ጥያቄ፤
የይህዋ ምስክሮች እነማን ናቸው? ምንድን ነው የሚያምኑት?
መልስ፤
አሁን የይህዋ ምስክሮች በመባል የሚታወቀው ክፍል የተጀመረው በፔንሲልቫኒያ በ1870 በቻርሰስ ታዝ ሩስል እንደ የመጽሐፍ ቅዱስ ትምህርት ክፍል ውስጥ ነበር፡፡ ሩስል ቡድኑን ‹‹ሚሊኒያል ዳውን መጽሐፍ ቅዱስ ጥናት›› ብሎ ነው የሚጠራው፡፡ ቻርሰስ ታዝ ሩስል ሚሊኒያል ዳውን የተሰኘ ተከታታይ ክፍል ያለው መጽሐፍ ጀመረ፡ ከመሞቱ በፊት የጻፈው እስከ ስድስተኛ ክፍል የደረሰ ሲሆን አብዛኛው አሁን የየህዋ ምስክሮች ያላቸውን ስነመለኮት የያዘ ነው፡፡ ሩስል ከሞተ በኃላ በ1916 ዳኛ የነበረ ጄ ኤፍ ሩተርፎርድ የሩሰል ጓደኛ እና እርሱን ተከትሎ የተካው ሰባቱን እና የመጨረሻውን የሚሊኒያል ዳውን ተከታታይ ጥራዝ ‹‹ያለቀው ምስጢር›› ""The Finished Mystery"" በ1917 ጻፈ፡፡ የመጠበቂያ ግንብ የመጽሐፍ ቅዱስና የትራክት ማህበር በ1886 ተመሰረተ እናም በፍጥነት የሚሊኒያል ዳውን እንቅስቃሴ እግር በመሆኑ ሃሳባቸውን ለሌሎች ማከፈል ጀመሩ፡፡ ቡድኑ እስከ 1931 ሩሰሊስት በመባል ይታወቅ ነበር በድርጅቱ ውስጥ በደረሰው መከፋፈል እንደገና የይህዋ ምስክር “Jehovah’s Witnesses.” የተባለ ስም ተሰጠው፡፡ ተከፍሎ የቀረው ቡድን የመጽሐፍ ቅዱስ ተማሪዎች “Bible students.”ተብሎ ታወቀ፡፡
የይህዋ ምስክሮች የሚያምኑት ምንድን ነው? ቀርበን የአስተምህሮአቸውን ደረጃ በጥልቀት ስንፈትሸው በእነዚህ ትምህርት አይነቶች ስለ ክርስቶስ መለኮትነት ድኅነት ስላሴ መንፈስ ቅዱስ እና የክርስቶስ መስወዕትነት የሚያሳዩት ከጥርጣሬ በላይ በእነዚህ ርዕሶች ያልተቃወሰ ቀጥተኛ የክርስቲያኖችን አቋም አልያዙም፡፡ የይህዋ ምስክሮች ኢየሱስ ከተፈጠሩ አካላት መካከል ትልቅ ስፍራ ያለው ሚካኤል ነው ብለው ያምናሉ፡፡ ይህ ኢየሱስ መለኮት እንደሆነ በግልጥ ከሚናገሩ ከብዙ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር ይጋጫል (ዮሐ 1:1,14, 8:58, 10:30). የይህዋ ምስክሮች ደህንነት በእምነት በመልካም ስራ እና በመታዘዝ በአንድነት የሚገኝ እንደሆነ ያምናሉ፡፡ ይህ ከቁጥር በላይ ከሆኑ ደህንነት በጸጋ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በእምነት እንደሆነ ከሚናገሩ የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍሎች ጋር አይስማማም (ዮሐ 3:16; ኤፌ 2:8-9; ቲቶ 3:5). የይህዋ ምስክሮች ስላሴን ይቃወማሉ፤ ኢየሱስ የተፈጠረ እንደሆነ እና ስለ መንፈስ ቅዱስ በመሰረቱ የእግዚአብሔር ግዑዝ ኃይል እንደሆነ ያምናሉ፡፡ የይህዋ ምስክሮች የክርስቶስን የምትክነት መስዋዕት ሃሳብ ይቃወማሉ እና የቤዛነትን ንድፈ ሃሳብ ይልቅ የኢየሱስ ክርስቶስ ሞት ለአዳም ኃጢያት የተከፈለ ክፍያ ነው ይላሉ፡፡
የይህዋ ምስክሮች እንዴት ነው ይህን መጽሐፍ ቅዱሳዊ ያልሆነ እስተምህሮ ለማረጋገጥ የሚሞክሩት? በመጀመሪያ ቤተክርስቲያን ለዘመናት መጽሐፍ ቅዱስ የተዛባ እንዲሆን አድርጋለች ይላሉ፡፡ ከዛም መጽሐፍ ቅዱስን እነርሱ ኒው ወርልድ ትራንስሌሽን /World Translation/ ብለው ወደ ሚጠሩት ተረጎሙት፡፡ የዋች ታወር መጽሐፍ ቅዱስ እና ትራክት ማህበር የመጸሐፍ ቅሱስ ክፍሎቹን መጽሐፍ ቅዱስ በትክክል እንደሚያስተምረው አስተምህሮአቸውን መሰረት ከማስያዝ ይልቅ ለሐሰተኛ ትምህርታቸው እንደሚሰማማ አድርጎ አስተካከለው፡፡ ኒው ወርልድ ትራንስሌሽን በዙ ጊዜ የይህዋ ምስክሮች ከአስተምሮአቸው ጋር የማይስማማ ክፍል ባገኙ ቁጥር በዙ ጊዜ ለህትመት በቅቶአል፡፡
የይህዋ ምስክሮች አስተምህሮአቸውንና እምነታቸውን የመሰረቱት በቻርለስ ታዛ ሩሰል እና እርሱን በተካው በዳኛው ጆሴፍ ፈራክሊን ሩተርፎርድ በመጀመሪያው እና እንደ ገና ተስፋፍቶ በተጻፋ ትምህርት ላይ ነው፡፡ የዋችታወር የመጽሐፍ ቅዱስ እና ተራክት ማህበር የስልጣን አካል በኑፋቄ ትምህሩቱ ውስጥ መጽሐፍ ቅዱሳቸውን የመተሮጎም ስልጣን ያለው በቸኛው አካል ነው፡፡ በሌላ አባባል ይህ የስልጣን አካል በየትኛውም የመጽሐፉ ክፍል ላይ የሚለው እንደ መጨረሻው ቃል ይታያል እናም ከዚህ ሌላ ተቀጽላ ሃሳብ ፈጽሞ አይበረታታም፡፡ ይህ ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ ከሰጠው ተግሳጽ ጋር ቀጥተኛ መቃወም አለው(ለእኛም እንዲሁ) ስናጠና በእግዚአብሐር ተቀባይነትን ለማግኘት ይሆንና የእግዚአብሔርንም ቃል በትክክል በመያዛችን አናፍርም፡፡ ይህ ተግሳጽ 2ኛ ጢሞ 2፡15 ከእግዚአብሔር ግልጽ መመሪያ ሲሆን ሁለም ልጆቹ እንደ ቤሪያ ሰዎች በየዕለቱ የሚማሩት የእግዚአብሔርን ቃል ትምህርት ከቃሉ ጋር የሚስማማ እንደሆነ መመርመር አለባቸው፡፡
ምናልባት መልዕክታቸውን ለምስክርነት ይዞ ለመውጣት ባለ ታማኝነት እንደ ይህዋ ምስክሮች ያለ የኃይማኖት ተቋም የለም፡፡ ባልተጠበቀ መልኩ ግን መልዕክቱ የተዛባ የተጭበረበረ እና የሐሰት ትምህርት ነው፡፡ እግዚአብሔር የይህዋ ምስክሮችን አይን ለወንጌል እውነት ለእውነተኛው የእግዚአብሔር ቃል ትምህርት ይክፈት፡፡
English
የይህዋ ምስክሮች እነማን ናቸው? ምንድን ነው የሚያምኑት?