settings icon
share icon
ጥያቄ፤

የመንፈስ ቅዱስ ሚና በዛሬው ሕይወታችን ምንድነው?

መልስ፤


እግዚአብሔር ለሰው ልጆች ከሰጣቸው ስጦታዎች ሁሉ፣ከመንፈስ ቅዱስ መገኘት የሚበልጥ የለም። መንፈስ በርካታ ተግባራት፣ ሚናዎች፣ እና ሥራዎች አሉት። የመጀመሪያው፣እሱ በሰዎች ሁሉ ልብ በየትም ስፍራ የሚሠራው ሥራ ነው። ኢየሱስ ለደቀ-መዛሙርት ነግሯቸዋል፣መንፈስን ወደ ዓለም እንደሚልክ፣ “ስለ ኃጢአት ስለ ጽድቅም ስለ ፍርድም ዓለምን ይወቅሳል” (ዮሐንስ 16፡ 7-11)። እያንዳንዱ “የእግዚአብሔር ሕሊና” አለው፣ ቢቀበሉትም ባይቀበሉትም።መንፈስ የእግዚአብሔር እውነትን በሰዎች ልቦና ውስጥ ይተገብራል፣ እነርሱን በተገቢና በበቂ ክርክሮች ለማሳመን፣ ኃጢአተኛ ስለመሆናቸው። ለእዛ ወቀሳ ምላሽ መስጠት ሰዎችን ወደ ድኅነት/መዳን ያመጣቸዋል።

አንድ ጊዜ ከዳንና የእግዚአብሔር ከሆንን፣ መንፈስ በልባችን ለዘላለም መኖርያ ያደርጋል፣እኛን በማረጋገጫ፣ በማስረጃ፣ እና በተረጋገጠ ተስፋ፣ በዘላለማዊ አቋም እንደ ልጆቹ በማድረግ።ኢየሱስ መንፈስን እንደሚልክልን ነግሮናል፣ ረዳታችን፣ አጽናኛችን፣ እና መሪያችን ይሆን ዘንድ። “እኔም አብን እለምናለሁ ለዘላለምም ከእናንተ ጋር እንዲኖር ሌላ አጽናኝ ይሰጣችኋል” (ዮሐንስ 14፡16)።የግሪኩ ቃል እዚህጋ የተተረጎመው “አማካሪ” በሚል ሲሆን ፍችውም “በስተ ጎን ሆኖ የሚጠራ” ማለት ነው፣ እሱም የሚያበረታታና የሚያጸና የሚል ሐሳብ አለው።መንፈስ ቅዱስ በአማኞች ልብ ውስጥ ቋሚ መኖርያ ይይዛል (ሮሜ 8:9፤ 1 ቆሮንቶስ 6:19-20፣ 12:13)። ኢየሱስ መንፈሱን የሰጠው እንደ “ማካካሻ” ነው፣ እሱ በሌለበት ሰዓት፣ በእኛ ላይ ያለውን ተግባር ለማከናወን፣ያደርገው የነበረውን፣ እርሱም ከእኛ ጋር በግሉ እስካለ ድረስ።

ከእነዚያ ተግባራት መካከል እውነትን መግለጥ አንዱ ነው።የመንፈስ በእኛ ውስጥ መገኘት የእግዚአብሔርን ቃል እንድንረዳና እንድንተረጉም ያበቃናል። ኢየሱስ ለደቀ-መዛሙርቱ ነግሯቸዋል፣ “ግን እርሱ የእውነት መንፈስ በመጣ ጊዜ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችኋል” (ዮሐንስ 16፡13)። እሱም ለአእምሯችን ሞላውን የእግዚአብሔርን ምክር ይገልጥልናል፣ ከአምልኮ፣ ከዶክትሪን፣እና ከክርስትና አኗኗር ጋር በተያያዘ። እሱም ከሁሉ ሉዓላዊ የሆነ መሪ ነው፣ ቀደም ብሎ የሚሄድ፣መንገዱን የሚመራ፣ መሰናክሎችን የሚያነሣ፣ መረዳትን የሚገልጥ፣እና ሁሉንም ነገር ቀለል ያለና ግልጽ የሚያደርግ። እሱም በሁሉም መንፈሳዊ ነገሮች ላይ መሄድ ባለብን መንገድ ይመራናል።ያለ እንደዚህ ዓይነቱ መሪ፣ ወደ አስቸጋሪ ስህተት እንወድቃለን። እሱ የሚገልጸው ዋነኛው የእውነት ክፋይ፣ ኢየሱስ እሱ እኔ ነኝ ያለው እንደሆነ ነው (ዮሐንስ 15፡26፤ 1 ቆሮንቶስ 12፡3)።መንፈስ ያሳምነናል፣ ስለ ክርስቶስ መለኮትነት እና ሥጋዌነት (ሥጋ መልበስ) ስለ መሲህነቱ፣ስለ መከራውና ስለ ሞቱ፣ ስለ ትንሣኤውና ዕርገቱ፣ በእግዚአብሔር ቀኝ ከፍ ስለማለቱ፣እና በሁሉም ላይ ለመፍረድ ባለው ሚና። እሱም በነገሮች ሁሉ ለክርስቶስ ክብር ይሰጣል (ዮሐንስ 16፡14)።

ሌለኛው የመንፈስ ቅዱስ ሚና ስጦታን ሰጪ መሆኑ ነው። አንደ ኛቆሮንቶስ 12 ለአማኞች የተሰጡትን መንፈሳዊ ስጦታዎች ያብራራል፣ በምድር ላይ እንደ ክርስቶስ አካል መሥራት እንድንችል።እነዚህ ስጦታዎች ሁሉ፣ ታላቅ ይሁኑ አነስተኛ፣ በመንፈስ ነው የሚሰጡት፣በምድር ላይ የእርሱ አምባሳደሮች እንሆን ዘንድ፣ የእርሱን ጸጋ ለማሳየትና እሱን ለማክበር።

መንፈስ ደግሞ በሕይወታችን ፍሬ በማፍራት ይሠራል።እሱ በውስጣችን ሲያድር እሱ ሥራውን ይጀምራል በሕይወታችን ፍሬ የማፍራት አዝመራ— ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣በጎነት፣ እምነት፣ የውሃት እና ራስን መግዛት (ገላትያ 5፡22-23)። እነዚህ የሥጋችን ሥራዎች አይደሉም፣ እነዚህን ፍሬዎች ለማፍራት የሚችሉ፣ነገር ግን እነርሱ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ሲገኝ የሚያፈሩ ናቸው።

እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን ማደሪያ ማድረጉን የምንገነዘበው፣እሱ እነዚህን ተአምራዊ ነገሮችን ሁሉ በማድረጉ ነው፣ እናም ከእኛ ጋር ለዘላለምይኖራል፣እሱም ፈጽሞ አይተወንም ወይም አይለየንም፣ በታላቅ ደስታና መጽናናት መሐል እንድንሆን ያደርጋል።ስለዚህ ውድ ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን— ስለ መንፈስ ቅዱስ እና እሱ በሕይወታችን ስላደረገው ሥራው!

English



ወደ አማርኛ መነሻ ገጽ ለመመለስ

የመንፈስ ቅዱስ ሚና በዛሬው ሕይወታችን ምንድነው?
© Copyright Got Questions Ministries