settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


መጽሐፍ ቅዱስ ፍቅርን እንዴት እንደሚገልጸው እንመልከት፣ ከዚያም በኋላ እግዚአብሔር የፍቅር መገለጫ የሆነባቸውን ጥቂት መንገዶች እንመለከታለን። “ፍቅር ይታገሣል፥ ቸርነትንም ያደርጋል፤ ፍቅር አይቀናም፤ ፍቅር አይመካም፥ አይታበይም፤ የማይገባውን አያደርግም፥ የራሱንም አይፈልግም፥ አይበሳጭም፥ በደልን አይቆጥርም፤ ከእውነት ጋር ደስ ይለዋል እንጂ ስለ ዓመፃ ደስ አይለውም፤ ሁሉን ይታገሣል፥ ሁሉን ያምናል፥ ሁሉን ተስፋ ያደርጋል፥ በሁሉ ይጸናል። ፍቅር ለዘወትር አይወድቅም” (1ኛ ቆሮንቶስ 13፡4-8ሀ)፣ ይህ የእግዚአብሔር የፍቅር መግለጫ ነው፣ እናም፣ ምክንያቱን እግዚአብሔር ፍቅር ስለሆነ (1ኛ ዮሐንስ 4፡8)፣ እሱ ይሄን ነው የሚመስለው።

ፍቅር (እግዚአብሔር) በማንም ላይ ግዴታ አያደርግም። ወደ እሱ የሚመጡትም በእሱ ፍቅር ምላሽ እንደሱ ያደርጋሉ። ፍቅር (እግዚአብሔር) ለሁሉም ፍቅሩን ያሳያል። ፍቅር (ኢየሱስ) በወጣበት ሁሉ ያለ ምንም ልዩነት ለሁሉም መልካም ያደርግ ነበር። ፍቅር (ኢየሱስ) የሌሎችን አይመኝም ነበር፣ የትሕትና ሕይወትን ያለ ምንም ማጉረምረም ይኖር ነበር። ፍቅር (ኢየሱስ) ስለ ራሱ አልተመካም፣ በሥጋ በነበረበት ሰዓት፣ ምንም እንኳ የሚገናኘውን ሁሉ በኃይል በላጭነት ቢኖረውም። ፍቅር (እግዚአብሔር) ታዛዥነትን አይጠይቅም። እግዚአብሔር ታዛዥነትን ከልጁ አልጠየቀም፣ ነገር ግን ኢየሱስ በፍቃዱ በሰማይ የሚኖር አባቱን ታዘዘ። “ነገር ግን አብን እንድወድ ዓለም ሊያውቅ አብም እንዳዘዘኝ እንዲሁ አደርጋለሁ” (ዮሐንስ 14፡31)። ፍቅር (ኢየሱስ) ዘወትር የሚመለከተው ከሌሎች ፍላጎት አኳያ ነበር/ነው።

ታላቁ የእግዚአብሔር የፍቅር መግለጫ ለእኛ የተደረገው በዮሐንስ 3፡16 ነው፡ “በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ሕይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለሙን እንዲሁ ወዶአልና።” ሮሜ 5፡8 ተመሳሳይ መልዕክት ያቀርባል፡ “ነገር ግን ገና ኃጢአተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለ እኛ ሞቶአልና እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።” ከእነዚህ ቁጥሮች ለማየት የምንችለው በሰማያዊ ቤቱ፣ በመንግሥተ ሰማያት ከእሱ ጋር እንድንሆን የእግዚአብሔር ታላቅ ፍላጎቱ መሆኑን ነው። እሱም መንገዱን የሚቻል አድርጎታል፣ የኃጢአታችንን ዋጋ በመክፈል። እሱ ወድዶናል ምክንያቱም ይህን እንደ ፍቃዱ ድርጊት ስለመረጠ። ፍቅር ይቅርታ ያደርጋል። “በኃጢአታችን ብንናዘዝ ኃጢአታችንን ይቅር ሊለን ከዓመፃም ሁሉ ሊያነጻን የታመነና ጻድቅ ነው” (1ኛ ዮሐንስ 1፡9)።

ስለዚህ፣ እግዚአብሔር ፍቅር ነው ማለት ምን ማለት ነው? ፍቅር የእግዚአብሔር ድርሻ ነው። ፍቅር የእግዚአብሔር ባሕርይ ዋነኛው ገጽታ ነው፣ የማንነቱ። የእግዚአብሔር ፍቅር ከእሱ ቅድስና፣ ጽድቅ፣ ፍትሓዊነት፣ ወይም ከእሱ ቁጣ ጋር እንኳ ቢሆን በምንም መልኩ አይቃረንም። ሞላው የእግዚአብሔር ባሕርያት በፍጹም ኅብር ናቸው። እግዚአብሔር የሠራው ሁሉ ፍቅር ነው፣ እሱ ያደረገው ነገር ሁሉ ትክክልና ቀጥተኛ እንደሆነ ሁሉ። እግዚአብሔር የእውነተኛ ፍቅር የፍጹም ምሳሌ ነው። በሚያስደንቅ መልኩ፣ እግዚአብሔር ልጁን ኢየሱስን እንደ ግል አዳኛቸው ለተቀበሉት፣ እሱ እንዳደረገው ሁሉ የማፍቀር ችሎታን በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በኩል ይሰጣቸዋል (ዮሐንስ 1፡12፤ 1ኛ ዮሐንስ 3፡1፣ 23-24)።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ፍቅር ነው ማለት ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries