settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እውነት ነውን?

መልስ፤


ቃሉ የተረጋገጠ ማስረጃ ኢየሱስ ክርስቶስ በርግጥ ከሙታን ስለመነሣቱ ያቀርባል። የኢየሱስ ትንሣኤ በማቴዎስ 28፡1-20፤ ማርቆስ 16፡1-20፡ ሉቃስ 24፡1-53፤ እና ዮሐንስ 20፡1-21፡25 ተመዝግቧል። የተነሣው ክርስቶስ ደግሞ በሐዋርያት ሥራ መጽሐፍ ላይ ተገልጿል (ሐዋርያት ሥራ 1፡1-11)። ከእነዚህ አንቀጾች ስለ ክርስቶስ ትንሣኤ በርካታ “ማረጋገጫዎች” ማግኘት ትችላላችሁ። የመጀመሪያው የሐዋርያት አስገራሚ ለውጥ ነው። እነሱ ከጥቂት የፈሩና የተደበቁ ሰዎች ወደ ጠንካራና ጽኑዓን ምስክሮች መለወጣቸውና ወንጌልን በመላው ዓለም ማሰራጨታቸው ነው። ይህ አስገራሚ ለውጥ በፊታቸው መደረጉ ከተነሣው ክርስቶስ ይልቅ ምን ሌላ ነገር ሊያስረዳ ይችላል?

ሁለተኛው የሐዋርያው ጳውሎስ ሕይወት ነው። እሱን ከቤተ ክርስቲያን አሳዳጅነት ወደ ቤተ ክርስቲያን ሐዋርያነት ምን ቀየረው? ይህ የሆነው የተነሣው ክርስቶስ በደማስቆ መንገድ ላይ ስለተገለጠለት ነው (ሐዋርያት ሥራ 9፡1-6)። ሦስተኛው አሳማኝ ማረጋገጫ ባዶው መቃብር ነው። ክርስቶስ ባይነሣ ኖሮ፣ ሥጋው የት ይሆን ነበር? ደቀ መዛሙርቱና ሌሎችም የተቀበረበትን መቃብር ተመልክተዋል። በተመለሱ ጊዜ ሥጋው እዛ አልነበረም። መላእክት፣ እንደተናገረ ከሙታን መነሣቱን አውጀዋል (ማቴዎስ 28፡5-7)። አራተኛ፣ ለትንሣኤው ተጨማሪ ማስረጃ የሚሆነው ለብዙ ሰዎች የተገለጠበት ነው (ማቴዎስ 28፡5፣ 9፣ 16-17፤ ማርቆስ 16፡9፤ ሉቃስ 24፡13-35፤ ዮሐንስ 20፡19፣ 24፣ 26-29፣ 21፡1-14፤ ሐዋርያት ሥራ 1፡6-8፤ 1ኛ ቆሮንቶስ 15፡5-7)።

ሌለኛው ለኢየሱስ ትንሣኤ ማረጋገጫ የሚሆነው ሐዋርያት ለኢየሱስ ትንሣኤ ታላቅ ክብደት መስጠታቸው ነው። ለክርስቶስ ትንሣኤ ቁልፉ አንቀጽ 1ኛ ቆሮንቶስ 15 ነው። በዚህ ምዕራፍ፣ ሐዋርያው ጳውሎስ የክርቶስን ትንሣኤ ማወቅና ማመን በጣም ወሳኝ መሆኑን ያብራራል። ትንሣኤው በሚከተሉት ምክንያቶች ጠቃሚ ነው፡ 1) ክርስቶስ ከሙታን ካልተነሡ፣ አማኞች አይኖሩም ነበር (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡12-15)። 2) ክርስቶስ ከሙታን ካልተነሣ፣ የእሱ ለኃጢአት መሥዋዕት መሆን በቂ አይሆንም ነበር (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡16-19)። የኢየሱስ ትንሣኤ የሚያረጋግጠው ሞቱ ለኃጢአታችን ማስተስርያ ይሆን ዘንድ በእግዚአብሔር ተቀባይነት ማግኘቱን ነው። እሱ ዝም ብሎ ሞቶ ቢቀር ኖሮ፣ የሱ መሥዋዕት በቂ አለመሆኑን ያመለክት ነበር። በውጤቱም፣ ኃጢአታቸው ይቅር አይባልም ነበር፣ እንዲሁም ከሞቱ በኋላ ሞተው ይቀሩ ነበር (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡16-19)። እንደዘላለም ሕይወት የሚሆን ነገር የለም (ዮሐንስ 3፡16)። “አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኵራት ሆኖ ከሙታን ተነሥቷል” (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡20 NAS አዲሱ የአሜሪካ መደበኛ ትርጉም)።

በመጨረሻ፣ ቃሉ ግልጽ ነው፣ በኢየሱስ ክርስቶስ የሚያምኑ ሁሉ፣ እሱ እንደተነሣ ለዘላለም ሕይወት ይነሣሉ (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡20-23)። አንደኛ ቆሮንቶስ 15 ጨምሮ የሚያስረዳው የክርስቶስ ትንሣኤ የሚያረጋግጠው፣ የእሱን በኃጢአት ላይ ድል ማድረግ ሲሆን ለእኛም በኃጢአት ላይ የድል አድራጊነት ኃይል ይሰጠናል (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡24-34)። እሱ የሚያስረዳው የምንቀበለውን የክብር ተፈጥሮ ያለውን የትንሣኤ አካል ነው (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡35-49)። እሱ የሚያውጀው፣ ከክርስቶስ ትንሣኤ የተነሣ፣ በእሱ የሚያምኑ በሞት ላይ አስተማማኝ ድል ይኖራቸዋል (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡50-58)።

የክርስቶስ ትንሣኤ እንዴት ያለ የክብር እውነት ነው! “ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳይሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ፥ የማትነቃነቁም፥ የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ” (1ኛ ቆሮንቶስ 15፡58)። እንደ መጽሐፍ ቅዱስ፣ የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ ፈጽሞ በእርግጠኝነት እውነት ነው። መጽሐፍ ቅዱስ የክርስቶስን ትንሣኤ የመዘገበው፣ በ400 ሰዎች የተመሰከረለትን ነው፣ እናም ወሳኝ የሆኑ የክርስቲያን መሠረተ እምነቶችን በኢየሱስ ትንሣኤ ታሪካዊ ሐቅ ላይ ተመሥርቶ በማውጣት በመቀጠል ላይ ያለ ነው።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የኢየሱስ ክርስቶስ ትንሣኤ እውነት ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries