ጥያቄ፤
በመንፈስ መመላለስ ምን ማለት ነው?
መልስ፤
አማኞች የሚያድረው የክርስቶስ መንፈስ አላቸው፣ የሚያጽናና እሱም ከአብ የሚወጣ (ዮሐንስ 15፡26)። መንፈስ ቅዱስ አማኞችን በጸሎት ይረዳል (ይሁዳ 1፡20) እና “እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ስለ ቅዱሳን ይማልዳልና” (ሮሜ 8፡27)። እሱም ደግሞ አማኝን ወደ ጽድቅ ይመራል ገላትያ 5፡16-18) እናም ፍሬውን ያፈራል፣ ለእርሱ ለተሰጡት (ገላትያ 5፡22-23)። አማኞች ለእግዚአብሔር ፍቃድ መገዛት ይኖርባቸዋል፣ ብሎም በመንፈስ መመላለስ።
“መመላለስ” በመጽሐፍ ቅዱስ ዘወትር ዘይቤአዊ ነው፣ ለየዕለቱ ተግባራዊ አኗኗር። የክርስቲያን ሕይወት ጕዞ ነው፣ እናም ልንራመደው ይገባል— እኛ ቋሚ የሆነ የወደፊት ጕዞ ማድረግ አለብን። ለሁሉም አማኞች መጽሐፍ ቅዱሳዊው ደንብ (አገባብ) በመንፈስ መመላለስ እንደሚኖርባቸው ነው፡ “በመንፈስ ብንኖር በመንፈስ ደግሞ እንመላለስ” (ገላትያ 5፡25፣ KJV (ኪጀት)፤ ሮሜ 8:14)። በሌላ አገላለጽ መንፈስ ሕይወት ይሰጠናል፣ በአዲስ ልደት (ዮሐንስ 3፡6)፣ እናም በየዕለቱ በመንፈስ መኖራችንን መቀጠል ይገባናል።
በመንፈስ መመላለስ ማለት ለእርሱ ቁጥጥር መሰጠት አለብን ማለት ነው፣ የእርሱን አመራር እንከተላለን፣ እሱም በእኛ ላይ ተጽዕኖውን እንዲያሳድር መፍቀድ ይኖርብናል። በመንፈስ መመላለስ እሱን ከመቃወም/ከመቀናቀን ተቃራኒ ነው፣ ወይም እሱን ከማሳዘን (ኤፌሶን 4፡30)።
ገላትያ 5 መንፈስ ቅዱስ በአማኝ ውስጥ የሚሠራውን ሥራ ይመረምራል። ዐውደ-ጽሑፉ ከሙሴ ሕግ ነጻ ስለመሆን ነው (ገላትያ 5፡1)። በመንፈስ የሚራመዱ “ተስፋ የምናደርገውን ጽድቅ በእምነት በጉጉት ይጠብቃሉ” (ቁጥር 5) እናም ከሕግ ነጻ ናቸው (ቁጥር 18)። ደግሞም በመንፈስ የሚራመዱ “የሥጋን ምኞት አይፈጽሙም” (ቁጥር 16)። ሥጋ—በኃጢአት ኃይል ምክንያትየወደቀው ተፈጥሯችን — ከመንፈስ ጋር ቀጥተኛ ግጭት ላይ ነው (ቁጥር 17)። ሥጋ የበላይ ሲሆን/ሲቆጣጠር ውጤቱ ግልጽ ነው (ቁጥር 19-21)። መንፈስ በሚቆጣጠር ጊዜ ግን፣ እሱ መልካም ባሕርያትን በውስጣችን ይፈጥራል፣ ከሕግ ብርቱ ወቀሳ በተለየ (ቁጥር 22-23)። አማኞች “ሥጋን ከክፉ መሻቱና ከምኞቱ ጋር ሰቀሉ” (ቁጥር 24፣ እናም እንግዲህ በመንፈስ እንራመዳለን (ቁጥር 25)።
በመንፈስ የሚራመዱ ከነእርሱ ከእርሱ ጋር ይተባበራሉ፣ እናም የመንፈስን ፍሬ የሚያፈሩ ይሆናሉ። እንግዲህ፣ በመንፈስ የሚራመዱ በፍቅር ይራመዳሉ— እነርሱ ለእግዚአብሔርና ለሌላው ሰው (ለባልንጀራቸው) በፍቅር ይኖራሉ። በመንፈስ የሚራመዱ በደስታ ይራመዳሉ—እነርሱ እግዚአብሔር ላደረገው፣ እያደረገ ላለው፣ ለሚያደርገው ነገር ለደስተኝነት ማስረጃ ናቸው። በመንፈስ የሚራመዱ በሰላም ይራመዳሉ— እነርሱ ከጭንቀት ነጻ የሆነ ሕይወት ይኖራሉ፣ ጭንቀትንም እምቢ ይላሉ (ፊሊጵስዩስ 4፡6)። በመንፈስ የሚራመዱ በትዕግሥት ይራመዳሉ—እነርሱ የሚታወቁት “በትዕግሥታቸው” ነው፣ እናም ቁጣቸውን አያነዱም። በመንፈስ የሚራመዱ በቸርነት ይጓዛሉ— ለሌሎች መሻቶች/መቸገር ልባዊ ግዴታ እንዳላቸው (የሚመለከታቸው መሆኑን) ያሳያሉ። በመንፈስ የሚራመዱ በደግነት ይጓዛሉ— ድርጊታቸው መልካምነትንና ቅድስናን ያንጸባርቃል። በመንፈስ የሚራመዱ በታማኝነት ይጓዛሉ— እነርሱ በእግዚአብሔርና በቃሉ ላይ ያላቸው መታመን ጽኑ ነው። በመንፈስ የሚራመዱ በበጎነት/በጨዋነት ይጓዛሉ— ሕይወታቸው ባሕርይ ያደረገው ትሕትናን፣ ጸጋን፣ እና እግዚአብሔርን ማመስገን ነው። በመንፈስ የሚራመዱ ራሳቸውን በመቆጣጠር ይጓዛሉ— እነሱም ልከኝነትን፣ ራስን መቆጣጠርን፣ እና ለሌላው መገደድን፣ እና ለሥጋ “እምቢ” የማለት ችሎታን ያሳያሉ።
በመንፈስ የሚራመዱ በመንፈስ ቅዱስ ይታመናሉ፣ በአስተሳሰብ፣ በቃል፣ እና በሥራ ይመራቸው ዘንድ (ሮሜ 6፡11-14)። በየዕለቱ ወደፊት ያመላክታሉ፣ በየደቂቃ ደቂቃው ቅድስና፣ ልክ ኢየሱስ ያደርግ እንደነበረው፣ “መንፈስ ቅዱስ መልቶበት [እሱ] ከዮርዳኖስ ተመለሰ፥ በመንፈስም ወደ ምድረ በዳ ተመርቶ” ተፈተነ (ሉቃስ 4፡1)።
በመንፈስ መመላለስ ማለት በመንፈስ መሞላት ማለት ነው፣ እናም በመንፈስ የመሞላት አንዳንድ ውጤቶች ማመስገን፣ መዘመር፣ እና ደስታ ናቸው (ኤፌሶን 5፡18-20፤ ቆላስይስ3፡16)። በመንፈስ የሚራመዱ የመንፈስን ምሪት ይከተላሉ። እነርሱ “የክርስቶስ ቃል በውስጣቸው በሙላት እንዲያድር ይፈቅዳሉ” (ቆላስይስ 3፡16፣ ESV)፣ እናም መንፈስ የእግዚአብሔርን ቃል “በጽድቅ ለማስተማር፣ ለመገሠጽ፣ ለማረምና ለማለማመድ” ይጠቀማል (2 ጢሞቴዎስ 3፡16)። ሞላው የሕይወት መንገዳቸው የሚኖረው በወንጌል ሕግ መሠረት ነው፣ መንፈስ ወደ መታዘዝ በሚመራቸው መሠረት። በመንፈስ ስንራመድ፣ የሥጋ ኃጢአተኛ ፍላጎት ከዚያ በኋላ እኛን እንደማይገዛን እናውቃለን።
English
በመንፈስ መመላለስ ምን ማለት ነው?