ጥያቄ፤
እግዚአብሔር እስራኤልን የእርሱ ህዝብ አድረጎ መረጦአል?
መልስ፤
ስለ እስራኤል ህዝብ በቃሉ በዘዳ 7፡7-9 ሲናገር፡- ‹‹ እግዚአብሔርም የወደዳችሁና የመረጣችሁ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ስለ በዛችሁ አይደለም እናንተ ከአሕዛብ ሁሉ በቍጥር ጥቂቶች ነበራችሁናነገር ግን እግዚአብሔር ስለ ወደዳችሁ ለአባቶቻችሁም የማለላቸውን መሐላ ስለ ጠበቀ፥ ስለዚህ እግዚአብሔር በጽኑ እጅ አወጣችሁ፥ ከባርነትም ቤት ከግብፅ ንጉሥ ከፈርዖን እጅ አዳናችሁ።አንተም አምላክህ እግዚአብሔር እርሱ አምላክ እንደ ሆነ፥ ለሚወድዱትም ትእዛዙንም ለሚጠብቁ ቃል ኪዳኑንና ምሕረቱን እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ የሚጠብቅ የታመነ አምላክ እንደ ሆነ እወቅ››
እግአብሔር የእስራኤል ህዝብ እግዚአብሔር ከኃጢያትና ከሞት ለማዳን ኢየሱስ ክርስቶስ የሚወለድበት ህዝብ እንዲሆኑ መረጠ (ዮሐ 3፡16)፡፡ እግዚአብሔር ስለ መሲሁ አዳምና ሔዋን በኃጢያት ከወደቁ በኋላ ተሰፋን ሰጠ (ዘፍ ምዕራፍ 3)፡፡ ከዛ በኋላ መሲሁ በአብርሃም ይሳሐ እና በያዕቆብ ዘር እንደሚወለድ ተናገረ (ዘፍ 12:1-3)፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እስራኤላዊያን የእረሱ ህዝብ እንዲሆኑ የመረጠበት ትልቁ ምክንያት ነው፡፡ እግዚአብሔር ህዝብ መመረጥ አያስፈልገውም ነገር ግን በዛ መንገድ ማድረግ ፈለገ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ከአንድ ህዝብ መምጣት ነበረበት ስለዚህ እስራኤልን መረጠ፡፡
የሆነው ሆኖ እግዚአብሔር እስራኤልን የመረጠበት ምክንያት መሲሁ እንዲወለድበት ብቻ አይደለም፡፡ እግዚአብሔር ለእስራኤል የነበረው አላማ ስለ እርሱ ወደ ሌሎች ሄደው እንዲናገሩ ነው፡፡ እስራኤላዊያን የእርሱ የካህናት መንግስት ነብይ እና ለአለም መልዕክተኛ እንዲሆኑ ነበር፡፡ የእግዚአብሔር እቅድ ለእስራኤል የተለየ ህዝብ እንዲሆኑ ነበር ፤ ሌሎችን ወደ እግዚአብሔር የሚጠቁሙ ወዳዘጋጀው የመዋጀት ስራ ወደ መሲሁ እና ወደ አዳኙ ነው፡፡ በአብዛኛው ክፍል እስራኤል በዚህ ስራ ወድቃለች፡፡ ሆኖም እግዚአብሔር ለእስራኤል ያለው አላማ፤ መሲሁን ወደ አለም ማምጣት በኢየሱስ ክርስቶስ በትክክል በኢየሱስ ክርስቶስ ተፈጽሞአል፡፡
English
እግዚአብሔር እስራኤልን የእርሱ ህዝብ አድረጎ መረጦአል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?