ጥያቄ፤
የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት በሉይ ኪዳን የት ጋር ነው የሚተነብየው?
መልስ፤
በዙ የብሉይ ኪዳን ትንቢቶች ስለ ክርስቶስ ኢየሱስ አሉ፡፡ አንዳንድ ተርጓሚዎች ቁጥራቸውን በመቶዎች ያደርሱታል፡፡ የሚከተሉት ግን ግልጽ እና ዋና ዋናዎቹ ናቸው፡፡
ስለመወለዱ አስመልክቶ፡ ኢሳ 7፡14፡ ‹‹ስለዚህ ጌታ ራሱ ምልክት ይሰጣችኋል እነሆ፥ ድንግል ትፀንሳለች፥ ወንድ ልጅም ትወልዳለች፥ ስሙንም አማኑኤል ብላ ትጠራዋለች።›› ሚኪ 5፡2፡ ‹‹አንቺም ቤተ ልሔም ኤፍራታ ሆይ፥ አንቺ በይሁዳ አእላፋት መካከል ትሆኚ ዘንድ ታናሽ ነሽ ከአንቺ ግን አወጣጡ ከቀድሞ ጀምሮ ከዘላለም የሆነ፥ በእስራኤልም ላይ ገዥ የሚሆን ይወጣልኛል።››
የኢየሱስ አገልግሎት እና ሞት፡ ዘካ 9፡9 ‹‹አንቺ የጽዮን ልጅ ሆይ፥ እጅግ ደስ ይበልሽ አንቺ የኢየሩሳሌም ልጅ ሆይ፥ እልል በዪ እነሆ፥ ንጉሥሽ ጻድቅና አዳኝ ነው ትሑትም ሆኖ በአህያም፥ በአህያይቱ ግልገል በውርጫይቱ ላይ ተቀምጦ ወደ አንቺ ይመጣል።›› መዝ 22፡16-18፡ ‹‹ብዙ ውሾች ከብበውኛልና የክፋተኞች ጉባኤም ያዘኝ እጆቼንና እግሮቼን ቸነከሩኝ።አጥንቶቼ ሁሉ ተቈጠሩ እነርሱም አዩኝ ተመለከቱኝም።ልብሶቼን ለራሳቸው ተከፋፈሉ፥ በቀሚሴም ላይ ዕጣ ተጣጣሉ።››
ስለ ኢየሱስ ልክ ግልፅ እንደሆኑት ትንቢቶች የኢሳያስ 53 ሙሉው ምዕራፍ ነው፡፡ ኢሳ 53፡3-7፡ በተለይ ምን ስህተት የለበትም፡ ‹‹የተናቀ ከሰውም የተጠላ፥ የሕማም ሰው ደዌንም የሚያውቅ ነው ሰውም ፊቱን እንደሚሰውርበት የተናቀ ነው፥ እኛም አላከበርነውም።በእውነት ደዌያችንን ተቀበለ ሕመማችንንም ተሸክሞአል እኛ ግን እንደ ተመታ በእግዚአብሔርም እንደ ተቀሠፈ እንደ ተቸገረም ቈጠርነው።እርሱ ግን ስለ መተላለፋችን ቈሰለ፥ ስለ በደላችንም ደቀቀ የደኅንነታችንም ተግሣጽ በእርሱ ላይ ነበረ፥ በእርሱም ቍስል እኛ ተፈወስን።እኛ ሁላችን እንደ በጎች ተቅበዝብዘን ጠፋን ከእኛ እያንዳንዱ ወደ ገዛ መንገዱ አዘነበለ እግዚአብሔርም የሁላችንን በደል በእርሱ ላይ አኖረ።ተጨነቀ ተሣቀየም አፉንም አልከፈተም ለመታረድ እንደሚነዳ ጠቦት፥ በሸላቾቹም ፊት ዝም እንደሚል በግ፥ እንዲሁ አፉን አልከፈተም።››
‹‹ሰባ ሰባቱ›› ዳንኤል ምእራፍ 9 ትንቢት የሚተነብየው ትክክለኛ ኢየሱስ መሲሁ የሚገደልበትን ቀን ነው፡፡ ኢሳ 50፡6 ኢየሱስ የተቀበለውን መከራ ይጠቅሳል፡፡ ዘካ 12፡10 ኢየሱስ ከሞተ በኋላ ስለሚያለቅሱለት ለቅሶ ይናገራል፡፡ ቡዙ ምሳሌዎችን ማቅረብ ይቻላል ግን እነዚህ ይበቃሉ፡፡ በሉይ ኪዳን በእርግጠኝነት ስለኢየሱስ ክርስቶስ በመሲህነት መምጣት ተንብዮአል፡፡
English
የኢየሱስ ክርስቶስን መምጣት በሉይ ኪዳን የት ጋር ነው የሚተነብየው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?