ጥያቄ፤
በመንፈስ ቅዱስ እንዴት ልሞላ እችላለሁ?
መልስ፤
በመንፈስ ቅዱስ መሞላትን በተመለከተ ጠቃሚው ቁጥር ዮሐንስ 14፡16 ሲሆን፣ እሱም ኢየሱስ በአማኞች ላይ መንፈስ ቅዱስ እንደሚያድርባቸውና ይህም ማደሩ ቋሚ እንደሚሆን ተስፋ የሰጠበት ነው። የሚድርብንን መንፈስ እና መንፈስ ቅዱስ መሞላትን ለይተን መመልከቱ ጠቃሚ ነው። በቋሚነት የመንፈስ ቅዱስ ማደር ለተወሰኑ ጥቂት አማኞች ብቻ የሚሆን አይደለም፣ ነገር ግን ለሁሉም አማኞች ነው። በቃሉ ውስጥ ብዙ ማጣቀሻዎች አሉ ይሄንን ድምዳሜ ለማጠናከር። በመጀመሪያ፣ መንፈስ ቅዱስ ለሁሉም በኢየሱስ አማኞች ያለ ልዩነት የሚሰጥ ነው፣ እናም በክርስቶስ ከማመን በቀር ምንም ዓይነት ቅድመ ሁኔታ ለዚህ ስጦታ አልተቀመጠም (ዮሐንስ 7፡37-39)። ሁለተኛ፣ መንፈስ ቅዱስ የሚሰጠው በዳንንበት ቅጽበት ነው (ኤፌሶን 1፡13)። ገላትያ 3፡2 ለዚሁ ሐቅ አጽንዖት ይሰጣል፣ የመንፈስ ማኅተምና ማደር የሚከናወነው በሚታመንበት ጊዜ ነው፣ በማለት። ሦስተኛ፣ መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ላይ በቋሚነት ያድራል። መንፈስ ቅዱስ ለአማኞች የሚሰጠው እንደ ቅድሚያ ክፍያ፣ ወይም በቀጣይ ለሚሆነው በኢየሱስ የሆነ ክብር ማረጋገጫ ነው (2ኛ ቆሮንቶስ 1፡22፤ ኤፌሶን 4፡30)።
ይህም መንፈስን መሞላት ከሚለው በኤፌሶን 5፡18 ከተጠቀሰው በተጻራሪው ነው። ራሳችን ሙሉ ለመሉ ለመንፈስ ቅዱስ መሰጠት አለብን፣ እሱም ሙሉ ለሙሉ እንዲያድርብን፣ እንዲሁም በዚሁ አግባብ እንዲሞላን። ሮሜ 8፡9 እና ኤፌሶን 1፡13-14 የሚያስረዳው እሱ በሁሉም አማኝ ውስጥ እንደሚያድር ነው፣ ነገር ግን ሊያዝን ይችላል (ኤፌሶን 4፡30)፣ እናም የእሱ ሥራ በውስጣችን ጸጥ ሊል ይችላል (1ኛ ተሰሎንቄ 5፡19)። እኛም ይህ እንዲሆን ስንፈቅድ፣ የመንፈስ ቅዱስን ሥራና የሱን ኃይል በውስጣችን በሙላት ሳንለማመደው እንቀራለን። መንፈስ ቅዱስን መሞላት የሚያስከትለው፣ እያንዳንዱን የሕይወታችን ክፍል፣ መምራቱንም ሆነ እኛን መቆጣጠሩን እንዲይዝ፣ ለእሱ ነጻነት መስጠት ነው። ከዚያም የእሱ ኃይል በውስጣችን ይገለጥና የምንሠራው ለእግዚአብሔር ፍሬአማ ይሆናል። የመንፈስ ቅዱስ ሙላት በውጫዊ ድርጊቶች ብቻ ተግባራዊ አይደረግም፤ እሱ ደግሞ ተግባራዊ የሚደረገው ውስጣዊ በሆኑ ሐሳቦች እና የድርጊቶቻችን ዓላማዎች ላይ ነው። መዝሙር 19፡14 እንዲህ ይላል፣ “አቤቱ፥ ረድኤቴ መድኃኒቴም፥ የአፌ ቃልና የልቤ አሳብ በፊትህ ያማረ ይሁን።”
ኃጢአት የመንፈስ ቅዱስ ሙላትን የሚያዘገይ ነው፣ ለእግዚአብሔር መታዘዝ ደግሞ የመንፈስ ቅዱስ ሙላት የሚካሄድበት ነው። ኤፌሶን 5፡18 በመንፈስ ቅዱስ እንድንሞላ ታዟል ፤ ሆኖም ይህ ማለት ለመንፈስ ቅዱስ ሙላት መጸለይ አይደለም፣ ሙላቱን የሚያመጣው። የእኛ ለእግዚአብሔር ትዕዛዞች መታዘዝ ነው መንፈስ ቅዱስ በውስጣችን እንዲሠራ ነፃነትን የሚሰጠው። አሁንም ቢሆን በኃጢአት በመበከላችን የተነሣ ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ ለመሞላት አይቻለንም። ኃጢአትን ስንሠራ፣ ወዲያውኑ ለእግዚአብሔር መናዘዝና፣ መንፈስ ቅዱስን የተሞላና መንፈስ ቅዱስ የሚመራው የመሆናችንን ቁርጠኝነት ማደስ ይኖርብናል።
English
በመንፈስ ቅዱስ እንዴት ልሞላ እችላለሁ?