settings icon
share icon
ጥያቄ፤

እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው ወይም ክርስቲያኖችን በቻ ይወዳል?

መልስ፤


እግዚአብሔር በዓለም ሁሉ ያለውን እያንዳንዱን ሰው የሚወድበት ስሜት አለ (ዮሐንስ 3:16; 1 ኛ ዮሐንስ 2: 2; ሮሜ 5 8)፡፡ ይህ ፍቅር ተለዋዋጭ አይደለም፤ በእግዚአብሔረ ባህርይ ላይ የተመሠረተ ነው በእርሱ በፍቅር ላይ የተመሠረተ ነው (1 ዮሐንስ 4 8, 16)፡፡ እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው ያለው ፍቅር እንደ "በምህረት የሞላ ፍቅሩ" ሊታሰብ ይችላል፤ ይህም እግዚአብሔር ሰዎችን ለኃጢአታቸው ወዲያውኑ አያቀጣቸውም (ሮሜ 3 23; 6 23)፡፡ ‹‹በሰማያት ያለው አባታችሁ. . . በክፉውና በጥሩ ሰዎች ላይ ፀሐይን ያወጣልና በጻድቃንና በኃጢአተኞችም ላይ ዝናቡን ያዘንባል››(ማቴዎስ 5፡45)፡፡ ይህ ሌላው እግዚአብሔር ለሁለም ያለው ፍቅር ነው፡፡ ርኅራሄው ፍቅር፤ደግነቱ ለክርስቲያኖች ብቻ ሳይሆን ለሁሉም ነው፡፡

እግዚአብሔር ለዓለም ያለው መሐሪ ፍቅር ለሰዎችም ንስሐ እንዲገቡ እድል በመስጠቱም ተገልጾአል፡- ‹‹ለአንዳንዶች የሚዘገይ እንደሚመስላቸው ጌታ ስለ ተስፋ ቃሉ አይዘገይም፥ ነገር ግን ሁሉ ወደ ንስሐ እንዲደርሱ እንጂ ማንም እንዳይጠፋ ወዶ ስለ እናንተ ይታገሣል።›› (2 ጴጥሮስ 3፡9) እንዲሁ የሚወደው የእግዚአብሔር ፍቅር እርሱ ሰውን ሁሉ ወደ ደህንነት ከጠራበት ጥሪው ጋር አብሮ የሚሄድ ሲሆን ይህም ዘወትር የእርሱን ዝንባሌ ፍጡም ፈቃድ የሚገልጥ እና እርሱን ደስ የሚያሰኝ የሆነውን የሚገልፅ ነው፡፡

ይሁን እንጂ እግዚአብሔር ለሁሉም ሰው ባለው ፍቅር ሁሉም ሰው ይድናል ማለት አይደለም (ማቴዎስ 25:46 ተመልከቱ)፡፡ እግዚአብሔር ኃጢያትን ቸል ሊለው አይችልም፤ እግዚአብሔር የፍትህ አምላክ ነውና (2 ተሰሎንቄ 1፡6)፡፡ ኃጢአት ለዘላለም ሳይቀጣ ሊቀር አይችልም (ሮሜ 3፡25-26)፡፡እግዚአብሔር ኃጢአትን ችላ ብሎ ዝም ብሎ ለዘላለም እንዲቀጥል ከፈቀደ እርሱ ፍቅር አይኖረውም፡፡ የእግዚአብሄር በምህረት የተሞላ ፍቅር ችላ ማለቱ, ክርስቶስን አለመቀበል ወይም የተቤዘዠንን አዳኝ መካድ (2 ኛ ጴጥሮስ 2፡1) ወደ ዘለአለማዊው የእግዚአብሔር ቁጣ መገባት ነው (ሮሜ 1 18) እንጂ የእርሱ ፍቅር አይደለም፡፡

ኃጢአተኞች ማጽደቅ የሚያስተምረው የእግዚአብሔር ፍቅር ለሁሉም ሰው አይደለም በኢየሱስ ክርስቶስ ለሚያምኑ ብቻ ነው (ሮሜ 5፡1)፡፡ ሰዎች ከእግዚአብሔር ጋር ወደ ወዳጅነት ቅርርብ እንዲመጡ የሚያደርጋቸው የእግዚአብሔር ፍቅር ለሁሉም ልጆች ሳይሆን የእግዚአብሔርን ልጅ ለሚወዱ ብቻ ነው (ዮሐ 14፡21). ይህ ፍቅር እንደ እግዚአብሔር "ቃልኪዳን ፍቅር" ተደርጎ ሊወሰድ ይችላል እና በሁኔታዎች ላይ የተመሠረተ ነው ይህም የሚሰጠውም ለደህንነታቸው በኢየሱስ ለሚያምኑ ብቻ ነው (ዮሐ. 3 36)፡፡ በጌታ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ ሁልጊዜ የተወደደ ናቸው ደህንነታቸው ለዘላለም ይጠበቃል፡፡

አምላክ ሁሉንም ይወዳል? አዎን፤ ለሁሉም ርኅራኄና ደግነት ያሳያቸዋል፡፡ እግዚአብሔር ክርስቲያኖች ክርስቲያኖች ካልሆኑት በላይ ይወዳል? አይ፤ እንደ ምህረት እንደሞላበት ፍቅሩ የሚታይ አይደለም፡፡እግዚአብሔር በተለየ መንገድ ክርስቲያኖች ከማያምኑ ሰዎች ይልቅ ይወዳል? አዎ፤ አማኞች በእግዚአብሔር ልጅ ላይ እምነት አላቸው፤ የዳኑ ናቸው፡፡ እግዚአብሔር ከክርስቲያኖች ጋር ልዩ ግንኙነት አለው ምክንያቱም በእግዚአብሔር ዘላለማዊ ጸጋ መሰረት ይቅር የተባሉት ክርስቲያኖች ብቻ ናቸው፡፡ አምላክ ያለ ምንም ቅድመ ሁኔታ መሐሪ የሆነ ፍቅር ወደ በእግዚያብሄር ወደ ማመን ሊመራን ይገባል፤ በአገባቡ ኪዳናዊ ፍቅርን ኢየሱስ ክርስቶስን አዳኝ አድርገው ለተቀበሉት ሰጥቶአቸዋል፡፡

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

እግዚአብሔር ሁሉንም ሰው ወይም ክርስቲያኖችን በቻ ይወዳል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries