settings icon
share icon
ጥያቄ፤

በመንፈስ መሠዋት/መታረድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?

መልስ፤


እጅግ በተለመደው መልኩ፣ “በመንፈስ መሠዋት/መታረድ” የሚሆነው አንድ አገልጋይ በአንዱ ላይ እጆቹን ሲጭን ነው፣ እናም ያ ሰው ወለሉ ላይ ይወድቃል፣ በመንፈስ ቅዱስ እንደ ተነካ በማሰብ። በመንፈስ መሠዋትን/መታረድን የሚለማመዱ የመጽሐፍ ቅዱስን ምንባቦች ይጠቀማሉ፣ “እንደ ሞተ ሰው ሆኑ” ስለተባሉት ሰዎች በማለት ይናገራሉ (ራዕይ 1፡17) ወይም በግንባራቸው ስለሚደፉ (ሕዝቅኤል 1፡28፤ ዳንኤል 8፡17-18፣ 10፡7-9)። ሆኖም፣ የተወሰኑ ተቃርኖዎች አሉ፣ ስለዚህ መጽሐፍ-ቅዱሳዊ በግንባር መደፋትእና በመንፈስ መሠዋት/መታረድ ልምምድ መካከል።

1. መጽሐፍ ቅዱሳዊው መደፋት/መውደቅ የግለሰቡ ምላሽ ነው፣ በራዕይ ወይም በተለየነት የሆነ ሁነት ባየ ጊዜ፣ እንደ ክርስቶስ መለወጥ ዓይነት ያለ (ማቴዎስ 17፡6)። በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ልምምድ በመንፈስ መሠዋት/መታረድ፣ ግለሰቡ ለሌላው መንካት ምላሽ ይሰጣል ወይምለተናጋሪው የክንድ ንቅናቄ።

2. መጽሐፍ ቅዱሳዊዎቹ ገጠመኞች/ሁነቶች ጥቂትና የተራራቁ ናቸው፣ እነርሱም የተከሰቱት እጅግ ባልተዘወተረና በጥቂት ሰዎች ሕይወት ላይ ብቻ ነው። በመንፈስ መታረድ ክስተት ጊዜ፣ መውደቅ ተደጋጋሚ ሁነት ነው፣ እናም እጅግ በብዛት የሚሆን ልምምድ።

3. በመጽሐፍ ቅዱሳዊ ገጠመኞች፣ ሰዎች በፍርሃት በግንባራቸው የሚደፉት፣ ከሚያዩት ምን ወይም ማንነት የተነሣ ነው። በመንፈስ መሠዋት/መታረድ ማስመሰል ላይ ወደ ኋላቸው ነው የሚወድቁት፣ አንድም በተናጋሪው ክንድ ንቅናቄ ምላሽ ወይም በቤተ-ክርስቲያን መሪዎች መነካት የተነሣ (ወይም በአንዳንድ አጋጣሚ በመገፋት)።

ሁሉም በመንፈስ የመሠዋት/መታረድ ምሳሌዎች ማሳሳቻ ናቸው ወይም ለመነካት ወይም ለመገፋት የሚደረጉ ምላሾች ናቸው እያልን አይደለም። ብዙ ሰዎች እንደሚያስረግጡት አንድ ኃይል ብርታት ወደ ኋላቸው እንዲወድቁ እንዳደረጋቸው ይገልጻሉ። ሆኖም፣ ለዚህ ጽንሰ-ሐሳብ ምንም ዓይነት መጽሐፍ ቅዱሳዊ መሠረት አናገኝም። አዎን፣ አንዳች ኃይል ወይም ብርታት ተካቶ ሊሆን ይችላል፣ እንዲያ ከሆነ ግን፣ ከእግዚአብሔር ሊሆን አይችልም፣ ብሎም የመንፈስ ቅዱስ ሥራ ውጤት።

እንደ አለመታደል ሆኖ ሰዎች ይህን የመሰለውን አጠራጣሪ ማስመሰል፣ ምንም መንፈሳዊ ፍሬ የሌለውን ይፈልጋሉ፣ ተግባራዊውን ፍሬ ከመፈለግ ይልቅ፣ እሱም መንፈስ የሚሰጠንን፣ ክርስቶስን በሕይወታችን ለማክበር ዓላማ (ገላትያ 5፡22-23)። በመንፈስ መሞላት በዚህ ዓይነቱ ማስመሰል ማስረጃ ሊሆን አይችልም፣ ነገር ግን በእግዚአብሔር ቃል በተሞላ ሕይወት እንጂ፣ እሱም ውዳሴን፣ ምስጋና ማቅረብን፣ እና ለእግዚአብሔር መታዘዝን የሚያመነጨውን።

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

በመንፈስ መሠዋት/መታረድ መጽሐፍ ቅዱሳዊ ነውን?
© Copyright Got Questions Ministries