settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የማቲዎስ እና የሉቃስ የኢየሱስ ክርስቶስ የዘር ሃረግ ለምን ይለያያል?

መልስ፤


የኢየሱስ ክርስቶስ የዘር ሃረግ በቃሉ ውስጥ በሁለት ስፍራ ተጠቅሶአል፡ ማቲ 1 እና ሉቃ 3፡23-38፡፡ ማቲዎስ የዘር ሃረጉን ከኢየሱስ በማንሳት እስከ አብርሃም ያስቀምጣል፡፡ ሉቃስ የዘር ሃረጉን ከኢየሱስ እስከ አዳም ይጠቅሳል፡፡ ይሁን እንጂ ማቲዎስ እና ሉቃስ የተለያየ የዘር ሃረግ እንደጠቀሱ ለማማመን በእርግጥ ጥሩ ማስረጃ አለ፡፡ ለምሳሌ ማቲዎስ የዮሴፍ አባት ያእቆብ እንደሆነ ይጠቅሳል (ማቲ1፡16)፣ ሆኖም የዮሴፍ አባት ኤሌ እንደሆነ ይጠቅሳል (ሉቃ 3፡23)፡፡ ማቲዎስ መስመሩን ሲያስቀምጥ በዳዊት ልጅ በሰለሞን በኩል ነው (ማቲ 1፡6) ሉቃስ መስመሩን በዳዊት ልጅ በናታን ይጠቅሳል (ሉቃ 3፡31)፡፡ እውነት ነው በዳዊት እና በኢየሱስ የዘር ሃረግ አንድ በጋራ የተጠቀሱ ስሞች ቢኖሩ ሰላትያልዘሩባቤል ናቸው (ማቲ 1፡12፤ ሉቃ 3፡27)፡፡

አንዳንዶች እነዚህን ልዩነቶች በመጽሐፍ ቅዱስ ያሉ ስህተቶች አድርገው ይገልጻሉ፡፡ ሆኖም ግን አይሁዶች ጠንቃቃ መረጃ ጠባቂዎች ናቸው በተለይ ደግሞ በዘር ሃረግ፡፡ ማቲዎስ እና ሉቃስ በአንድ የዘር ሀረግ ላይ ሁለት ሙሉ በመሉ የሚጋጩ የዘር ሃረግ ይገነባሉ ብሎ ማለት የማይታመን ነው፡፡ እንደገና ከዳዊት እስከ ኢየሱስ የተዘር ሃረጉ ፈጽሞ የተለየ ነው፡፡ የሰላትያል እና የዘሩባቤል የተጠቀሰው እንዲሁ የተለያዩ ግለሰቦች በአንድ አይነት ስሞች ያመለክት ይሆናል፡፡ ማቲዎስ የሳላቲያል አባት ኢኮንያን በሎ ሲጠቅስ ሉቃስ የሳላቲያልን አባት የኔሪ ነው ይላል፡፡ የተለመደ ሊሆን ይችላል ሳላቲያል ተብሎ የሚጠራን ሰው ልጁን ታዋቂ በሆነ ሰው ስም ዘሩባቤል ብሎ መጥራት (ይህንን በዕዝራና በነህሚያ መጽሐፍ ተመልከቱ)፡፡ አንዱ ኢሱቢያስ በተባለ የቤተክርስቲያን ታሪክ አዋቂ የሚሰጥ ገለጻ ምንድን ነው ማቲዎስ የጠቀሰው የቀደመውን ሳይንሳዊ ባዮሎጂካል የዘር ሃረግ ሲሆን ሉቃስ ለማረጋገጫነት የወሰደው መረጃ በብሉይ ኪዳን ወንድሙ ሲሞት ለወንድሙ ዘር ለማስቀረት የወንድሙን ሚስት መበለቷን የሚያገባበትን፡፡ እንደ ኢሱቢያስ አመለካከት ሚልኪ (ሉቃ 3፡24) እና ማታን (ማቲ 1፡15) በተለያየ ጊዜ አንዲትን ሴት አግብተው ነበር (በባህላዊ ስም ኢሽታ)፡፡ ይህ ኤሊ (ሉቃ 3፡23) እና ያዕቆብ (ማቲ 1፡15) በግማሽ ወንድሙ ያደርገዋል፡፡ ኤሊ ያለ ልጅ ሞተ እና የእርሱ በግማሽ ወንድሙ የሆነው ያዕቆብ መበለት የሆነችውን የወንድሙን ሚስት አግብቶ ዮሴፍ እንደወለድ አደረገ፡፡ ይህ ደግሞ የሴፍን ‹‹የኤሊን ለጅ›› በህግ እንዲሁም በተፈጥሮ ህግ ‹‹ያዕቆብ ልጅ›› ያደርገዋል፡፡ እንግዲያውስ ማቲዎስና ሉቃስ የሚጠቅሱት ተመሳሳይ የዘር ሃረግ ነው (ዮሴፍ) ግን ሉቃስ የተከተለው ህጋዊውን የዘር ሃረግ ነው ግን ማቲዎስ የተከተለው ተፍጥሮአዊው ባዮሎጂካሊ ነው፡፡

ብዙ አጥባቂዎች የመጽሐፍ ቅዱስ አዋቂዎች የተለያዩ አመለካከቶች አሉአቸው ሲጠቅሱም ሉቃስ የማሪያምን የዘር ሃረግ ነው የጠቀሰው ማቲዎስ የዮሴፍን ነው ይላሉ፡፡ ማቲዎስ የተከተለው የዮሴፍን የዘር ሃረግ ነው (የኢየሱስ ክርስቶስ ህጋዊ አባት) በዳዊት ልጅ በሰለሞን በኩል፤ ግን ሉቃስ የተከተለው የማሪያምን የዘር ሃረግ ነው (የኢየሱስ የደም ሃረግ) የዳዊት ልጅ ናታን፡፡ በግሪክ አማች የልጅ ባል “son-in-law,” ለሚለው የግሪክ ቃል ስለሌለ ዮሴፍ ‹‹የኤሌ ልጅ›› ተበሎ ይጠራ ነበር ለማሪያም በጋብቻ፤ የኤሊ ልጅ፡፡ በማሪያምም ሆነ በዮሴፍ የዘር ሃረግ ኢየሱስ የዳዊት ዘር ነው፤ መስህ ተብሎም ሊጠራ ይገባዋል፡፡ የዘር ሃረግን በእናት በኩል መጥቀስ የተለመደ አይደለም፤ ግን ድንግል ስትወልድ ግን ሆኖ ነበር፡፡ የሉቃስ ገለጻ ኢየሱስ የዮሴፍ ልጅ እንደነበር ነው፡፡ ‹‹ሃሳቡም ይህው ነበር›› (ሉቃ 3፡23)፡፡ English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የማቲዎስ እና የሉቃስ የኢየሱስ ክርስቶስ የዘር ሃረግ ለምን ይለያያል? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries