settings icon
share icon
ጥያቄ፤

ኢየሱስ ያድናል ማለት ምን ማለት ነው?

መልስ፤


‹‹ኢየሱስ ያድናል›› በግጭት መከላከያ ማስታወቂያዎች የታወቀ ምልክት ነው በአትሌቲክ ዝግጅት ምልክት እና ባንዲራዎችም በትንሽ አይሮፕላን በሰማይ ላይ ይለቀቃሉ፡፡ በሚያሳዝን ሁኔታ ጥቂቶች ‹‹ኢየሱስ ያድናል›› የሚለውን ቃል ሲያዩ በእውነትና በሙሉ ምን ማለት እንደሆነ ይረዱታል፡፡ አስደናቂ የሆነ ኃይል እና እውነት በእነዚህ ሁለት ቃላት ውስጥ ታጭቀዋል፡፡

ኢየሱስ ያድናል ግን ኢየሱስ ማን ነው?
ብዙ ሰዎች ኢየሱስ ክርስቶስ 2000 ዓም ገደማ በእስራኤል ይኖር የነበረ ሰው እነደ ነበር ብዙዎች ያምናሉ፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ በዙ በዓለም ላይ ያሉ ሃይማኖቶች ኢየሱስ ክርስቶስ ጥሩ አስተማሪና ነብይ እንደነበር ያምናሉ፡፡ አንዚህ ሁሉ ነገሮች ሁሉ እውነት ሆኖ እያለ ኢየሱስ ማን እንደሆነ በትክክል አይገልጹም ወይንም ኢየሱስ እንዴትና ለምን ኢየሱስ እንደሚያድን አይገልጹም፡፡ ኢየሱስ በሰው አምሳል የተገለጠ እግዚአብሔር ነው (ዮሐ 1፡1? 14) ኢየሱስ መለኮት ነው፡፡ ወደ ምድር ፍጹም ሰው ሆኖ መጣ (1ዮሐ 4፡12) መለኮት በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ሰው ሆኖአለ ይህውም እኛን ስለማዳን፡፡ ያም ደግሞ የሚቀጥለውን ጥያቄ ያስከትላል፡ ለምንድን ነው መዳን የሚያስፈልገን?

ኢየሱስ ያድናል ግን ለምንድን ነው መዳን የሚያስፈልገን?
መጽሐፍ ቅዱስ በምድር ላይ ያለ ሰው ሁሉ እንደበደለ ያስተምረናል (መክ 7፡20? ሮሜ 3፡23)፡፡ ኃጢያት አንድ የሆነ ነገር የእግዚአብሔርን ቅዱስ እና ፍጹም ማንነጽ በመቃወም በሃሳብ በቃል በተግባርማድረግ ነው፡፡ በኃጢያታችንም ምክንያት ሁላችንም የእግዚአበሔር ፍርድ አለብን (ዮሐ 2፡18?36)፡፡ እግዚአብሔር ፍጹም ጻድቅ ነው ስለዚህ ኃጢያትን አይፈቅድም እናም ክፉዎችን ሳይቀጣ አይተውም፡፡ እግዚአብሔር ወሰን የሌለው ዘላለማዊ እንደመሆኑ እና ሁሉም ኃጢያት በአጠቃላይ እርሱን መቃወም ነው (መዝ 51፡4) ዘላለማዊ ቅጣት ብቻ ነው በቂ የሚሆነው፡፡ የኃጢያት ትክክለኛው ቅጣት ዘላለማዊ ሞት ብቻ ነው፡፡ ለዚህ ነው ድኅነት የሚያስፈልገን፡፡

ኢየሱስ ያድናል ግን እንዴት ነው የሚያድነግ?
የበደልነው እግዚአብሔር ወሰን የለውም በተመሳሳይ ወስን የሆነው አካል (እኛ) ለኃጢያታችን ወሰን ለሌለው ጊዜ መክፈል ነበረብን ወይንም ወሰን የሌለው ክርስቶስ ለእኛ ኃጢያት አንድ ጊዜ ዋጋውን መክፈል ነበረበት፡፡ ሌላ አማራጭ አልነበረም፡፡ ኢየሱሰ በእኛ ቦታ በመሞት አዳነን፡፡ በኢየሱስ ክርስቶስ አካል እግዚአብሔር ራሱን በእኛ ፈንታ መስዋዕት አደረገ፤ እርሱ ብቻ ሊከፍለው የሚችለውን ወሰን የሌለውን እና ዘላለማዊ ቅጣት (2 ቆሮ 5:21? 1 ዮሐ 2:2). እኛ የሚገባንን ቅጣት የኃጢያታችንን ውጤት ኢየሱስ ክርስቶስ እኛን ከዘለአለም አስከፊ ከሆነው የዘለዓለም ጥፋት ለማዳን ቅጣታችንን ወሰደ፡፡ ለእኛ ባለው ትልቅ ፍቅር ምክንያት ኢየሱስ ነፍሱን አሳልፎ ሰጠን (ዮሐ 15:13), እኛ የሚገባንን ቅጣት ግን ደግሞ ለመክፈል የማንችለውን፡፡ ኢየሱስ የእኛን የኃጢያት እዳ ለመክፈል በቂ እንደሆነ ለመግለጽ ከሙታን ተነሳ፡፡(1 ቆሮ 15).

ኢየሱስ ያድናል ግን እንዴት ነው የሚያድነው?
ኢየሱስ ክርስቶስ የእርሱን የድኅነት ስራ ሊቀበሉ የሚወዱትን ሁሉ ያድናል፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ እርሱ ስለ ኃጠያት በከፈለው ዋጋ ብቻ የሚያምኑትን ያድናቸዋል፡፡ (ዮሐ 3:16? ሥራ 16:31). የኢየሱስ ክርስቶስ መስዋዕትነት የሰው ልጆችን ቅጣት ሁሉ ለመክፈል በቂ ሆኖ ሳለ ኢየሱስ የእርሱን ውድ ስጦታ ለመቀበል ፍቃደኛ የሆኑትን ብቻ ያድናቸዋል፡፡ (ዮሐ 1:12).

ኢየሱስ ያድናል ማለት ምን ማለት እንደሆነ አሁን ከተረዳህ እና የግል አዳኝ አድርገህ ልታምንበት ከፈለግክ እነዚህን መረዳትህን እርግጠኛ ሁን እና በእምነት እርምጃ በእነዚህ እግዚአብሔርን ተገናኘው፡፡ ‹‹እግዚአብሔር ኃጢያተኛ መሆኔን አውቃለሁ እናም በኃጢያቴ ምክንያት ለዘለአለም ከአንተ መለየት እንደሚገባኝ አውቃለሁ፡፡ ባይገባኝም እንኳ በልጅ በኢየሱስ ሞት በኩል ስላዘጋጀህልን የኃጢያት መስዋዕተ አመሰግንሃለሁ፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስ ለእኔ እንደሞተ አምናለሁ እርሱ ብቻ ሊያድነኝ እንደሚችልም አምናለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ከኃጢያት ይልቅ ላንተ እንድኖር እርዳኝ፡፡ ከዚህ በኋላ አስደናቂውን ደኅንነት ለሰጠህኝ ላንተ ምላሽ በመስጠት እንድኖር እርዳኝ፡፡ ኢየሱስ ሆይ ስላዳንከኝ አመሰግንሃሉ!

English


ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ
ኢየሱስ ያድናል ማለት ምን ማለት ነው?
© Copyright Got Questions Ministries