ጥያቄ፤
ሰንበት ምን ቀን ነው፣ ቅዳሜ ወይስ እሑድ? ክርስቲያኖች የሰንበትን ቀን መጠበቅ ይገባቸዋልን?
መልስ፤
ተዘውትሮ ይባላል “እግዚአብሔር ሰንበትን በኤደን መሥርቷል” በሰንበትና በፍጥረት መካከል ባለው ግንኙነት ምክንያት፣ በዘጸአት 20፡11። ምንም እንኳ የእግዚአብሔር ዕረፍት በሰባተኛው ቀን (ዘፍጥረት 2፡3) መጪውን የሰንበት ሕግ በንግር ቢያመላክትም፣ አንዳችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ የሰንበት ማስረጃ የለም፣ የእስራኤል ልጆች ምድረ-ግብፅን ከመልቀቃቸው ቀደም ብሎ። በቅዱስ ቃሉ አንዳችም ቦታ ምንም ዓይነት ፍንጭ የለም፣ ሰንበትን የመጠበቅ ልምምድ ከአዳም ጀምሮ እስከ ሙሴ ድረስ ስለመኖሩ።
የእግዚአብሔር ቃል እሱን ፈጽሞ ግልጽ አድርጎታል፣ ሰንበትን መጠበቅ በእግዚአብሔርና በእስራኤል መካከል ልዩ ምልክት መሆኑን። “የእስራኤልም ልጆች ለልጅ ልጃቸው ለዘላለም ቃል ኪዳን በሰንበት ያርፉ ዘንድ ሰንበትን ይጠብቁ። እግዚአብሔር ሰማይንና ምድርን በስድስት ቀን ስለ ፈጠረ፥ በሰባተኛውም ቀን ከሥራው ስላረፈና ስለ ተነፈሰ፥ በእኔና በእስራኤል ልጆች ዘንድ የዘላለም ምልክት ነው።” (ዘጸአት 31:16–17)።
በዘዳግም 5፣ ሙሴ አስርቱን ትዕዛዛት ለቀጣዩ የእስራኤላውያን ትውልድ መልሶ ያኖራል። እዚህ፣ ሰንበትን ስለ መጠበቅ ካዘዘ በኋላ፣ ቁጥር 12—14፣ ሙሴ ሰንበት ለእስራኤል ሕዝብ የተሰጠበትን ምክንያት ይገልጻል፡ “አንተም በግብፅ ባሪያ እንደ ነበርህ አስብ እግዚአብሔር አምላክህ በጸናች እጅና በተዘረጋ ክንድ ከዚያ አወጣህ ስለዚህ እግዚአብሔር አምላክህ የሰንበትን ቀን ትጠብቅ ዘንድ አዘዘህ” (ዘዳግም 5፡15)።
እግዚአብሔር ሰንበትን ለእስራኤላውያን የሰጠበት ሐሳብ ተፈጥሮን እንዲያስታውሱ አልነበረም፣ ነገር ግን የግብፅ ባርነታቸውንና የእግዚአብሔርን ማዳን እንዲያስታውሱ ነው። ሰንበትን ለመጠበቅ መሟላት ያለባቸውን ተገንዘቡ፡ በ’ዛ የሰንበት ሕግ የተቀመጠ ሰው ቤቱን በሰንበት ትቶ መሄድ አይችልም (ዘጸአት 16፡29)፣ እሳት ማቀጣጠል አይችልም (ዘጸአት 35፡3)፣ እንዲሁም ማንንም እንዲሠራ ሊያደርግ አይችልም (ዘዳግም 5፡14)። የሰንበትን ሕግ የሻረ ሰው ይገደል ነበር (ዘጸአት 31፡15፤ ዘኅልቍ15፡32—35)።
የአዲስ ኪዳን ገጾችን መመርመር አራት ጠቃሚ ነጥቦችንን ያሳየናል፡ 1) ክርስቶስ በትንሣኤ አካሉ ሲገለጥ፣ የተጠቀሰው ቀን፣ ዘወትር ከሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን ነው (ማቴዎስ 28:1፣ 9፣ 10፤ ማርቆስ 16:9፤ ሉቃስ 24:1፣ 13፣ 15፤ ዮሐንስ 20:19፣ 26)። 2) ከሐዋርያት ሥራ እስከ ራዕይ ሰንበት የተጠቀሰበት ጊዜ ለአይሁድ የወንጌላዊነት ዓላማ ነው፣ መቼቱም ዘወትር በምኵራብ ነው (ሐዋርያት ሥራ ምዕራፍ 13—18)። ጳውሎስ ጽፏል፣ “ለአይሁድ እንደ አይሁድ ሆንኩ፣ አይሁዶችን አድን ዘንድ” (1ቆሮንቶስ 9፡20)። ጳውሎስ ወደ ምኵራብ የሚሄደው ለኅብረት እና ከቅዱሳን ጋር ለመንጻት አልነበረም፣ ነገር ግን የጠፉትን ኃጢአታቸውን ለማሳየትና ለማዳን ነበር። 3) ጳውሎስ አንድ ጊዜ “ካሁን በኋላ ወደ አሕዛብ እሄዳለሁ” ካለ በኋላ (ሐዋርያት ሥራ 18፡6)፣ ሰንበት ፈጽሞ እንደገና አልተጠቀሰም። እና 4) ከሰንበት ቀን ጋር የሚያስተሳስር ሐሳብ ከመሰንዘር ይልቅ፣ የአዲስ ኪዳን አስታዋሽ ተቃራኒውን ነው የሚያስረግጠው (ከላይ ከተጠቀሡት 3 የተለየ ነጥብ ጭምር፣ ቆላስያስ 2፡16 ላይ ይገኛሉ)።
ከላይ ያለውን ነጥብ 4ን በጣም ቀረብ ብሎ መመልከት የአዲስ ኪዳን አማኞች ሰንበትን ለመጠበቅ ግዴታ የለባቸውም፣ እናም ደግሞ የሚያመላክተው የእሑድ “የክርስቲያን ሰንበት” ሐሳብም መጽሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም። ከላይ አንደተብራራው፣ አንድ ጊዜ ብቻ ነው ሰንበት የተጠቀሰበት፣ ጳውሎስ በአሕዛብ ላይ ማተኮር ከጀመረ በኋላ፣ “እንግዲህ በመብል ወይም በመጠጥ ወይም ስለ በዓል ወይም ስለ ወር መባቻ ወይም ስለ ሰንበት ማንም አይፍረድባችሁ። እነዚህ ሊመጡ ያሉት ነገሮች ጥላ ናቸውና፥ አካሉ ግን የክርስቶስ ነው።” (ቆላስያስ 2፡16—17)። የአይሁድ ሰንበት በመስቀል ተወግዷል፣ ክርስቶስ “በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው” (ቆላስያስ 2፡14)።
ይህ ሐሳብ በአዲስ ኪዳን ከአንድ ጊዜ በላይ ተደግሟል፡ “ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ። ቀንን የሚያከብር ለጌታ ብሎ ያከብራል” (ሮሜ 14:5–6ሀ)። አሁን ግን እግዚአብሔርን ስታውቁ ይልቅስ በእግዚአብሔር ስትታወቁ እንደ ገና ወደ ደካማ ወደሚናቅም ወደ መጀመሪያ ትምህርት እንዴት ትመለሳላችሁ? እንደ ገና ባሪያዎች ሆናችሁ ዳግመኛ ለዚያ ልትገዙ ትወዳላችሁን? ቀንንና ወርን ዘመንንም ዓመትንም በጥንቃቄ ትጠብቃላችሁ” (ገላትያ 4፡9—10)።
አንዳንዶች ግን በአጽንዖት ይናገራሉ፣ ማለትም፣ ለቁስጥንጥንያ በተሰጠው ውክልና በ321 ዓ.ም ሰንበት ከቅዳሜ ወደ እሑድ ተቀይሯል በሚል። የጥንቷ ቤተ-ክርስቲያን ለአምልኮ የምትሰበሰበው ምን ቀን ነበር? ቅዱስ ቃሉ የሰንበት (የቅዳሜ) ስብሰባ መኖሩን ፈጽሞ አይጠቅስም፣ ለአማኞች ኅብረትም ሆነ ለአምልኮ። ሆኖም፣ ግልጽ የሆኑ አንቀጾች አሉ በሳምንቱ መጀመሪያ ቀን ስለመደረጉ። ለምሳሌ፣ ሐዋርያት ሥራ 20፡7 “ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን እንጀራ ለመቁረስ ተሰባሰብን” ይላል። በ1 ቆሮንቶስ 16፡20 ጳውሎስ የቆሮንቶስን አማኞች ያሳስብ ነበር፣ “ከሳምንቱም በመጀመሪያው ቀን እያንዳንዱ እንደቀናው ገንዘቡን ያስቀምጥ” እያለ። ጳውሎስ ይህንን ስጦታ እንደ “አገልግሎት” ከሰየመው ወዲህ፣ 2 ቆሮንቶስ 9፡12 ላይ፣ ይሄ ገንዘብ ማሰባሰብ የግድ የሚያያዘው ከክርስቲያን ስብሰባ የእሑድ አምልኮ አገልግሎት ጋር ነው። ከታሪክ አኳያ እሑድ፣ ቅዳሜ ሳይሆን፣ በቤተ-ክርስቲያን የክርስቲያኖች የመሰባሰቢያ መደበኛ ቀን ነበር፣ እናም ልምምዱ ወደ ኋላ ወደ አንደኛው ክፍለ-ዘመን ቀናት ይዘልቃል።
ሰንበት የተሰጠው ለእስራኤል ነው እንጂ ለቤተ-ክርስቲያን አይደለም። ሰንበት አሁንም ቅዳሜ ነው፣ እሑድ ሳይሆን፣ እናም ፈጽሞ አልተለወጠም። ነገር ግን ሰንበት የብሉይ ኪዳን ሕግ አካል ነው፣ እናም ክርስቲያኖች ከሕግ ባርነት ነጻ ናቸው (ገላትያ 4:1-26፤ ሮሜ 6:14)። ሰንበትን መጠበቅ ከክርስቲያኖች አይጠበቅም— ቅዳሜ ይሁን እሑድ። ከሳምንቱ የመጀመሪያው ቀን፣ እሑድ፣ የጌታ ቀን (ራዕይ 1፡10) አዲሱን ፍጥረት ያከብራል፣ ከክርስቶስ ጋር እንደ እኛ ከትንሣኤ ራስ። ሙሴአዊ የሰንበት ዕረፍት እንድንከተል አንገደድም፣ ነገር ግን የተነሣውን ኢየሱስን ማገልገልን ልንከተል አሁን ነጻ ነን። ሐዋርያው ጳውሎስ እንዳለው እያንዳንዱ ክርስቲያን ግለሰብ ስለ ሰንበትን ዕረፍት መወሰን ይኖርበታል፣ “ይህ ሰው አንድ ቀን ከሌላ ቀን እንዲሻል ያስባል፥ ያ ግን ቀን ሁሉ አንድ እንደ ሆነ ያስባል፤ እያንዳንዱ በገዛ አእምሮው አጥብቆ ይረዳ” (ሮሜ 14፡5)። እግዚአብሔርን በየዕለቱ እናመልከዋለን፣ ቅዳሜ ወይ እሑድ ሳይሆን።
English
ሰንበት ምን ቀን ነው፣ ቅዳሜ ወይስ እሑድ? ክርስቲያኖች የሰንበትን ቀን መጠበቅ ይገባቸዋልን?