ጥያቄ፤
የዘፍጥረት ሰዎች ለምን ረጅም ዕድሜ ሊኖሩ ቻሉ?
መልስ፤
በአንድ መልኩም ምሥጢር ይመስላል፣ በዘፍጥረት ፊተኞቹ ምዕራፎች ሰዎች ይሄን ያህል ዕድሜ መኖራቸው። በርካታ ንድፈ-ሐሳቦች በመጽሐፍ ቅዱስ ሊቃውንት ተሰንዝረዋል። ዘፍጥረት 5 ላይ ያለው የዘር ግንድ ዝርዝር የአዳምን መልካም ዝርያዎች አስፍሯል— መሲሑን የሚወልደው የዘር ግንድ። እግዚአብሔር ይሄንን ዘር ባርኮታል፣ በተለየ ረጅም ዕድሜ፣ በመልካምነታቸውና በመታዘዛቸው ምክንያት። ይሄ ታሳቢ ማብራሪያ ሲሆን፣ መጽሐፍ ቅዱስ የትም ስፍራ ቢሆን ረጅም ዕድሜን አልወሰነም፣ ዘፍጥረት ምዕራፍ 5 ላይ ለተጠቀሱት ሰዎች። በተጨማሪም ከሔኖክ በቀር፣ ዘፍጥረት 5 የተለየ መልካምነት ያላቸውን ግለሰቦች አንዳቸውም አልጠቀሰም። ሊሆን የሚችለው በዛ ጊዜና ሰዓት የሚኖረው ሁሉ ብዙ መቶ ዓመት እንደሚኖር ነው። ለዚህም በርካታ ምክንያቶች ሊጠቀሱ ይችላሉ።
ዘፍጥረት1፡6-7 ውኃው እጅግ መነሣቱን ይጠቅሳል፣ ምድርን የሚሸፍን ውኃ። ይህን መሰሉ የውኃ ሽፋን የከባቢ አየር (ግሪን ሀውስ) ተጽእኖ ይፈጥራል፣ እናም አብዛኛውን ጨረር ያግደዋል፣ አሁን ምድር ላይ የሚያርፈውን። ይህም በሕይወት የመቆያውን ሁኔታዎች አስገኘ። ዘፍጥረት 7፡11 የሚያመለክተው በጥፋት ውኃ ጊዜ፣ የውኃው ሽፋን በምድር ላይ ይፈስስ ነበር፣ በሕይወት የመኖርያ ሁኔታዎችን ከፍጻሜ እያደረሰ። ከጥፋት ውኃ በፊት የነበረውን በሕይወት የመቆያ ዘመን (ዘፍጥረት 5፡1-32) ለጥፋት ውኃ ወዲህ ካለው ጋር (ዘፍጥረት 11፡10-32) ጋር አወዳድሩ። ከጥፋት ውኃ በኋላ ወዲያውኑ፣ ዕድሜ ባስገራሚ ሁኔታ ቀንሷል።
ሌላው ግምት ውስጥ የሚገባው ከፍጥረት በኋላ በመጀመሪያዎቹ ጥቂት ትውልዶች፣ የሰዎች የዘር መለያ ላይ ጥቂት ጉድለቶች እየጎለበቱ መጥተዋል። አዳምና ሔዋን ፍጹም ሆነው ነው የተፈጠሩት። እነርሱም በርግጥ በሽታና ሕመምን እጅግ ይቋቋሙ ነበር። የእነርሱ ዝርዮችም እነዚህን ጠቀሜታዎች ወርሰው ነበር፣ ምንም እንኳ በአነሰ መጠን ቢሆንም። ከጊዜ በኋላ፣ በኃጢአት ምክንያት የሰዎች የዘር መለያ ብልሽቱ እየጨመረ መጣ፣ እናም የሰው ልጆች ለሞትና ለበሽታ እጅግ ተጋላጭ ሆኑ። ይህም የሕይወት የመቆያ ጊዜን በከፋ ሁኔታ ቀነሰው።
English
የዘፍጥረት ሰዎች ለምን ረጅም ዕድሜ ሊኖሩ ቻሉ?