ጥያቄ፤
አስርቱ ትዕዛዛት የትኞቹ ናቸው?
መልስ፤
አስርቱ ትዕዛዛት እስሬኤላዊያን ከግብጽ ከወጡ በኋላ እግዚአብሔር ለእስራኤል ህዝብ የሰጣቸው ትዕዛዛት ናቸው፡፡ አስርቱ ትዕዛዛት በቡልይ ኪዳን ያሉ 613 ህጎች ማጠቃለያ ነው፡፡ የመጀመሪያዎቹ አራት ትዕዛዛት ከእግዚአብሔር ጋር ስላለን ግንኙነት የሚናገሩ ናቸው፡፡ የመጨረሻዎቹ 6 ህጎች እርስ በእርሳችን ስለሚኖረን ግንኙነት የሚናገሩ ናቸው፡፡ አስርቱ ትዕዛዛት በዘጽ 20፡1-17 እና በዘዳግም 5፡6-12 እንደሚከተለው ተጠቅሰው እናገኛቸዋልን፡፡
1) ‹‹ከእኔ በቀር ሌሎች አማልክት አይሁኑልህ።›› ይህ ትዕዛዝ ከአንዱ ከእውነተኛው ከእግዚአብሔር ሌላ ሌሎችን አማልክትን ሁሉ ማምለክን የሚቃወም ነው፡፡ ሌሎች አማልክት ሁሉ ሀሰተኛ አማልክት ናቸው፡፡
2) ‹‹በላይ በሰማይ ካለው፥ በታችም በምድር ካለው፥ ከምድርም በታች በውኃ ካለው ነገር የማናቸውንም ምሳሌ፥ የተቀረጸውንም ምስል ለአንተ አታድርግ።አትስገድላቸው፥ አታምልካቸውምም በሚጠሉኝ እስከ ሦስተኛና እስከ አራተኛ ትውልድ ድረስ የአባቶችን ኃጢአት በልጆች ላይ የማመጣ ለሚወድዱኝ፥ ትእዛዜንም ለሚጠብቁ እስከ ሺህ ትውልድ ድረስ ምሕረትን የማደርግ እኔ እግዚአብሔር አምላክህ ቀናተኛ አምላክ ነኝና።›› ይህ ትዕዛዝ የሚቃወመው በሚታይ መልኩ እግዚአብሔርን በመተካት አማልክትን ምስልን መቅረጽን ነው፡ ፡ ለእግዚአብሔር ምንም አይነት ምስል ይህን ይመስላል ብለን ልንቀርጽለጽ አንችልም፡፡ እግዚአብሔርን የሚተካ ምስል መቅረጽ ሀሰተኛ አማልክትን ማምለክ ነው፡፡
3) ‹‹የእግዚአብሔርን የአምላክህን ስም በከንቱ አትጥራ እግዚአብሔር ስሙን በከንቱ የሚጠራውን ከበደል አያነጻውምና።›› ይህ ህግ የሚቃወመው የእግዚአብሔርን ድምጽ መከንቱ መጥራትን ነው፡፡ የእግዚአብሐር ስም በቀላሉ በከንቱ እንዲጠራ ማድረግ የለብንም፡፡ ለእግዚአብሔር ያለንን ፍቅርና አክብሮት የምናሳየው እርሱን በክብርና በአክብሮት ስንጠራው ብቻ ነው፡፡
5) ‹‹ አባትህንና እናትህን አክብር እግዚአብሔር አምላክህ በሚሰጥህ ምድር ዕድሜህ እንዲረዝም።›› ይህ ትዕዛዝ ቤተሰብን ሁልጊዜ የሚገባውን ክብር በመስጠት ማክበርን ያመለክታል፡፡
6) ‹‹አትግደል።›› ይህ ህግ የሚመለከተው አንድን ሰው አስቀድሞ አስቦ መግደልን ነው፡፡
7) ‹‹አታመንዝር›› ይህ ህግ የሚቀወመው ከራሱ ሚስት ውጪ አንድ ሰው የሚያደርገውን ጾታዊ ግንኙነት ነው፡፡
8) ‹‹አትስረቅ›› ይህ ህግ የሚቃወመው የራስ ያልሆነውን ያለ ባለቤቱ ፈቃድ መውሰድ ነው፡፡
9) ‹‹ባልንጀራህ ላይ በሐሰት አትመስክር።›› ይህ ህግ በሃሰት ሌላ ሰው ላይ መመስከርን ይከለክላል፡፡ በትክክል ወሸትን የሚቃወም ህግ ነው፡፡››
10) ‹‹የባልንጀራህን ቤት አትመኝ የባልንጀራህን ሚስት ሎሌውንም ገረዱንም በሬውንም አህያውንም ከባልንጀራህ ገንዘብ ሁሉ ማናቸውንም አትመኝ።›› ይህ ህግ የሚቃወመው የሌላው ሰው የሆነን ነገር መፈለግን ነው፡፡ መመኘት ከላይ የተጠቀሱትን ትዕዛዛት አንዱን ወደ መጣስ ሊወሰድ ይችላል፤ መግደል ማመንዘር መስረቅ፡፡ አንድን ነገር ማድረግ ትክክል ካልሆነ ያንን ነገር መመኘትም ትክክል አይደለም፡፡
ብዙ ሰዎች በተሳሳተ መልኩ አስርቱን ትዕዛዛት ቢከተሉት ከሞት በኋላ ወደ ሰማይ ለመግባት ዋስትና የሚሰጥ የተዕዛዛት ስብስበስ አድርገው ይመለከታሉ፡፡ በንጽጽር የአስርቱ ትዕዛዛት አላማ ህጉን መሉ ለሙሉ ፈጽመው መጠበቅ እንደማይችሉ እንዲረዱ የሚያስገድድና የእግዚአብሔር ምህረት እንደሚያስፈልጋቸው የሚያመለክት ነው (ሮሜ 7:7-11)፡፡ በማቲ 19፡16 አንድ ጎበዝ መሪ እንደጠየቀው ማንም ሰው አስርቱንም ትዕዛዛት ፈጽሞ መጠበቅ አይችልም፡፡ (መክ 7:20) አስርቱ ትዕዛዝ የሚያሳየን ሁላችንም ኃጢያት ሰርተናል፤ በልጁ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን ብቻ የሚገኘው የእግዚአብሔር ምህረት ያስፈልገናል፡፡
English
አስርቱ ትዕዛዛት የትኞቹ ናቸው? ሁልጊዜ በገንዘብ አያያዝ ብድር ስህተት ነው? ገንዘብ ማበደር ወይም መበደር ሁልጊዜም ስህተት ነው?