settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የሮማውያን የድነት መንገድ ማለት ምንድ ነው?

መልስ፤


የሮማውያን የድነት መንገድ በሮሜ መጽሐፍ ውስጥ ያሉትን ጥቅሶች በመጠቀም የድነትን የምስራች ቃል ማብራራት ማለት ነው። ለምን ድነት እንደሚያስፈልገን፣ እግዚሐብሔር እንዴት አድርጎ ድነትን እንዳዘጋጀልን፣ ድነትን እንዴት መቀበል እንደምንችልና የድነትን ውጤቶች ቀለል ብሎ ጥልቀት ባለው ዘዴ የተገለፁበት መንገድ ነው።

በሮማውያን የድነት መንገድ የመጀመሪያው ጥቅስ ሮሜ 3፡ 23 ነው። “ሁሉም ኃጢያትን ሰርተዋልና የእግዚሐብሔርም ክብር ጎድሎአቸዋል።” ሁላችንም ኃጢያት ሰርተናል። እግዚሐብሔርን የሚያሳዝኑ ብዙ ነገሮችን ፈፅመናል። ፃድቅ የሆነ አንድም ሰው የለም። ኃጢያት በሕይወታችን የሰራውን ምስል ግልፅ በሆነ መንገድ በሮሜ 3፡ 10-18 ተቀምጧል። በሮማውያን የድነት መንገድ የሚገኘው የወንጌል ጥቅስ ሮሜ 6፡ 23 ሲሆን ስለኃጢያት ውጤት ያስተምረናል። “የኃጢያት ደመወዝ ሞት ነውና፣ የእግዚሐብሔር የፀጋስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው።” ለኃጢያታችን ያገኘነው ቅጣት ሞት ነው። የስጋ ሞት ብቻ ሳይሆን ነገር ግን ዘላለማዊ ሞት!

ሦስተኛው የሮማውያን የድነት መንገድ የሚቀጥለው ሮሜ 6፡ 23 ካቋረጠበት “የእግዚሐብሔር የፀጋ ስጦታ ግን በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን የዘላለም ሕይወት ነው” ብሎ ይቀጥላል። ሮሜ 5፡ 8 ሲያብራራ “ነገር ግን ኃጢያተኞች ሳለን ክርስቶስ ስለእኛ ሞቶአልና እግዚሐብሔር ለኛ ያለውን የራሱን ፍቅር ያስረዳል።” ኢየሱስ ክርስቶስ ለኛ ሲል ሞተ! በኢየሱስ ሞት የኃጢያታችን ዋጋ ተከፈለ! የኢየሱስ ትንሳኤ የሚያረጋግጠው ነገር ቢኖር እግዚሐብሔር የኢየሱስን ሞት እንደ ኃጢያታችን ቅጣት መቀበሉን ነው።

በሮማውያን የድነት መንገድ አራተኛ መቆሚያችን ሮሜ 10፡ 9 ነው። “ኢየሱስ ጌታ እንደሆነ በአፍህ ብትመሰክር እግዚሐብሔርም ከሙታን እንዳስነሳው በልብህ ብታምን ትድናለህና።” ኢየሱስ ክርስቶስ በኛ ቦታ ስለሞተ ማድረግ ያለብን ነገር በእርሱ ማመን ነው፣ የእርሱ መሞት ለኃጢያታችን የተከፈለ ደመወዝ መሆኑን ማመን እኛን ያድነናል! ሮሜ 10፡ 13 እንደገና እንደዚህ ያስቀምጠዋል። “የጌታን ስም የሚጠራ ሁሉ ይድናልና።” ኢየሱስ የሞተልን የኃጢያታችንን ቅጣት ለመክፈልና ከዘላለማዊ ሞት ሊያድነን ነው። የኃጢያታችን ስርየት የሆነው ድነት ኢየሱስ ክርስቶስን እንደጌታና አዳኝ አምነው ለተቀበሉት ሁሉ የተሰጠ ነው።

የሮማውያን የድነት መንገድ የመጨረሻ ገፅታ የድነት ውጤቶችን የሚያሳየው ነው። ሮሜ 5፡ 1 ይህንን አስገራሚ መልዕክት ይዟል። “እንግዲህ በእምነት ከፀደቅን በእግዚሐብሔር ዘንድ በጌታችን በኢየሱስ ክርስቶስ ሰላምን እንያዝ።” በኢየሱስ ክርስቶስ በኩል ከእግዚሐብሔር ጋር ሰላም ያለው ግንኙነት ሊኖረን ይችላል። ሮሜ 8፡1 ሲያስተምረን “እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱሰ ላሉት አሁን ኩነኔ የለባቸውም” ይላል። ኢየሱስ በእኛ ቦታ በመሞቱ ምክንያት በኃጢያታችን አይፈረድብንም። በመጨረሻም በሮሜ 8፡ 38-39 ይህን የመሰለ ውድ ተስፋ ከእግዚሐብሔር ተገብቶልናል። “ሞት ቢሆን፣ ዝምታም ቢሆን፣ልዩ ፍጥረትም ቢሆን፣ በክርስቶስ ኢየሱስ በጌታችን ካለ ከእግዚሐብሔር ፍቅር ሊለየን እንዳይችል ተረድቻለሁ።” የሮማውያንን የድነት መንገድ መከተል ትፈልጋለህ? የምትስማማ ከሆነ ይህንን ቀላል ፀሎት ወደ እግዚሐብሔር ማቅረበ ትችላለህ። ይህንን ፀሎት ስታቀርብ ለድነትህ በኢየሱስ ክርስቶስ መደገፍህን ለእግዚሐብሔር የምታስታውቅበት መንገድ ነው። ቃላቶቹ በራሳቸው ድነትን አያስገኙልህም። በኢየሱስ ክርስቶስ መታመን ብቻ ነው ድነትን የሚያስገኘው! “እግዚሐብሔር ሆይ በአንተ ላይ ኃጢያት ሰርቼአለሁና ቅጣት ይገባኛል። ለኔ የሚገባውን ቅጣት ኢየሱስ ክርስቶስ ተቀብሎታልና በእርሱ በመታመኔ ይቅርታ ተደርጎልኛል። ለድነቴ ባንተ እርዳታ እምነቴን ባንተ ጥያለሁ። ስለአስደናቂው ፀጋህና ይቅርታህ እንዲሁም ስለየዘላለም ሕይወት ስጦታህ አመሰግንሐለሁ! አሜን!

እዚህ ባነበብከው ምክንያት ለክርስቶስ ውሳኔ ላይ ደርሰሃል? እንዲያ ከሆነ፣ “ዛሬ ክርሰቶስን ተቀብያለሁ” የሚለውን ቁልፍ ተጫን

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የሮማውያን የድነት መንገድ ማለት ምንድ ነው?
© Copyright Got Questions Ministries