ሕይወት መካከል ልዩነት አያደርግም፤ ክርስቲያናዊ ሕይወት ነው፣ ያለው ብቸኛው ሕይወት። ኢየሱስ ራሱን ገልጿል፣ “መንገድ፣ እውነት፣ እና ሕይወት” በሚል (ዮሐንስ 14፡6) እና፣ እንደዚያ በማድረግ የእኛ የዓለም አተያይ ሆኗል።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የክርስቲያን የዓለም አተያይ ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries