ጥያቄ፤
ኢየሱስ መለኮት ቢሆን ኖሮ እንዴት ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር? ኢየሱስ ለራሱ ነበር የሚጸልየው?
መልስ፤
ኢየሱስ መለኮት ሆኖ ወደ ሰማይ አባቱ የጸለየውን ለመረዳት ዘላለማዊ አባቱ እና የዘለአለም ለጁ ኢየሱስ ሰው ከሞሆኑ በፊት ዘላለማዊ ግንኙነት እንዳላቸው ማስተዋል አልብን፡፡ እባካችሁን ዮሐ 5፡19-27 አንብቡት በተለይም ቁ. 23 ኢየሱስ አባት ልጁን እንደላከው የሚያስተምርበት (እንደሁም ዮሐ 5፡10 ተመልከቱ)፡፡ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ልጅ የሆነው በቤተልሄም ሲወለድ አይደለም፡፡ እርሱ ከዘልአለም የእግዚአብሔር ልጅ ነበር፤ አሁንም የእግዚአብሔር ልጅ ነው ሁሉገዜም እንደዚሁ ነው፡፡
ኢሳ 9፡6 ወንድ ልጅ ተሰጥቶናል እና እጻን ተወልዶአል ሲል ይነገርናል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ሁልጊዜም በስላሴ አካል አንድነት ውስጥ ነበር፤ ከመንፈስ ቅዱስ ጋር፡፡ ሶስትነት ሁልጊዜም ይኖራል፤ እግዚአብሔር አባት ልጁ አማላክ እና መንፈስ ቅዱስ አምላክ አማልክቶች አይደለም፤ ግን አንድ እግዚአብሔር አለ በሶስት አካል ይኖራል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ እና እግዚአብሔር አንድ እንደሆኑ አስተምሮአል (ዮሐ 10፡30) እርሱ እና እግዚአብሔር አንድ አይነት የማንነት ይዘት እና አካል አላቸው፡፡ አባት ልጅ እና መንፈስ ቅዱስ ሶስቱም በእኩል አካል በእግዚአብሔርነት ይኖራሉ፡፡ እነዚህ ሶስቱ ዘላለማዊ ግንኙነት ነበራቸው አላቸው እንዳለቸው ለዘለአለም ይቀጥላሉ፡፡
ኢየሱስ የእግዚአብሔር ዘላለማዊ ልጅ ኃጢያት የሌለበትን ስብእና ሲወስድ በባሪያ መልክ ነው የወሰደው፤ ሰማያዊ ክብሩን በመተው (ፊሊ 2፡5-11)፡፡ በሰው መልክ እንደተገለጥ አምላክ ለአባቱ መታዘዝን መማር (ዕብ 5፡8) በኃጢያት መፈተን በሰዎች በሃሰት መከሰሰ በራሱ ሰዎች መገፋት ከዚያም መሰቀል ነበረበት፡፡ ወደ አባቱ የጸለየው ጸሎት ኃይልን ለመለመን ነበር (ዮሐ 11፡41-42) እንዲሁም ጥበብን (ማር 1፡35፤ 6፡46)፡፡ ኢየሱስ እንደ ታላቅ ክህነቱ በዮሐ 17 ወደ አባቱ የጸለየው ጸሎት በአባቱ ላይ የመቤዠት እቅዱን ለመፈጸም ያለውን መታመን ያመለክታል፡፡ ጸሎቱ ለአባቱ ፈቃድ ያለውን ፍጹም መገዛት ይገልጻል፤ እኛ የእግዚአብሔር ህግ በመጣሳችን ወደ መስቀል ለመሄድ እና የሞትን ቅጣት ለመቀበል (ማቲ 26፡ 31፡46)፡፡ እርግጥ ነው በአካል ከመቃብር ተነስቶአል በእረሱ አዳኝነት ለሚያምኑ እና ከኃጢያታቸው ለሚመለሱ ይቅርታን እና ዘላለማዊ ህይወትን እንዲቀዳጁ፡፡
ለእግዚአብሔር ልጅ ወደ እግዚአብሔር ወደ አባቱ ለመጸለይ እና ለማውራት ምንም ችግር የለበትም፡፡ እንደተጠቀሰው ኢየሱስ ሰው ከመሆኑ አስቀድሞ ዘላለማዊ ግንኙነት አላቸው፡፡ ይህ ግንኙነት ስለዚህ የእግዚአብሔር ልጅ በሰውነቱ የአባቱን ፈቃድ እንደተሸከመ እና እንደፈጸመ ለልጆቹም እንዴት መዋጀትን እንዳስገኘላቸው በወንጌላት ተብራርቶአል (ዮሐ 6፡36)፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ ለሰማይ አባቱ ያለው የማያቋርጥ መገዛት በጸሎት ህይወቱ ይታደሳል የማያቁርጥ ትኩረት ይኖረዋል፡፡ የኢየሱስ ክርስቶስ የጸሎት ምሳሌነት እኛ እንድንከተለው ነው፡፡
ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሰማይ አባቱ በምድር ሆኖ ሲጸልይ ከአምላክነት አያንስም ነበር፡፡ ኃጢያት በሌለበት ማንነት እንኳ የጸሎት ህይወት የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈጸም ምን ያህል አስፈላጊ እንደሆነ አሳይቶአል፡፡ የኢየሱስ ወደ አባቱ መጸለይ ከስላሴ አካል ጋር ያለው ግንኙነት መገለጫ ነበር እና ለእኛም እንዳለብን በጸሎት ጥንካሬ እና ጥበብን ለማገኘት በእግዚአብሔር መታመን እንዳለብን ምሳሌ ነበር፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ በስጋ የተገለጠ አምላክ ሆኖ ሳለ የማያቋርጥ የጸሎት ህይወት ያስፈልገው ነበር ስዚህ ዛሬም የክርስቶስ ተከታዮች ይህ ያስፈልጋቸዋል፡፡
English
ኢየሱስ መለኮት ቢሆን ኖሮ እንዴት ወደ እግዚአብሔር ይጸልይ ነበር? ኢየሱስ ለራሱ ነበር የሚጸልየው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?