settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ አግብቶ ነበር?

መልስ፤


ኢየሱስ ክርስቶስ በእርግጠኝነት አላገባም፡፡ የታወቁ የፈጠራ ወሬዎች በአሁን ጊዜ ኢየሱስ ክርስቶስ መግደላዊት ማሪያምን አግብቶ እንደነበር ይናገራሉ፡፡ ይህ አፈ ታሪክ በእርግጠኝነት የተሳሳተ እና በስነመለኮት በታሪክ መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሰረት ምንም መሰረት የለውም፡፡ ሆኖም አንዳንድ የኖስቲክ ወንጌላት ኢየሱስ የቀረበ ግንኙን ከመግደላዊት ማሪያም ጋር እንደነበረው ይናገራሉ፤ የትኞቹም በግልጽ ኢየሱስ ክርስቶስ ከመግደላዊት ማሪያም ጋር በግልጽ የተለየ ግንኙነት እንደነበረው አይናገሩም ውይንም የፍቅር ግንኙነት እንደነበረው አይናገሩም፡፡ ከየትኞቹም የሚቀራረበው ኢየሱስ ክርስቶስ መግደላዊት ማሪያምን ስሟታል የሚል ነው፤ ይህም ደግሞ በቀላሉ የጓደኝነት መሳም ሊሆን የሚችል ነው፡፡ በተጨማሪም የኖስቲክ ወንጌል ኢየሱስ ክርስቶስ መግደላዊት ማሪያምን እንዳገባ ቢናገሩም ምንም ስልጣን የላቸውም የኖስቲክ ወንጌላት የኢየሱስ ክርስቶስ የኖስቲክ አመለካከቶችን ለመፍጠር የማስመሰል ስራዎች መሆናቸው በመረጋገጡ፡፡

ኢየሱስ አግብቶ በሆን ኖሮ፤ መጽሐፍ ቅዱስ እንደዛ ብሎ ይነግረን ነበር ወይንም ወይንም ሌሎች አጠራጣሪ አረፍተ ነገሮች እውነቱን ለማረጋገጥ ይኖሩ ነበር፡፡ ቃሉ እንደዚህ ባለ ዋና ነገር ላይ ሙሉ ሉሙሉ ዝም ሊል አይችልም ነበር፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን እናት አሳዳጊ አባቱን በግማሽ ወንድሞቹ እንዲሁም በግማሽ እህቶቹንይጠቅሳል፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ኢየሱስ ክርስቶስ ሚስት እንደ ነበረው እንዴት ላይጠቅስ ይችላል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እንዳገባ የሚያምኑ እና የሚያስተምሩ ኢየሱስን ወደ ሰውነት የበለጠ ለማስጠጋት እየሞከሩ ነው፤ እርሱን የበለጠ ተራ ለማድረግ እንደማንኛውም አይነት ሰው ለማድረግ፡፡ ሰዎች ሲየሱስ ክርስቶስ በስጋ የተገለጠ እግዚአብሔር እንደሆን ማመን አይፈልጉም (ዮሐ 1፡1፤ 14፤ 10፡30)፡፡ ስለዚህ ኢየሱስ ክርስቶስ አግብቶ እንደነበር ልጆች እንደነበሩት እና አንድ ተራ ሰው እንደነበር የፈጠራ ታሪኮችን ይፈጥራሉ ያምናሉ፡፡

ሊላኛው አላስፈላጊ ጥያቄ ሊሆን የሚችለው ‹‹ኢየሱስ ክርስቶስ ሊያገባ ይችላል?›› በማግባት ምንም አይነት ኃጢያት የለም፡፡ በጋብቻ ውስጥ የግብረ ስጋ ግንኙነት መፈጸም ምንም ችግር የለውም፡፡ ስለዚህ አዎን ኢየሱስ ሊያገባ ይችል ነበር እና ግን ምንጊዜም ኃጢያት የሌለበት በግ እና የአለም አዳኝ ነው፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ምንም አይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ ምክንያት ኢየሱስ እንዲያገባ የለም፡፡ በዚህ ክርክር ነጥቡ ይህ አይደለም፡፡ ኢየሱስ እንዳገባ የሚያምኑ ኃጢያት እንደሌለበት አያምኑም ወይንም መስህ እንደሆነ፡፡ እግዚአብሔር የላከው ለማግባት እና ልጆችን ለመውለድ አይደለም፡፡ ማር 10፡45 ኢየሱስ ለምን እንደመጣ ይነግረናል፡ ‹‹እንዲሁ የሰው ልጅም ሊያገለግልና ነፍሱን ለብዙዎች ቤዛ ሊሰጥ እንጂ እንዲያገለግሉት አልመጣም።››

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

ኢየሱስ አግብቶ ነበር? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries