settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የጌታ ጸሎት ምንድነው፣ መጸለይስ አለብን?

መልስ፤


የጌታ ጸሎት፣ ጌታ ኢየሱስ ደቀ-መዛሙርቱን ጸሎት ያስተማረበት ነው፣ ማቴዎስ 6:9-13 እና ሉቃስ 11:2-4። ማቴዎስ 6:9-13 ይላል፣ “እንግዲህ እናንተስ እንዲህ ጸልዩ። በሰማያት የምትኖር አባታችን ሆይ፥ ስምህ ይቀደስ፤ መንግሥትህ ትምጣ፤ ፈቃድህ በሰማይ እንደ ሆነች እንዲሁ በምድር ትሁን፤ የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን፤ እኛም ደግሞ የበደሉንን ይቅር እንደምንል በደላችንን ይቅር በለን፤ ከክፉም አድነን እንጂ ወደ ፈተና አታግባን፤ መንግሥት ያንተ ናትና ኃይልም ክብርም ለዘለዓለሙ፤ አሜን።” ብዙ ሰዎች የጌታን ጸሎት አላግባብ ይረዱታል፣ ቃል በቃል መድገም ያለብን ጸሎት አድርገው። አንዳንድ ሰዎች የጌታን ጸሎት እንደ አስማት ቀመር ይወስዱታል፣ ቃላቱ ራሳቸው የሆነ ኃይል እንዳላቸው ወይም በእግዚአብሔር ላይ ተጽዕኖ እንደሚያሳድሩ።

መጽሐፍ ቅዱስ የሚያስተምረን ተቃራኒውን ነው። እግዚአብሔር በምንጸልይበት ሰዓት በተሻለ የሚፈልገው ልባችንን እንጂ ቃላታችንን አይደለም። “አንተ ግን ስትጸልይ፥ ወደ እልፍኝህ ግባ መዝጊያህንም ዘግተህ በስውር ላለው አባትህ ጸልይ፤ በስውር የሚያይ አባትህም በግልጥ ይከፍልሃል። አሕዛብም በመናገራቸው ብዛት እንዲሰሙ ይመስላቸዋልና ስትጸልዩ እንደ እነርሱ በከንቱ አትድገሙ” (ማቴዎስ 6፡6-7)። በጸሎት ላይ፣ ልባችንን ለእግዚአብሔር ማፍሰስ አለብን (ፊሊጵስዩስ 4፡6-7)፣ የሚታወሱ ቃላትን ለእግዚአብሔር መድገም ሳይሆን።

የጌታ ጸሎት መወሰድ ያለበት እንደ ምሳሌ፣ አገባብ፣ እና እንዴት እንደሚጸለይ ነው። እሱም በጸሎት ውስጥ “ተካታች ነገሮችን” ይሰጠናል። እሱም እንዴት እንደሚከፋፈል እነሆ። “በሰማይ የምትኖር አባታችን ሆይ” ጸሎታችንን ለማን እንደምናቀርብ ያስተምረናል—ለአብ። “ስምህ ይቀደስ” እግዚአብሔርን አንድናመልክ፣ እና እሱን ስለማንነቱ እንድናመሰግን ይነግረናል። ውዳሴው “መንግሥትህ ትምጣ፣ ፍቃድህ በሰማይ እንደሆነች እንዲሁም በምድር ትሁን” የሚለው እግዚአብሔር በሕይወታችንና በዓለም ስላለው ዕቅድ እንድንጸልይ የሚያስታውሰን ነው፣ ለግል ዕቅዳችን ሳይሆን። የእግዚአብሔር ፍቃድ እንዲሆን እንጸልያለን፣ የእኛ ሐሳብ ሳይሆን። እግዚአብሔርን ስለሚያስፈልገን ነገር እንድንለምነው እንበረታታለን “የዕለት እንጀራችንን ዛሬ ስጠን።” “በደላችንን ይቅር በለን እኛም የበደሉንን ይቅር እንደምንል” የሚያስታውሰን፣ ኃጢአታችንን ለእግዚአብሔር እንድንናዘዝና ከሱም ዞር እንድንል ነው፣ እንዲሁም ሌሎችን ይቅር እንድንል፣ እግዚአብሔር ይቅር እንዳለን። የጌታ ጸሎት ማጠቃለያ፣ “ወደ ፈተና አታግባን፣ ከክፉ አድነን እንጂ” በኃጢአት ላይ ድልን ለማግኘት ዕርዳታ መጠየቂያ የትሕትና ልመና ነው፣ እንዲሁም ከሰይጣን ጥቃት መጠበቂያ።

እንደገናም፣ የጌታ ጸሎት አስታውሰን ወደ እግዚአብሔር መልሰን የምንደግመው ጸሎት አይደለም። እሱ እንዴት መጸለይ እንዳለብን ምሳሌ ነው። የጌታን ጸሎት ማስታወስ ላይ ችግር አለን? በርግጥ የለውም! የጌታን ጸሎት መልሰን ወደ እግዚአብሔር መጸለይ ችግር አለበትን? የለውም፣ ልብህ በእርሱ ላይ ካለና እውነት እንደምትለው ቃል ከሆነ። ጸሎት ላይ፣ እግዚአብሔር በጣም የሚፈልገው ከእርሱ ጋር መገናኘታችንንና ከልባችን መናገራችንን ነው፣ ከምንጠቀምባቸው የተወሰኑ ቃላት ይልቅ። ፊሊጵስዩስ 4፡6-7 ይገልጻል፣ “በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ። አእምሮንም ሁሉ የሚያልፍ የእግዚአብሔር ሰላም ልባችሁንና አሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል።”

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የጌታ ጸሎት ምንድነው፣ መጸለይስ አለብን?
© Copyright Got Questions Ministries